Tag Archives: Prime Minister Abiy Ahmed

የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር የተጀመረው ሂደት መቆሙን ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ!

13 Oct
የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር የተጀመረው ሂደት መቆሙን የገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገንዘብ ሚኒስትር አቶ አህመድ ሽዴ የ2013 ዓ.ም የመጀመሪያው ሩብ ዓመት አፈፃፀምን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በገቢ ደረጃ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 80 ነጥብ ቢሊየን ብር በላይ ገቢ ሲሰበሰብ፤ 97 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ወጪ ተደርጓል ብለዋል።

ይህም በወጪ ደረጃ የበጀት እጥረት እንደነበር ጠቅሰው፥ እጥረቱን ለመሸፈን ከብሄራዊ ባንክ ወጪ በማድረግ የዋጋ ግሽበት እንዳይጨምር በግምጃ ቤት ሰነድ አማካኝነት ከግል ባንኮች በመደበር እንዲሸፈን ተደርጓልም ነው ያሉት።

በብድር እና እርዳታ በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 474 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን ያነሱት ሚኒስትሩ፥ ከኮሮና ጋር በተያያዘ በሚደረግ ድጋፍ 131 ሚሊየን ዶላር ከጀርመን እና ከጃፓን መንግስት መገኘቱንም አስታውቀዋል።

ከዋጋ ግሽበት ጋር በተያያዘ ካለፈው ወር ጋር ሲነፃፀር መጠነኛ ቅናሽ ማሳየቱንም ሚኒስትሩ በመግለጫቸው አንስተዋል።

ከፕራይቬታይዜሽን ጋር በተያያዘ በቴሌኮም ዘርፍ ከዚህ ቀደም ፍቃድ ይሰጣል ከተባለው ሁለት የቴሌኮም ኩባንያዎች በተጨማሪ ከመንግስት ጋር በጋራ የሚሰራ ለአንድ ተጨማሪ የቴሌኮም ኩባንያም ፍቃድ እንደሚሰጥም አውስተዋል።

ይህም በአጠቃላይ በያዝነው ዓመት ፍቃድ ይሰጣቸዋል የተባሉትን የቴሌኮም ኩባንያዎች ቁጥር ወደ 3 ከፍ እንደሚያደርገው እና ይህንን ለማስኬድም የፕራይቬታይዜሽን ስራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ገልፀዋል።

የፕራይቬታይዜሽን አካል የሆነውን የሎጂስቲክስ ዘርፍ ግን ኢትዮጵያ የባህር ወደብ የሌላት በመሆኑ የሎጂስቲክ አገልግሎት እንዲሳለጥ ከማድረግ አንፃር ለግል ድርጅቶች ይሰጣል ነው ያሉት።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር በተያያዘ የኢትዮጵያ አየር መንገድን በከፊል ወደ ግል ለማዘዋወር የተጀመረው ሂደት መቋረጡንም ጠቁመዋል።

ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ስምና ዝና እንዲሁም ትርፋማ ከሆኑ ድርጅቶች አንዱ በመሆኑም መንግስት ይህን በመገንዘብ ፕራይቬታይዝ የማድረጉን ሂደት ማቋረጡን አስረድተዋል።

ከስኳር ፋብሪካ ፕሮጀክቶች ጋር በተያያዘ ፕሮጀክቶቹን ወደ ግል ለማዛወር የተለያዩ የውጭ ኩባንያዎች እንዲገቡ እየተሰራ መሆኑንም ነው በመግለጫቸው ያነሱት።

ለመንግስት የስራ ሀላፊዎች ሲ ኤም ሲ አካባቢ የተገነቡ መኖሪያ ቤቶችን በጨረታ በመሸጥ እስከ 1 ቢሊየን ብር ለማግኘት መታቀዱንም ነው ሚኒስትሩ የገለፁት።

ይህም ህንፃዎች በተገነቡበት አካባቢ የሪል ስቴት መንደር በመሆኑ እና ከደህንነት አንፃርም ጥያቄ የሚያስነሳ ስለሆነ ቤቶቹን ለመሸጥ ጨረታ ወጥቷል ብለዋል ሚኒስትሩ።

ከትግራይ ክልል ጋር በተያያዘ የፌዴሬሽን ምክር ቤት በክልሉ የሚገኙ የካቢኔ አባላት ህጋዊ ባልሆነ ምርጫ ተመርጠናል በሚል የሀገሪቱን ህገ መንግስት በመጣሳቸው አሁን ባለው ሁኔታ የገንዘብ ሚኒስቴር ለትግራይ ክልል መንግስት በጀት እንደማይለቅም ነው የተናገሩት።

በትግራይ ክልል ለሚገኙ የአገልግሎት ሰጪ ተቋማት በወረዳዎች እና ከተማ አስተዳደሮች በኩል በተጠና ሁኔታ እንዲደርሳቸው ጥረት እየተደረገ እንደሚገኝም ጠቅሰዋል።

ከአንበጣ መንጋ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ በሀገሪቱ ኢኮኖሚ ላይ ያደረሰው ጉዳት ምን ያክል ነው የሚለው ወደ ፊት የሚጠና ሆኖ፤ አሁን ላይ ከዓለም ባንክ በተገኘ 60 ሚሊየን ዶላር ከግብርና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተለያዩ የመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ወረርሽኑ በኢትዮጵያ አቅም ብቻ የሚጠፋ ባለመሆኑ ከኢዳግ እና ከምስራቅ አፍሪካ የአንበጣ መከላከል ባለስልጣን ጋር በቅንጅት ለመስራት ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

/በፀጋዬ ንጉስ

ቴድሮስ ፀጋዬ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአዲስ ወግ መዝጊያ ላሰሙት ንግግር የሠጠው ምላሽ!

25 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

 

በአድዋ ድል መለኪያነት ዜጎች ምን እንዳተረፉ በመጠየቅ፣ በሃገር ደረጃ ተጠያቂነትን ማጠናከር ይችላሉ!

2 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በከፍያለው ገብረመድኅን

አምስት ዓመት ሊሆነው መሰለኝ፣ Nicholas Clairmont ሐምሌ 31, 2013: “History shows that both those who do not learn history and those who do learn history are doomed to repeat it” ሲል መጻፉ ትውስ አለኝ። ፀሐፊው ይህንን ሃሣብ ሲያብራራ፦

“The quote is most likely due to writer and philosopher George Santayana [Jorge Agustín Nicolás Ruiz de Santayana y Borrás], and in its original form it read, “Those who cannot remember the past are condemned to repeat it… According to Santayana’s philosophy, history repeats. The phrasing itself certainly is catchy. It’s a big one, not only because it is so common, but also because if it is true and if history, driven by human nature, is ugly (hint: it is), then this saying ought to guide our public and private policy.”

በዚሁ መነጽር፡ እስቲ የኢትዮጵያን ተስፋ ከቲም ለማ መምጣት በኋላ አስታውሱትና የተሰማንን ፍንደቃ ለጥቂት ደቂቃ በአዕምሮአችሁ አንገዋሉት! ከዚያም ከሰሞኑ እየታየ ያለው ቲም ለማ—አያደርገውም የሚባልለትን ስላደረገ—ማለትም የዜጎች መፈናቀልሃገሪቷ የመጭው ዘመን ተስፋ ብላ የተቀበለችው መደመር ላይ ጥርጥር ሳይፈጥር የቀረ ይመስልም።

ከተገረሰሰው የመለሰ ዜናዊና ፍሬዎቹ ሥርዓት አረመኔነት ባልተናነሰበተለይም በሕግ መከበር ሽፋን፥  የለጋጣፎ ነዋሪዎች በሰባት ቀን ከቤቶቻ ካልወጡ ቤቶቻቸውን  ያፈረሰበትን እንደሚያስከፍላቸው በማስፈራት የዜጎችን ቤቶች በቀን በጨለማም ሲያፈራርስ ሰነበተ። 

ሁኔታው ጥድፊያው ምንድነው የሚል ጥያቄን ቢጋብዝ አያስገርምም። የዛሬዎቹ መሪዎች ለሃገሪቱ በጎ አመለካከት ቢኖራቸውም፣ በሥራቸውና ባሕሪዎቻቸው (instinct & modus operandi)፣ ምናልባትም  George Santayana እንዳለው፣ ታሪክን ያነበቡትም ያላነበቡት ሁለቱም  በቀላሉ መርሳታቸውን አሳይቶናል!

ይባስ ተብሎም፡ የካቲት 26/2019 አቶ ለማ መገርሣ በጨፌ ኦሮሚያ ማዕከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ— በአንድ በኩል ለመሬት ወረራው “ጥፋቱ የአስተዳደሩ ነው” ሲሉ፣ በሌላ በኩል ደግሞ ሕዝቡ ያለወንጀሉ የሚቀጣበትን ካሣ የሌለው የመኖሪያ ቤቶችን ድርመሳ—”እየተወሰደ ያለው እርምጃ በየትኛውም አካል ጫና እንደማይቆመም” መናገራቸው፣ አባባላቸውን መንግሥት ለሕዝቡ የሕግ ሃላፊነትና ዜግነታዊ ግዴታ እንዳለበት የዘነጋ አስመስሎታል።

እነዚህ መሪዎች ለኢትዮጵያውያን በተደጋጋሚ ከገቡት ቃል አንጻር፥ በተለይ ለጋጣፎ (እንዲሁም ሌሎቹ)  የተፈጸሙትን አውግዘን የፃፍነውን ጭምር “እንዴት ሊሆን ቻለ?” ለሚለው ከግምት ውጭ  መልስ ስሌለን፣ መደበቂያ ያሣጣ ሆኗል!

ለምን?

አንደኛ፣ አዲስ መሪዎች እንጂ አዲስ ሥርዓት የለምና፥ የምንነጋገረው ከሕወሃት ፍንገላ በኋላ ስለመጡት የኦሮሞ ዴሞክራቲክ ፓርቲ (ኦዲፓ) አመራርና አጋሮቹ ነው። ይኸውም  በመንግሥትነት ዓመት ሳይሞላቸው፣ ለዜጎች ተለዋጭ መኖሪያ እንኳ ሳያዘጋጁ: ያላንዳች ካሣ (without compensation)-— ልክ ሕወሃት ያደርግ እንደነበረውበድንገት አንዳንዴም ጨለማን ተገን በማድረግ ቤቶቻችውን በማፈራረስ  የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ሲያካሄዱ ከረሙ!

የሃገሪቱ ሕግና ብሔራዊ ኅሊናችንም ይህን አለመደገፋቸው ብቻ አሣይሆን፡ ሃገሪቷ ዓለም አቀፍ ግዴታ እንዳለባት እንዴት አልተገነዘቡም? ለሕወሃት ዋሾነት እንዳልበጀው በማስታወስ፡ አዲሱስ መንግሥት ለዜጎች ዋሽቶ፣ ለባዕዳን ወዳጆችስ ዋሽቶ ይዘልቀዋልን?

ሁለተኛ፣ ለሕዝቡ ማስረዳት የማይችሉና፡ የተምታታ ክህደት የሚረጩ ሹሞች ከመላክ ውጭ፣ እርምጃ መውሰድ የሚችል ባለሥልጣን ተፈናቃዮቹን አልጎበኛቸውም“መብታችን ነው! ውሃና መብራት አስገብታችሁልን፤ ግብር ስንከፍል ተቀብላችሁ፣ አሁን ሕገወጥ ስትሉን ተቀባይነት የለውም” ላሏቸውም፣ በአፍራሽ ሠራተኞች በኩል ከሕገ ወጥ ስድብ ውጭ ሌላ መልስ አልበረም!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶር ዐብይም የክተማዋ አስተዳዳሪ አለመሆናቸውን አስረግጠው፡ ስለ ለጋጣፎ ፕላንና ቤቶች ምንጠራ ምንም እንደማያውቁ ተናግረው እጃቸውን ማጠባቸውን በቴለቪዥን ተመልክተናል።ይህንን ሲናገሩም ሕዝቡ ወደእኔ መመልከቱ ግን ትክክል ነው ማለታቸው —ለጊዜው ማፈራረሱን አስቁሟል!

ሶስተኛ፣ ቤቶቹን ለማፈራረስ አጣዳፊ ሁኔታ እንኳ አለ ቢባል፡ በትንሹ ከእሥር ዓመት በላይ ተደልለውም ይሁን በፖለቲካ ኃይሎች ተገፍተው ገበሬዎች የለቀቁት መሬት ላይ ‘ገዥዎቹ’ ለገነቧቸው ቤቶች መንግሥት አገልግሎት እየሠጠና ግብር እየተቀበለ ያቆያቸው ሆነው ሳለ፣ በድንገት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ “የአዲስ አበባ አረንጓዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ዕይታና ሃብቷን ለማሳደግ” የታሰበውን ፕሮጄክት ሃሣብ ተግባራዊ  እንደሚሆን ተሰማ! የፈረሱት ቤቶች በዚህ ፕላን መሠረት ለአረንጓዴ ልማት በማስተር ፕላኑ ተካቷል በሚሉ የማዘጋጃ ቤት ሰዎች፣ አዲስ አበባ ዙርያ ቤቶች ማፈራረሱ እንደተንቀሳቀስ ተሰማ። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዓላማ፣ ማለትም “የአዲስ አበባ አረንጓዴ ልማት፣ የተፈጥሮ ዕይታና ሃብቷን የማሳደግ” ግቡ ጠቀሜታ ግልጽ ነው!

እነዚህ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው እንዴት ነው በዚህ ፕሮጄክት ሊጽናኑ የሚችሉት— ድምፅ የላቸውም ካልተባለ በስተቀር?

የፕሮጄክቱ ሃሣብ አፍላቂ የሃገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ናቸውና ለዚህ ነው ይህ አሠራር የፖለቲካ ሥልጣኑ ግፊት የተጸነሰ ነው ያስኘው! እነዚህ ቤቶቻቸው የፈረሱባቸው ግለሰቦች ኢትዮጵያውያን ናቸውና እንዴት ይመልከቱት ለሚለው ምላሽ ያስፈልጋል?አርብ ጥዋት በቲውተር ዜጎች የጻፉትን ሳነብ፡ ይህንን የአንድ ኦሮሞዘካርያስ ኃይሉን —መልዕክት አገኘሁ!  ስለ ወደድኩት፣ ከአንብባያን ጋር ልካፈለው ወሰንኩ:-


ዘካርያስ ያለውን ታሪከ አልቀበለውም ያለ ዜጋ: ወይንም ከሌሎች ጋር በጋራ አስተሳሰብ የሚንቀሳቀስ ግለሰብ ሊሆን ይችላል።

ዕድሜ ለመደመር! ኢትዮጵያውያንን ላጎናጸፈን ነፃነት! ይህንን ነፃነት እያንዳንዳችንን ስማችንን ጠርቶ፡ ወይንም በዘር ቆጥሮ ፡ ሲልም በጾታ ለይቶ አይደለም ያከፋፈለን! ለዚህ ነው የዘካርያስን ቲውተር መልዕክት የወደድኩት! አውጥቶ አውርዶ —በታሪካዊ ግኝቶች ላይ ተመሥርቶ ይሁን በቅብብሎሽ በተከሰተ የጥቂቶች ጥፋት/ቶች— ምናልባት ስለሚኒልክ ሆነ ስለአድዋ ጭራሽ መስማት አይፈልግም ነበር ይሆናል (“As an Oromo I can’t like & admire Menilik & all his generals…”። አስቦበትና አውጥቶ አውርዶ ግን “.. As an African I can’t help admiring and celebrating him [Menilik] for defeating European colonialists. Things are more nuanced than they appear. is a great African & Ethiopian Day” ከዚህ በላይ ምን ውበት አለ?

መብቱ ነው!ይህንን የጻፈውን አቶ ዘካርያስን አላውቀውም! የፃፈው ግን መብቱ መሆኑን የተገነዘበና ታሪክን በታሪክ ዋጋነቱ የሚያይ እንጂ በተጠቃሚ አፍራሽ ፕሮፓጋንዲስቶች የማይመራ ዜጋ ነው የሚል እምነት አሳድሮብኛል። በአንፃሩ አሁንም ከኦዲፓ ጋር ሹም ሆነው ሲሠሩ ቆይተው በቅርቡ ሹመት እየጠበቁ ያሉት ዛሬበትዊተር የለቀቁትን ለተገነዘበ ውጫችን ጸድቶ በቆሸሸ ውሥጣችን፡ ለማወቅ ያልቻሉትን ማወናበዱ ይቁም!

የአድዋን ታላቅ የዓለም ሕዝብ ከፍ ያደረገውን ታሪክ በማቆሸሸ ‘ለመጠቀም’ ከመሻት ይልቅ፡ የታሪከ መረጃ ያለው አውጥቶ ያስተምርና ሕዝቡ ይገምግመው! ይህንንም ማድረግ የሚሻ ዜጋ መብቱ ነው! መደመርም ይህን መገደብ ካሻ ስህተት ነው!

መንግሥት ይህንን ታላቅ ታሪክ ሕዝቡ እንዲያውቅ ከፈለገ ፕሮግራም ያዘጋጅና ያስተምር፡ ያከራክር! የሰው ልጅ ግን ያመነበት ዕውቀቱ ጋር የመኖር መብቱን ያክብር!

በፖለቲካችን ምክንያት፣ ልዩነቶችን ለማሸነፍ ብቻ ከተሠማራን ጤነኛ ሕዝብና ሃገር አንሆንም። ልዩነቶቻችንን አቻችለን ለመሥራት አስካልቻልን፣ ተገንዝበናቸውለመግባባት እስከበቃን ድረስ ትልቅ ተስፋ ይኖረናል። ሽፋፍነን በምክንያት የጠፉ ማስመሰሉ የሃገራችንን ችግሮች ያባብሳል። እንደኅብረተሰብ አሸናፊነትን የምንቀዳጀው ልዩነቶቻችን ተቀብለን: ተቻችለን አብረን መሥራት ከቻልን ነው። 

*******

 

123ኛው የአድዋ ድል በዓል በሚከበርበት በአሁኑ ወቅት— የዐቢይም አስተዳደር አንደኛ ዓመቱ ዋዜማ ላይ እንደመሆኑ—ይህንን ወቅት ማሰታወስ የሚገባን በአጼ ሚኒልክ አመራር የኢትዮጵያ ሕዝብ ወራሪን ኢምፔርያሊስት ኃይል በጦር ሚዳ ድል ማድረጉን ብቻ አይደለም። ዳግማዊ ሚኒልክ የዚህ ጽሁፍ እምብርት ለሆነው የጊዜው በየአደባባያቸው ፍርድ ቤቶች (territorial courts) ምሥረታቸውና አሠራር ማድረጋቸውን ለማሳየት ይሞክራል ።

እጅግ ያስደነቀኝ፡ ንጉሠ ነገሥቱ እስከ ዛሬ በብዙ ሃገሮች ተግባራዊ የሚሆንውን የጅራፍ ግርፋት እንዲቀር፣ በዳኝነት ከመሬት ማፈናቀል እንዲቆም፡ እንዲሁም ቅጣትና ውርርድ  በደምብ የፍርድ ቤት አሠራር እንዳይሆን ማወጃቸው፣ በጊዜያቸው ትልቅ ዕይታ የነበራቸው መሪ (visionary leader) ነበሩ ማለት፣ የነተስፋዬ ገብረአብ “የቡርቃ…” ምናምን አይደለም!

ስለ አፄ ሚኒልክ ብዙ አከራካሪ ጉዳዮች ይሰማሉ! ምናልባትም መደመር የኢትዮጵያን ደህንነትና ጤንነት ለማረጋገጥ፡ መረጃ ላይ የተመሠረተ ታሪክ፥ የውይይት ዕድል ይከፍት ይሆናል ብዬ አምናለሁ!

ከላይ ያልኩትን የማሠምርበትን ምክንያት በአንድ ‘በቅርብ ልበለው’ በቴሌቪዥን በሁለት ወቅቶች ከተከታተልኳቸው ውይይቶች በመነሳት እንደሚከተለው ልግለጽ። የኦሮሞ ነጻ አውጭ ግንባር (ኦነግ) ለትውልድ ባስተላለፈው አፍራሽነት ምክንያት አያሌ የሃገራችንን ወጣቶች ክፉኛ በመረዘባት ኢትዮጵያ —አቶ ለንጮ ባቲ ያኔ የኦነግ አባል አሁን የኦሮሞ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲው (ኦዲፓ)፣ በSchool of Deconstructionism ምልከታን በመጠቀም፣ እርሳቸው በቅርብ እንዳስቀመጡት— በኦሮሞች መቃብር ላይ መቆም የፈለገችውን የቀድሞዋ ኢትዮጵያ የገነባችውን ገጽታ እያፈረስን (“Deconstructing Ethiopia” — የእርሳቸው አባባል) የኦሮሞን ስብዕና ሰንገነባ (Building Oromo personality) እዚህ ደርሰናል ማለታቸው ይታወሰኛል።

እርሳቸው እንዳስቀመጡት አሁን፣ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ለውጥ ባሳደረባቸው እምነት ምክንያት —በግልጽ እንደሚደመጠው— ዛሬ ኦሮሞች የሚቀበሏትን ሁሉን የምታቅፈውን ኢትዮጵያን ለመገንባት ሥራ መጀመራቸውን አሰምተውናል። 

ይህ አመለካከት ለኦነጋዊ ግለሰብ እንኳን ከዓመት ከወራትም በፊት የሚታሰብ አልነበረም። እርሳቸው ግን ይህንን የተናተገሩት ሃገር ሳይገቡ፣ ለውጡ ሳይጀመር በመሆኑ፡ ከቀድሞ ጀምሮ ምነው ኦሮሞች ኢትዮጵያዊነታቸውን የራሳቸው አድርገው እንደርሳቸው ዕድሳትና ግንባታውን ከሌሎች ጋር ሆነው ሁላችንም ወደፊት አብረን በተራመድን ለሚለው ርሃብና ጥማት ተጨማሪ ምክንያት ሆነውልኝ ነው ይህንን አርቲክል ለመጻፍ ቁጭ ያልሁት!

ዛሬ ከሙያ፡ ዕውቀትና መልካም ስብዕና መረጋጋትና በዘር ዝርያ መሳሳብ መሆኑን ዜጎች ያዩታል።  ያውቁታል። ግን ማናቸውም አይወዱትም! ለዚህ ነው ሁል ጊዜም ሽፍንፍን ነገር የሆነው! ከዚህ የበለጠ ለኢትዮጵያ ድኅንነት፡ የሕዝቦቿ መተሣሠር ምንም የወደፊት የዜጎቿን ሕይወት ብልጽግና የበለጠ ሊያረጋግጥ የሚችለው ይህን የዘካርያስን ሕልምና ግልጽነት መላበስ ብቻ ነው!

 

የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ ፍርድ ክልሎችን ስለመመሥረት፤ ዳኝነትና አዳዲስ ሕጎችን ተግባራዊ ስለማድረግ

የሃገር ዳር ድንበር በሚገባ ከተለየ በኋላ፡ ሃገርን መጠበቅና ዳር ድንበርን ማስከበር ለሚኒልክ ቀደምት ተግባር በመሆኑ፡ በውስጥም የጊዜው ዕወቀትና የመንግሥታቸው አቅም በፈቀደ መጠን ሕግና ሥርዓት እንዲከበር አጼ ምኒልክ ብርቱ ጥረት ያደርጉ ነበር። መለካት ያለባቸው በጊዜያቸው ፖለቲካና ዕይታ ብቻ ነው!

በአሥራ ስምንተኛው መቶ መባቻ ላይ የኢትዮጵያ ሕዝብ ቁጥር በጣም በመጨመሩ፡ ንትርኮች፡ ጎጂ ጠቦች በዜጎች መካከል በመበራከታቸው፡ የሃይ ባይ አስፈላጊነትን ለንጉሡ በሚገባ ግልፅ ነበር፣ ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ —የዳግማዊ አፄ ሚኒልክ የመጀመሪያ ጽሕፈት ሚኒስትር —በዘመነ ሚኒልክ ዘገባቸው አንዳስነበቡን።

በዚህም የአፄ ሚኒልክ ትልቁ ትኩረት ያረፈው የሃገሪቱን አስተዳደር ክልሎች ከፋፍለው (territorial judiciary/ territorial courts በአሜሪካ) የፍርድ: ዳኝነትና የፍትህ አገልግሎት —ከሩቅ መጓዝን ባያስቀርም—በእርሳቸው አደባባይ (Emperor’s Court) ፍርድ ማግኘት የሚቻልበትን አመቻቸ።

ለዚህም ዓላማ ተግባራዊነት—በእርሳቸው አደባባይ (Emperor’s Court) የሚተገበሩ ሆንው፥ በኢትዮጵያ አቆጣጠር በ1900 ዓ.ም. ኢትዮጵያን በስድስት የዳኝነት ክፍሎች ከፋፈሏት::

 

*******

ስድስቱ የዳኝነትና ፍርድ አስተዳደሮች የሚከተሉትን አካባቢዎች ያካተቱ ነበሩ፦

አንደኛ ቤጌምድር —የጁን ይዞ ከጨጨሆ በላይ ያለውን ሃገር፡ አማራ ሳይንትና ቦረና፡ ወሎና ወረሂመኖ አምባሰል፡ ቃሉና ተሁለደሬ፡ ወርጣዬና፡ ወረባቡ፡ ገርፋና፡ አውሳ፡ እርቄ፡ ከሸዋም ሸንኮራን፡ ከጫጫ በታች ያጼ፡ ገመድ፡ የወደቀብትን ሃገር፡ ከጋላም አሩሲን፡ ጉማን ጨምሮ፤

ሁለተኛ፡ የእቴጌ ግዛት በምሉ ከጋላ አገር ኖኖ፣ ቶኬ፣ ትቤ ናቸው።

ሶስተኛ፡ ትግሬ፡ ዋግ፡ ከሸዋ መንዝና ከሞፈር ውሃ ወዲያ ