Tag Archives: Parliament

ምክር ቤት ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲሠጥ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፀደቀ

5 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ሚያዚያ 27፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሕግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲሰጥ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ አፀደቀ።

የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 3ኛ ልዩ ስብሰባውን በዛሬው ዕለት አካሂዷል።

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አደራሽ ባካሄደው ስብሰባው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ምርጫን በተያዘለት ጊዜ ማካሄድ እንደማይችል ማስታወቁን በተመለከተ የቀረቡ የመፍትሄ አማራጮችን የውሳኔ ሃሳብ እንዲሁም የብድር ስምምነቶችን ተመልክቷል።

የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ንዑስ ሰብሳቢ አቶ አበበ ጌዴቦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ በኮቪድ 19 ወረርሽኝ የተነሳ 6ኛውን ሃገራዊ ምርጫ ለማከናወን አለመቻሉን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ በምክር ቤቱ መጽደቅን ተከትሎ ቀጣይ ሕገ መንግሥት የመፍትሄ ሃሳብ እንዲያቀርብ በተመራለት መሰረት ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ ለምክር ቤቱ አቅርበዋል።

በዚህም ቋሚ ኮሚቴው ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የሕገ መንግስት ትርጓሜ እንዲሰጥ የውሳኔ ሃሳብ ማቅረቡን አስታውቀዋል።

የውሳኔ ሀሳቡ የሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 54/1 አንቀፅ 58/3 እና አንቀፅ 93 ከሕገ መንግሥት ዓላማና ግቦች እንዲሁም መሰረታዊ መርሆች ጋር ለማስተሳሰር ትርጉም እንዲሰጥባቸው የሚል ሕገ መንግሥታዊ የመፍትሄ ሃሳብ ነው ያቀረበው።

በቀረበው የውሳኔ ሀሳብ ላይ የምክር ቤት አባላት ጥያቄዎችንና አስታያየቶችን የሰጡ ሲሆን፥ በውሳኔ ሃሳቡ ላይ ሌሎች የፖለቲካ ፓርቲዎች ለምን እንዲሳተፉ አልተደረገም? በሕገ መንግሥቱ ስለምርጫ በግልጽ የተቀምጠ ውሳኔ ለምን ሕገ መንግሥዊ ትርጉም አስፈለገው የሚሉ ጥያቄዎችንም አንስተዋል።

በተጨማሪም የምክር ቤቱ አባላት በህግ ባለሙያዎች ምክር ቤቱን መበተን፣ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መደንገግ፣ ሕገ መንግሥት ማሻሻልና ሕገ መንግሥታዊ ትርጓሜን መጠቀም እንደሚቻል ማስቀመጣቸውን ጠቁመው፤ ቋሚ ኮሚቴው ሕገ መንግሥታዊ ትረጓሜን መሰረት በማድረግ ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተገቢነት ያለው መሁኑንም ያነሱም አሉ።

ከዚህ ቀደም ሕዝቡ ያላመነባቸው አወጆችና ሕገ መንግሰታዊ ማሻሻዎች ይደረጉ እንደነበር ያስታወሱት የምክር ቤቱ አባል አቶ ተስፋዬ ዳባ፥ ሕገ መንግሥቱን መሰረት አድርጎ የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ መቃረን ተገቢነት የለውም ብለዋል።

በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 102 ምርጫን ማካሄድ የፌዴራል መንግስትና የምርጫ ቦርድ ሥልጣንና ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ ቦርዱ ምርጫን ለማራዘም ያቀረበው የውሳኔ ሃሳብ ተጋቢና ህገ መንግስታዊ ነው፤ ከዚህ ውጭ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎች ኢ-ህገ መንግስታዊ ናቸው ብለዋል።

የምክር ቤቱ አባል አቶ ጫላ ለሚ በበኩላቸው፥ ምክር ቤቱ የሚወያይትበት አጀንዳ ሀገርንና ሕዝብን የሚጠቅም፤ እንዲሁም ሕገ መንግሥታዊ መሆኑን አመልክተው፤ ቋሚ ኮሚቴው ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መቀበል ተገቢ መሆኑንም ገልጸዋል።

ከምክር ቤት አባላት ለቀረቡ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ላይ ማብራሪያ የሰጡት የቋሚ ኮሚቴው ንዑስ ሰብሳቢ አቶ አበበ ጌዴቦ፥ ኮሚቴው የተሰጠውን ሃለፊነት ተቀብሎ ከህገ መንግስቱ ጋር የማይጣረስና አማራጭ የመፍትሄ ሃሳብ ያቀረበ መሆኑን ገልጸው፥ ምክር ቤቱም የቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ተቀብሎ እንዲያጸድቅ ጠይቀዋል።


ምክር ቤት ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲሰጥ የቀረበውን የውሳኔ ሃሣብ አፀደቀ https://www.fanabc.com/%e1%88%9d%e1%8a%ad%e1%88%ad-%e1%89%a4%e1%89%b1-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab-%e1%89%a6%e1%88%ad%e1%8b%b5-%e1%88%9d%e1%88%ad%e1%8c%ab%e1%8a%95-%e1%89%a0%e1%89%b0%e1%88%98%e1%88%88%e1%8a%a8%e1%89%b0/amp/


በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በጣሊያን ሪፐብሊከ መንግስት መካከል ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ክህሎት ማሻሻያና ስራ ምክር ቤቱም የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ 6ኛውን ሀገራዊ ምርጫ ማከናወን አለመቻሉን አስመልክቶ ለምክር ቤቱ ያቀረበው የውሳኔ ሀሳብ በምክር ቤቱ መጽደቅን ተከትሎ ቀጣይ ህገ መንግስታዊ የመፍትሄ ሀሳብ እንዲያቀርብ በተመራለት መሰረት ያቀረበውን የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምርጫን በተመለከተ የተቀመጡ ሶስት አንቀጾች ላይ የሕገ መንግሥት ትርጓሜ እንዲሰጥ ያቀረበውን የውሳኔ ሀሳብ መርምሮ በ25 ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ አፅድቋል።

በመቀጠልም ምክር ቤቱ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክና በጣሊያን ሪፐብሊከ መንግስት መካከል ለቴክኒክና ሙያ ስልጠና ክህሎት ማሻሻያና ስራ ፈጠራ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ እንዲሁም የጤናውን ዘርፍ ዘላቂ የልማት ግቦች ለማሳካት ለሚከናወን በውጤት ላይ የተመሰረተ ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የተደረጉ ሁለት የብርድ ስምምነቶችን አፅድቋል።


የሚኒስትሮች ም/ቤት ለሕ/ተ/ም/ቤት አርብ የመራውና ፋና ያወጣው የብድር ዝርዝሮች አልተገጣጠሙም! ሕዝቡ ማወቅ የሚሻው ብድር መገኘቱን አይደለም! ስንት? ከማን የሚሉት ከዕዳ ከፋዩ ሕዝብ ለምን ሚሥጢር ተደረጉ? https://t.co/70LTWbZU19


በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ከጃፓን አለም አቀፍ የትብብር ኤጀንሲ መካከል ለጅማ- ጭዳ እና ሶዶ-ሳውላ የመንገድ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ ያደረገውን የብድር ስምምነት፣ ከኮሪያ ኤክስፖርት-ኢምፖርት ባንክ ጋር ለአዲስ አበባ ከተማ ፈጣን አውቶቡስ መስመር ግንባታ ፕሮጀክት ማስፈጸሚያ እንዲሁም ለመሬት መረጃ አስተዳደር ሥርዓት ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረጉ የብድር ስምምነቶችን በሙሉ ድምጽ አፅድቋል።

 

የAddis Fortune ጋዜጠኛ ፋሲካ ታደለ ከጄኔራል አሣምነው ጽጌ ጋር በመጀመሪያዎቹ ሰዓታት ስላደረገችው ቃለ መጠይቅና ይዘት!

4 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ዜጠኛ ፋሲካ ታደሰ (ፎቶ ቢቢሲ አማርኛ)

 

“መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ነገር የለም። መፈንቅለ መንግሥት በየመንደሩ አይደረግም። መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግ የሚችለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ነውና ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ምናልባት የምጠረጥረው የፌዴራል መንግሥት ወደ ክልሉ ለመግባት ፈልጎ የሠጠው ምክንያት ይሆናል ብዬ ነው የምገምተው”

—ጄኔራል አሣምነው ጽጌ

 

ሰኔ 15 ምን ይመስል ነበር?

ጋዜጣችን የእሑድ ጋዜጣ ነው፤ ቅዳሜ ምሽት ሁልጊዜም ቢዚ ነው። ጋዜጣውን ቅዳሜ ማታ ነው ማተሚያ ቤት የምናስገባው። ቅዳሜ ሁልጊዜ የሩጫ ቀን ነው።

በዚህ ሩጫ ውስጥ ሆነሽ የባሕርዳሩን ክስተት ለመጀመርያ ጊዜ ስንት ሰዓት ላይ ሰማሽ? ምንድነው የሰማሽው? ከማንስ ነው የሰማሽው?

በትክክል ሰዓቱን አላስታውስም። ግን ከ1፡30 እስከ 2፡00 ሰዓት ባለው ይመስለኛል። ቢሮ ነበርኩ፤ ያው ጋዜጣውን ጨርሰን ወደ ማተሚያ ቤት ለመላክ እየተሯሯጥን ነበር፤ ስለ ባሕርዳር የሰማንበት ሰዓት። ከአለቃዬ ተደውሎ ነው የተነገረኝ። ባህርዳር ላይ ችግር አለ እየተባለ ነው እስኪ አጣሪ ተባልኩ።

የብርጋዴር ጄነራል አሳምነው ጽጌ የቀብር ሥነ ሥርዓት ተፈፀመ

 

ከዚያስ?

ያው ክልሉ ላይ አንዳንድ ነገሮች ሲኖሩ የምናጣራው ወደ ክልሉ ኮሚኔኬሽን ኃላፊ አቶ አሰማኸኝ ጋ [በመደወል] ነው። አጋጣሚ እሱ ጋ ስንደውል እኔም ባልደረቦቼም፤ የሱ ስልክ አይሰራም ነበር። ፖሊስ ኮሚሽን፣ ጸረ ሙስና… ብቻ ሰው እናገኛለን ብለን የምናስባቸው ሁሉ ጋ ስንደውል ነበር።

የጄኔራሎቹና የአዴፓ አመራሮች ግድያ፡ ሙሉ እውነቱን ማን ይንገረን?

 

ከክልሉ ባለሥልጣናት መሀል በስም የሚታወቁ ሰዎች ጋ ደውለሻል።

አንድ ረዳት ኮሚሽነር ሰኢድ የሚባል ሰው አለ በክልሉ፤ እሱ ጋ፣ አቶ አሰማኸኝ ጋ ሌላ በስም የማላውቃቸው ጋ፣ [እንዲሁም ደግሞ] አማራ ክልል ያሉ ጋዜጠኞች እነዚህ ጋ ብትደውይ ያሉኝ ሰዎች [ዘንድ] አንድ አራቱ ጋ ደውያለሁ…

 

ሁሉም አያነሱም?

የአቶ አሰማኸኝ አይሠራም ነበር። የፖሊስ ኮሚሽን ያለው ልጅም አይሠራም። ሌሎቹ ግን ስልክ አያነሱም።

 

ዶ/ር አምባቸው ጋ ደውለሽ ነበር?

አልደወልኩም፤ የርሳቸው ኮንታክትም የለኝም።

 

ከዚያ ጄኔራል አሳምነው ጋ ደወልሽ?

አዎ መጨረሻ ላይ «ቆይ… ለምን የክልሉ ጸጥታ ክፍል ኃላፊ ጋ አልደውልም?» ብዬ ወደርሳቸው ጋ ደወልኩኝ። ከዚህ በፊትም ለአንድ ጉዳይ ደውዬላቸው ነበር። ስልካቸውም ነበረኝ።

 

ለምን ቆየሽ ግን? ከዚያ በፊት ትደዋወሉ ከነበረና በዚያ ላይ ጉዳዩ የጸጥታ ጉዳይ በመሆኑ በቀጥታ እሳቸውን የሚመለከት ሆኖ ሳለ ለምን እርሳቸው ጋ መጀመርያ አልደወልሽም?

እርግጠኛ አይደለሁም ለምን ቀድሜ እሳቸው ጋ እንዳላሰብኩኝ። መጀመርያ የመጣልኝ ኮሚኔኬሽን ቢሮው ኃላፊ ጋ ነበር። ከቆየሁ በኋላ ነው እርሳቸው ጋ መደወል የመጣልኝ። በመሀልም የከተማውን ነዋሪዎች ለማነጋገር እየሞከርን ነበር። «የት አካባቢ ነው ተኩስ ያለው? የተጎዱ ሰዎች አሉ ወይ?… እሱንም ለማጣራት እየሞከርን ነበር በመሀከል። መጨረሻ ላይ ግን እርሳቸው ጋ ነው የደወልኩት።

ብርጋዴር ጄኔራል አሳምነው ፅጌ መገደላቸው ተገለጸ

 

እርሳቸው ወዲያው አነሱት?

ወዲያው። [እንዲያውም] ሁለት ጊዜ ይመስለኛል የጠራው።

 

በዚያ ሰዓት ተጠርጣሪ እንደሆኑ ታውቂያለሽ?

ምንም የማውቀው ነገር የለም

 

ምን ተባባችሁ?

ደወልኩኝ አነሱ። እራሴን አስተዋወቅኩ። ከአዲስ አበባ እንደምደውልላቸው የምሠራበትን መሥሪያ ቤትና ለምን እንደደወልኩ አስረድቼ ክልሉ ላይ ያለውን ነገር ምን እንደሆነ አንዲያስረዱኝ ነበር የጠየቅኳቸው።

 

ምን አሉ?

ባህር ዳር ከተማ ላይ አንድ አንድ ግጭቶች እንዳሉ እና ጉዳቶችም እንደደረሱ ነገሩኝ። ‘ስፔሲፊክ’ እንዲሆኑልኝ ስለፈለኩኝ የጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ የፕሬስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊው አቶ ንጉሡ የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ነው ብለው መግለጫ ሰጥተዋል እና እርስዎ ግን ግጭት ነው ያሉኝ ስላቸው «መፈንቅለ መንግሥት ብሎ ነገር የለም። መፈንቅለ መንግሥት በየመንደሩ አይደረግም። መፈንቅለ መንግሥት ሊደረግ የሚችለው ማዕከላዊ መንግሥት ላይ ነው፤ እና ይህ ከእውነት የራቀ ነው። ምናልባት የምጠረጥረው የፌዴራል መንግሥት ወደ ክልሉ ለመግባት ፈልጎ የሰጠው ምክንያት ይሆናል ብዬ ነው የምገምተው» አሉኝ።

ከዚያ «መፈንቅለ መንግሥት ካልሆነ [ታዲያ] ምንድነው ‘ስፔሲፊካሊ’ ያለው ነገር ስላቸው «እሱን አሁን መናገር አንችልም፤ ምክንያቱም እኛ ምርመራ ላይ ያለነው፤ እያጣራን ነው። እሱን እንደጨረስን እናሳውቃችኋለን» አሉን።

“ብ/ጄነራል አሳምነው በባጃጅ ለማምለጥ ሲሞክሩ ነው የተገደሉት”

መቼ ነው የምታሳውቁን ስላቸው [ደግሞ] «ነገ ጠዋት በተወሰነ መልኩ ምርመራውን ስለምንጨርስ መግለጫ እንሰጣለን» አሉኝ ከዚያ ተሰነባብተን። ከዚያ በፊት ግን የመጨረሻ ጥያቄ ብዬ «ተኩስ አለ ይባላል፤ አሁንም ድረስ አልተረጋጋም ወይ?» ስላቸው «እኔም አልፎ አልፎ ተኩስ ይሰማኛል» አሉኝ።

«መከላከያ ገብቷል ስለሚባለውስ ነገር?» ስላቸው «እሱ ላይ ኮሜንት ማድረግ አልችልም፤ የማውቀው ነገር የለም አሉኝ፤ ከዚያ በኋላ ብዙም ጥያቄ ለመመለስ ፍላጎት አልነበራቸውም። የሚሉኝ የነበረው «ምርመራ ላይ ነን፤ እያጣራን ነው፤ አልጨረስንም፤ እሱን እንደጨረስን ነገ ጠዋት መግለጫ እንሰጣለን» የሚል ምላሽ ነበር የሰጡኝ።

 

ያወራሽው እርሳቸውን ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ?

ከርሳቸው ድምጽ ጋ ‘ፋሚሊያር’ ነኝ። [ድምጻቸው ለኔ አዲስ አይደለም]

 

ለምን እንደዛ አልሽ?

ከዚያ በፊት አውርቻቸው አውቃለሁ፤ እንደነገርኩህ። ክልሉ ላይ በነበሩ ጉዳዮች በጸጥታ ጉዳዮች አውርቻቸው አውቃለሁ’ኮ

 

አንቺ ግን ያውቁኛል ብለሽ ታስቢያለሽ?

ብዬ አስባለሁ። ምክንያቱ [ከዚህ ክስተት በፊት] የስልክ ልውውጦች ነበሩን። ‘ሜሴጄም’ አድርጌላቸው አውቃለሁ። ከዚያ በፊት በነበሩ ሁኔታዎች ማለቴ ነው። ምክንያቱም [ከዚህ ክስተት በፊት በነበሩ አጋጣሚዎች] ቴክስት ሳደርግላቸው ስብሰባ ላይ ነኝ እያሉ ይመልሱልኝ ስለነበር ስደውልላቸውም ራሴን አስተዋውቄ እንደዚህ ዓይነት ዜና እየሠራሁ ስለሆነ [ላናግርዎት ፈልጌ ነው] ብዬ ጽፌላቸው ስለማውቅና ስለመለሱልኝም ያውቁኛል ብዬ አስባለሁ፤ ላያውቁኝም ይችላሉ።እርግጠኛ አይደለሁም ግን።

 

አንቺ ግን አርሳቸው ስለመሆናቸው ይቺን ታህል ጥርጥ የለሽም ማለት ነው?

አዎ! አርግጠኛ ነኝ፤ ድምጻቸውን በደንብ አውቀዋለሁ። ስልካቸውም የርሳቸው ነው፤ የተሳሳተ ስልክ አይደለም።

 

ብዙ ጊዜ ድምፅ ስሜትን የመግለፅ ጉልበት አለው ብዬ አምናለሁ። እንው በደወልሽላቸው ሰዓት እሳቸው ላይ መረበሽ ተሰምቶሻል? ከጀርባ የሚሰማ የተኩስ ድምፅስ ነበር?

በጣም ፀጥ ያለ ቦታ። በቃ ድምፅም ጩኸትም ተኩስም የሌለበት ቦታ ነበር የነበሩት። ድምፃቸውም በጣም የተረጋጋ፤ሲያናግሩኝም ተረጋግተው ነበር።

 

ከሰማናቸው ነገሮች አንፃር መረጋጋታቸውና ፀጥታው የሚጠበቅ አይደለም። እንዴት እንደዚያ የተረጋጋ ድምፅ ሊኖራቸው የቻለ ይመስልሻል? ግምትሽ ምንድን ነው?

እርግጠኛ አደለሁም ግን የጦር ሰው ናቸው አደል። ብዙ ጊዜ የእንደዚህ ዓይነት ሰዎችን ስሜት ከድምፃቸው መረዳት የምንችል አይመስለኝም። የተባለው ነገር በእርግጥም ሆኖ ከነበረ መደናገጥና መረበሽ ያልሰማሁባቸው ወታደራዊ ሰው በመሆናቸው ነው ብዬ እገምታለሁ። ግን አሁንም እርግጠኛ መሆን አልችልም።

 

በደወልሽላቸው ሰዓት የክልሉ ፕሬዝዳንትን ጨምሮ ሌሎችም ሰዎች ተገድለዋል። እና ያንን ጉዳት አደረሰ የሚባል ሰው በዚያ መረጋጋት ማውራትና የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ ማብራራት፤ በማግሥቱም መግለጫ እንሰጣለን ሲሉ ከድምፃቸው ምንም ነገር መረዳት አለመቻል ለማመን አይከብድም? አንቺ ራስሽ አሁን ላይ ስታስቢው አይገርምሽም?

በርግጥ ግልፅ ቃለምልልስ ስለነበር ድምፃቸውን እቀርፅ ነበር። በሰዓቱ ከሰማሁት ነገር አንፃር እኔም ተረጋግቼ አልሰማኋቸው ይሆናል ብዬ በኋላም ደጋግሜ ሰምቼው ነበር፤ ድምፁን ግን አሁንም በጣም የተረጋጋ ድምፅ ነው ያላቸው።

 

ድምፃቸውን ቀድተሻል ብዬ አላሰብኩም ነበር። የስልክ ንግግራችሁ የስንት ደቂቃ ነበር?

ሶስት ደቂቃ ከ18 ሰከንድ መሰለኝ። አንዴ ቆየኝ እንዳላሳስትህ ቼክ ላድርገው።[ከአፍታ ቆይታ በኋላ] አዎ በትክክል ሦስት ደቂቃ ከ18 ሰከንድ ነው።

 

የደወልሽላቸው ስንት ሰዓት ነበር?

2፡29 ላይ ነበር።

 

በዚህች ደቂቃ ነው ያን ሁሉ ሐሳባቸውን የሰጡት?

አዎ!

 

ንግግራችሁን ለመቋጨት ይሞክሩ ነበረ? ጋዜጠኛ ስለሆንሽ ተጨማሪ ጥያቄዎችን እንደምታከታትይባቸው እገምታለሁ?

አዎ እንደዛ ነበረ። አንድ ሁለት ሦስት ጥያቄ መጀመሪያ ከመለሱ በኋላ ምርመራ እያደረግን ነው። እሱን ስንጨርስ ነው መናገር የምንችለው ነበር መልሳቸው። እኔ ግን በተደጋጋሚ ያለኝን ጥያቄ ሁሉ እጠይቃቸው ነበር። ምላሻቸው ያው እያጣራን ነው ነበር። ለምሳሌ ስሞች ጠቅሼ እነ እገሌ ጉዳት ደርሶባቸዋል እላቸው ነበር። ሌላ [ቅድም] ያልነገርኩህ ነገር የደረሰ ጉዳት? ስላቸው የክልሉ መስተዳደር አካባቢና የፓርቲ ጽ/ቤት ላይ ነው ጥቃት የደረሰው የሚል መልስ ሰጥተውኝ ነበር።

 

እሳቸው ግን በስም የጠቀሱልሽ ግለሰብ የለም?

እኛ ዜና ሰርተን ስለነበር እነ ዶ/ር አምባቸውን ስም ጠርቼ እነሱ ላይም ጉዳት ደርሷል ይባላል ስላቸው «ሊደርስም ላይደርስም ይችላል፤ እሱን እርግጠኛ ሆኜ መናገር አልችልም። እሱን የምናውቀው ምርመራችን ሲያልቅ ነው ነበር ያሉኝ።

 

ለምን እንደዛ ያሉሽ ይመስልሻል? ምትገምቻቸው ነገሮች አሉ?

ብዙ ነገር ሊሆን ይችላል ግን ይሄ ነው፣ ይሄ ነው ብሎ መገመትና መናገር ይከብደኛል። ነገሩ ገና በምርመራ ላይ ያለና ያልተቋጨ ነው። በምርመራ ሂደት ላይ ያለ ነገር ላይ [analysis and hypothesis ] መሥራት ከባድ ነው።

 

ሁልጊዜ የስልክ ንግግርሽን የመቀርጽ ልምድ አለሽ? ይሄን የምጠይቅሽ ከዚህ በፊትም የእሳቸው ተብሎ የወጣ ድምፅ ስላለ ነው። እሱ ቅንብር ነው፤የመንግሥት የስለላ መዋቅር ያሰናዳው ነው የሚሉ ነገሮች ተነስተውበታል። ምናልባት አንቺም በተመሳሳይ ልትጠረጠሪ የምትችይበት ዕድል ይኖራልና እንዴት ነው የምናምንሽ? በፊትም የመቅዳት ልምድ ነበረሽ ወይ? ስልክሽ ላይ የተጫነ ሶፍትዌር ነው ወይስ ስቱዲዮ ገብተሽ ነበር የደወልሽላቸው?

አይ ስልኬ ላይ [recorder]አለኝ። ለሥራ ቃለምልልስ በማደርግበት ጊዜ [on] አደርገዋለሁ። የግል ስልኮችን አልቀርጽም። ብዙ ጊዜ ለሥራ መደበኛ የቢሮ ስልኮችን ነው የምንጠቀመው። ግን የግል ስልኬን ስጠቀም እቀርፃለሁ። የዚያን ዕለት እንዲያውም የቢሮ ስልክ ነበር ልጠቀም የነበረው፤ ግን ሌሎችም ልጆችም ስለጉዳዩ እያጣሩ ስለነበር ነው ስልኬን የተጠቀምኩት።

 

ከድምፅ ጋር ተያይዞ በቅርቡ የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ሥራ አስኪያጅ ብርጋዲየር ጀነራል አሳምነው ጋር ያደረጉት ንግግር ወጥቷል። ያንን ድምፅ ጥያቄ ውስጥ የሚከቱት ሰዎች አሉ። አንቺ እሳቸውን በድምፅ እለያቸዋለሁ ስላልሽን ስለዚህ ድምጽ ምን ልትይን ትችያለሽ?

የሳቸው ድምፅ ሊሆን እንደሚችል እገምታለሁ። እንዳልኩህ ድምፃቸውን አውቃለሁ ሰምቼ፤ ደጋግሜ ስለሰማሁት እለየዋለሁ። እንዳልኩህ የሳቸው ድምፅ ይመስለኛል። “ኦዲዮው” ትክክል ነው፣ አይ ትክክል አይደለም፣ ተሰርቶ ነው በሚለው ላይ አስተያየት ባልሰጥ ደስ ይለኛል።…

 

ስትሰሚው ግን ላንቺ የተሰማሽ ስሜት ምንድን ነው? ጄኔራል አሳምነው ናቸው ነው ያልሽው? የመጀመሪያ ስሜትሽ ምንድን ነው?

ይቅርታ እዚህ ላይ በጭራሽ ምንም ኮሜንት ባላደርግ ደስ ይለኛል።

 

አወዛጋቢ ስለሆነ ነው?

አዎ ! የምልህ ጉዳዩ (ኬዙ) በደንብ ያልለየለት ነገር ነው፤ በዚህ ወቅት ምንም ብል የአንድን ሰው ሐሳብ እንደ መከራከሪያ ተደርጎ ፒክ ይደረጋል እና ቢቀር ነው የሚሻለኝ፤ እርግጠኛ ሆኜ ኮሜንት ማድረግ አልችልም።

 

እርሳቸውን ካናገርሻቸው በኋላ በምን ፍጥነት ነው ፌስቡክ ላይ ፖስት ያደረግሽው?

በጣም ቆይቻለሁ! ካናገርኳቸው “አይ ቲንክ” ሰላሳ አርባ ደቂቃ የቆየሁ ይመስለኛል። ምክንያቱም የጋዜጣውን ሥራ መጨረስ ስለነበረብን እሱን ጨርሰን ልክ ወደ ማተሚያ ቤት ከተላከ በኋለ ነው፤ ያንን ፖስት ያደረግኩት፤ አንድ ሰዓት ወይ እንደዚህ !

 

ፌስቡክ ላይ ስትለጥፊው ተጠርጣሪ እንደነበሩ ታውቂ ነበር?

በፍፁም አላውቅም፤ ከቢሮ ከወጣሁ በኋላ ፌስቡክ አካውንቴ ላይም ያንን ነገር «አብዴት» ካደረግኩ በኋላ አጋጣሚ ወደ መንገድ ነው የወጣሁት። ወደ አዳማ እየነዳሁ ነበር። በመሀሉ ብዙ ስልኮች ይደወሉ ነበር። የምሄድበት ቦታ ስደርስ ሌሊት ነው። ኢንተርኔት ተቋርጦም ስለነበር ምንም የሰማሁት ነገር የለም። በማግስቱ ጥዋት ነው አማራ ቴሌቪዥን ላይ እሳቸው ተጠርጣሪ ናቸው መባሉን የሰሙ ልጆች ደውለው የነገሩኝ። አጋጣሚ ያለሁበት ቦታ መብራት አልነበረምና ተጠርጣሪ ናቸው ወይም አሉበት ብሎ መንግሥት እንደሚጠረጥራቸው የሰማሁት ከሰው ነው።

 

ከክስተቱ በኋላ በጣም ብዙ ጥያቄዎች ይነሱ ነበር። ብዙ ግልፅ ያልሆኑ ነገሮች ነበሩ። ምናልባትም ብቸኛው መረጃ ከገለልተኛ ወገን በሳቸው ጉዳይ ላይ የፃፍሽው አንቺ ነሽ። ይሄ ጽሑፍ ይወትሽ ላይ ብዙ ተፅእኖ እንደፈጠረ እገምታለሁ። ከዛ ባሻገር ግን የደህንነት መዋቅሩ በዚህ ጉዳይ ላይ ሊያናግርሽ አልሞከረም ወይ? ምርመራ አልተደረገብሽም?

በፍፁም! ከዚያ በኋላ ማንም የትኛውም አካል ያናገረኝም የጠየቀኝም የለም። አንተም የምታውቀው ይመስለኛል ሶሻል ሚዲያ (ማህበራዊ ሚዲያ) ላይ ታፍና ተወስዳለች፤ ከዚያ ቀደም ብሎ ደግሞ ባልታወቁ ሰዎች ተገድላ ተጥላለች አይነት ዜናዎች ይሰሙ ነበር። ግን እንደሚባለው ምንም የደረሰብኝም ሆነ የጠየቀኝም፤ አፍኖ የወሰደኝ የለም።

 

ይህንን ቃለ ምልልስ እንድትሰጪና ምንም አልሆንኩም እንድትይ ማንም ግፊት አላደረገብሽም፤ ከመንግሥት?

ከዛ በፊት ከቀናቶችም በኋላ ምንም የደረሰብኝ ግፊት የለም። ማንም ጠርቶኝም፣ አናግሮኝምና ጠይቆኝም አያውቅም በዚህ ጉዳይ….

 

በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ሊያገኙሽና ስለዚህ ጉዳይ ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የሞከሩ ሰዎች የሉም በቀጥታ የፀጥታ አካላት ባይሆኑም….

የሉም! አንዳንድ የማቃቸው ሰዎች ፌስቡክ ‘አብዴት’ ያደረግኩትን ነገር ያዩ “እርግጠኛ ነሽ እሱን ነው ያናገርሽው? እሱ ስለመሆኑ ምን ያህል እርግጠኛ ነሽ” አይነት ጥያቄዎች ይጠይቁኛል። እነዚህ የማቃቸው ሰዎች ናቸው። ከዛ ውጭ የማላቃቸው ሰዎች በተዘዋዋሪ ጠይቀውኝ አያውቁም።

 

ለምን ዝምታን መረጥሽ? ባንች ጉዳይ ላይ ብዙ ሲባል ነበር። አንደኛ ከፌስቡክ ገፅሽ ላይ የፃፍሽውን አላወረድሽም፤ ሁለተኛ ከረጅም ጊዜ በኋላ ነው ዝምታሽን የሰበርሽው። ለምንድን ነው?

ኢንተርኔቱ ቅዳሜ ቀን ተቋረጠ። ስለዚህ ቅዳሜ፣ እሑድ፣ ሰኞ፣ ማክሰኞ እስከ ረቡዕ ድረስ ኢንተርኔት አልነበረም። አለሁ ብዬ ለመፃፍም የኢንተርኔት አገልግሎት [access] አልነበረኝም። ያንንም የሰማሁት ከአገር ውጪ ያሉ ሰዎች ሲደውሉልኝ ነበር። እንደዚህ ተብሎ ተፅፏል ብለው ነገሩኝ። አለሁ ለማለትም ኢንተርኔት ስላልነበር መመለስ አልቻልኩም።

ከዛ በኋላ ግን በቢሮ ስልክ ደውለው ያገኙኝ የሚዲያ ተቋማት [Media House] አሉ። ለምሳሌ አቤ ቶኪቻው ሳቅና ቁምነገር [ካልተሳሳትኩ] እሱ ደውሎ አናግሮኛል ‘አለሁ’ ብየዋለሁ። ዶይቼ ቬለ እንደዛው ደውለው አግኝተውኝ እንዳልታሰርኩ አረጋግጨላቸዋለሁ። ግን ኢንተርኔት እንዳገኘሁ እንዳለሁ ‘ስታተሴን አብዴት’ አድርጌያለሁ። አለመታሰሬን atleast የሚያሳውቅ ነገር።

ከማህበራዊ ሚዲያ ላይ ጽሑፉን ያላነሳሁት That’s …That’s fact ነው። Fact means እውነት ነው ሳይሆን፤ ቃለምልልስ አድርጌ ያገኘሁት ነገር ነው። ለእርሱ ደግሞ ማስረጃ አለኝ። የቀዳሁት [Record] ያደረኩት መረጃ አለኝ።

 

የተቀዳው ድምጽ እንዲወጣ ፍቃደኛ ነሽ? ለምሳሌ ከፈቀድሽ እኛም ልናወጣው እንችላለን ወይም በራሳችሁ ሚዲያ። እንደሱ ዓይነት ፍላጎት አለሽ?

አሁን ባይወጣ እመርጣለሁ። ምክንያቱም ያለቀለት፤ የተዘጋ ነገር አይደለም። ምርመራ ላይ ያለ ነገር ነው። ስለዚህ በዚያ መካከል ማውጣቱ ተገቢ ነው ብዬ አላስብም።

 

ከዚህ ክስተት በኋላ ሕይወት ላይ ወይም ቤተሰቡ የፈጠረው መረበሽ አለ?

ምንም ነገር። ማንም ጠይቆኝ ስለማያውቅ ምንም ነገር የለም። አንዳንድ የሚነግሩኝ ሰዎች አሉ። አደጋ [Risk] አለው እኮ… ለምን እንደዚህ አደረግሽ? እንደዚህ ቢሆን… እንደዚህ ቢከሰት … ዓይነት ነገሮች አሉ። ግን ከቤተሰብ በኩል የመጀመሪያ ሰሞን ይጨነቁ ነበር። ሰው እንደዛ ሲል ታስራለች … እንዲያውም ማክሰኞ ዕለት የነበረው ሞታ ተገኝታለች ሲባል ነበር። ግን ወዲያው ነው የቆመው እሱ ወሬ። ረቡዕ ዕለት ተመልሶ ታስራለች መባል ተጀመረ። የዚያን ጊዜ ይደነግጡ ነበር። የእውነትም ይመስላቸዋል። ደውለው እስከሚያጣሩና ድምፄን እስከሚሰሙ ድረስ የእውነት ይመስላቸው ነበር።

ምክንያቱም አሁን ነው የታሰረችው…ከሰዓታት በፊት ነው ዓይነት ነገር ይባላል እና ደጋግመው ይጠይቁኝ [Check] ያደርጉኝ ነበር ሥራ ቦታ ላይ ስለነበርኩኝ።

ከዚያ በኋላ ግን ከረቡዕ ዕለት በኋላ ነገሮች ሁሉ የተረጋጉ መሰለኝ። አልፎ አልፎ ነው አንዳንድ ሰዎች ‘ታስራለች’ የሚሉት እንጂ ግልፅ የሆነ መሰለኝ እንዳልታሰርኩኝ።

 

አንች ግን የሆነውን ሁሉ ተመልሰሽ ስታይው ምነው ያን ቀን ባልደወልኩ የሚል ስሜት ይፈጠርብሻል?

በፍፁም አይፈጠረብኝም፤ በፍፁም አልተፈጠረብኝም፤ አይፈጠርብኝም። ሥራ ላይ ነበርኩ ሥራዬን እየሰራሁ በነበረበት ሰዓት ነው አጋጣሚ የደወልኩት እና ምንም የተለየ ነገር እንዳደረኩም አይሰማኝም።

 

የመንግሥት የፀጥታ አካላት እስካሁን አንች ጋ አለመምጣታቸው ወይም ቃል ለመቀበልም አለመሞከራቸው ግን ይገርምሻል?

እ… No! አይ አይገርመኝም።

 

ለምን?

ጋዜጠኛ ነኝ። ጋዜጠኛ ነገሮችን ይጠይቃል፤ ያጣራል። ሶ እኔም ያደረኩት ያንን ነው። በዛ ሰዓት የደወልኩላቸው መረጃ ለመጠየቅ ነው። መረጃ ወስጃለሁ። መረጃ ያገኘሁትን ነገር አውጥቻለሁ ወይ ፅፌያለሁኝ። ያንን ማድረጌ ያስጠይቀኛል ብዬ አላስብም። ስጋትም አላደረብኝም።

 

ማሕበራዊ ሚዲያ ላይ ከእርሳቸው ጋር በተያያዘ የሚፃፉ ነገሮችን ትከታተያለሽ?

አልፎ አልፎ

ይህንን ነገር ለማጥራት እጅሽ ላይ ያለውን ድምፅ ለመልቀቅ ጊዜው አይደለም ብለሽ እንድታስቢ ያደረገሽ ምንድን ነው?

እ… አንደኛ ይህን ነገር ማጥራት የእኔ ኃላፊነት ነው ብዬ አላስብም። ይሄንን ኃላፊነት ያለው ክፍል አለ። በዛ ላይ አሁንም ደግሜ የምልህ ያለቀ ነገር አይመስለኝም። ምርመራ ላይ ያለ ነገር ነውና ምርመራ ላይ ያለ ነገር ላይ ጣልቃ ገብቶ እንደዚህ ነው እንደዛ ነው ማለት ትክክል አይመስለኝም፤ የሕግም ተጠያቂነት ያለበት ይመስለኛል።

 

/ “ብ/ጄኔራል አሳምነውን ቀድቻቸዋለሁ”: ቢቢሲ አማርኛ  

=====000=====


 

ተዛማጅ፡

እንደ ዋዛ የማይታለፈው የዶ/ር አምባቸው እና የጠ/ር አብይ ሙግት በዘመድኩን በቀለ ከነማስረጃው

 

 

 

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለፓርላማ ያቀረቡት የመጀመሪያው ግልፅና አስገራሚ ሪፖርት!

18 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ኮንትሮባንዲስቶች እነማን እንደሆኑ ለፓርላማው በግልጽ እንዲናገሩ የገቢዎችና ጉምሩክ ኃላፊዎች ተጠየቁ

31 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖተር
 

የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር — ኮንትሮባንዲስቶቹ የራሳቸው መጋዘን ያላቸው፣ በኔትወርክ የተደራጁና ተግባራቸውም በአሁኑ ወቅት አሳሳቢ የሚባል መሆኑን ጠቁመዋል!

‹‹በከፍተኛ የፖለቲካ አመራሩ ኮንትሮባንድን ለመዋጋት ቁርጠኝነት በመታየቱና ለይተን እንደናቀርብ በታዘዝነው መሠረት ቀንደኞቹን በጥናት ለይተን በአገር አቀፍ ደረጃ ለተቋቋመው ግብረ ኃይል አቅርበናል፤›› ያሉት አቶ ዘመድ፣ ‹‹እከሌ እከሌ ብሎ ማቅረብ ይቻላል ነገር ግን የሚወሰደውን ዕርምጃ በጋራ ብናይ ይሻላል፤›› ብለዋል፡፡

የአገሪቱን ኢኮኖሚ ከመጉዳት ባለፈ የፖለቲካ ቀውስ እየፈጠሩ ናቸው የሚባሉ ‹‹ኮንትሮባንዲስቶች›› ማንነት በግልጽ ለፓርላማው እንዲቀርብ፣ የፓርላማው አባላት ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ሳይሳካላቸው ቀርቷል፡፡
Continue reading

Ethiopia: Oromo, Amhara MPs boycott Parliament

21 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
(ESAT News) December 20, 2017: Oromo and Amhara MPs representing the Oromo People’s Democratic Organization (OPDO) and the Amhara National Democratic Movement (ANDM) have boycotted the Ethiopian Parliament saying the Prime Minister need to address the ongoing ethnic clashes and political crisis in the country.

The Parliament did not hold its regular session last Thursday and yesterday as the absence of the Oromo and Amhara MPs resulted in a below the quorum attendance. Ethiopian parliament requires 51% attendance to proceed with a regular session.
Continue reading

መሠረቱ የተናጋው የኢትዮጵያ 2015/2016 ፌዴራል በጀት (ክፍል 4)

18 Aug

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

በዚህ ርዕስ ሥር አቀርበዋለሁ ብዬ ቃል የገባሁትን ጽሁፍ – ማለትም ስለ ኢትዮጵያ የ2015/16 ፊዴራል በጀት (ክፍል አራት) – ላለማቅረብ በመወስኔ፣ ላቀርብ ያስብኩትን አምስት ገጽ+ ጽሁፍ በመጠኑም ቢሆን በተሻለ መንገድ ከዚህ በታች የተቀመጠው ግራፊክ ጠቅላላ ሃሣብ ያቀርባል ብዬ አምናለሁ።
Continue reading

$11.4ቢ በጀት እንደጸደቀ ተጨማሪ $1.2ቢ ጄኔራል ሣሞራ ለመሣሪያ ግዥ መጠየቃቸው ‘ሕዝቡን አስፈቅደው’ ኤርትራን ለመቅጣት ወይስ ዜጎችን? ለዛውም ጦሩ በ24 ዓመታት በጀቶቹ ምን እንደገነባ ሳይነግሩን ይህ ገንዝብ መነሻ ነው አሉ! (ክፍል 3)

24 Jul

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ክፍል ሶስት
 

መንደርደሪያ: የሥጋት ጊዜና በቅጽበት በውጥረት ወቅት ወደ ጦርነት በጀትነት የተለወጠው በጀት

የ’መንግሥት’ በጀት ላይ ይህንን ውይይት ስንጀምር (ክፍል 1) እና (ክፍል 2)፡ በሕወሃት ላይ እንዳሁኑ ዐይነት የጦርነት ከፍተኛ ሥጋት አላንዣበበም ነበር – ምንም እንኳ በዛ ያሉ መሣሪያ ያነገቡ ኃይሎች ሃገሪቱ ውስጥ መኖራቸው ቢታወቅም። ይህንን ውይይት ለመጀመር ምክንያት የሆኑኝ ሁለት ነበሩ። አንደኛው ከፍተኛ የሆነው የ$11.4 ቢሊዮን በጅት መዘጋጀቱና መጸደቁ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ ከብዛቱ አንጻር፡ ይህ ገንዘብ ለኢትዮጵያ ልማትና ዕድገት ከመዋሉ ይልቅ፡ እንደ ወትሮው ለሕወሃት ድርጅትች ሲሣይ መሆኑ፣ መመዝበሩ አሳስቦኝና አስቆጥቶኝ ነበር/ነውም።

አሁን ደግሞ፡ በሕወሃት የጦር ኃይሎችና የሕወሃት መመዝበሪያ የሆኑት የኤኮኖሚ ድርጅቶች ከግጭቱ ዒላማዎች መካከል መሆናቸው፣ እንዲሁም በእነዚህ ሁኔታዎች በጀቱ ወደ ጦርነት በጀት መለወጡ፡ የውይይታችንን ሂደት ቀያይሮታል። መረጃ ማግኘቱ አስቸጋሪ ቢሆንም፡ በተቻለ መጠን፡ በምናውቃቸውና በሚገኙት መለኪያነት በበጀቱ ላይ ውይይቱን እንቀጥላለን – ውይይቱ፥ የጦርነቱ ዓላማና በዚሁ የታሸው አየር አካል ናቸውና።

    አዲሱ የሲቪል በጀት ወደ ጦርነት በጀት መቀየሩና ኢትዮጵያን ከዘረኛ አገዛዝ ለማላቀቅ የሚነፍሰው የጦርነት አየር የዛሬይቷን ኢትዮጵያ ለሕወሃት የትናትናዋ የማድረጉ ሥጋት እያየለ ይመስላል!
    ሕወሃት በኢትዮጵያ የፈጠረው የሕግና መዋቅራዊ ምደረ በዳነት በሁሉም ረገድ ያስከተላቸው ጠንቆችን የሚቀለብስ ሁኔታ እንዲፈጠር ግፊቱ እየተጠናከረ ነው!
    አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት ካወጀበት ዕለት ጀምሮ የሃገራችን አንድ ቁጥር መወያያ ይኸው ብቻ ሆኖአል! ዶ/ር ብርሃኑ ነጋ አሥመራ መውረዱ ከተነገረ ጀምሮ በሕወሃት ዙሪያ ምጽዓት እየተጠበቀ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኖች ነገን በላቀ ተስፋ መጠበቅን “ሀ” ማለት ጀምረዋል!

Continue reading

የሕወሃት አስተዳደር የጠየቀው የ$11.4 ቢሊዮን የ2008 ፌዴራል በጀት ከሃገሪቱ አቅምና ገቢዋ አንጻር እጅግ ከፍተኛ ነው (ክፍል 2)

7 Jul

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ክፍል ሁለት

I. የ2008 በጀት ይዘት

የ2008 (2015/16) በጀትን በተመለከተ ቀደም ሲል በክፍል አንድ በቀረበው ጽሁፍ እንዳነሳሁት፣ በ’ፌዴራል መንግሥት’ በጀትነት ለ2008 ዓ.ም. ብር223.4 ቢሊዮን ($11.4 ቢሊዮን) በኢትዮጵያ ስም ተጠይቋል። ለአዲሱ በጀት ትርጉማዊነት፡ የሚጠበቀው የታክስ ገቢ ብር 141,208,500,000 ($6.8 ቢሊዮን) ሲሰበሰብ ሲሆን፣ ከ2007 ክንውን ግምት ጋር ሲነጻጸር 22.2 በመቶ ዕድገት ማሳየት አለበት ይላል ገንዘብ ሚኒስቴር፡፡
Continue reading

%d bloggers like this: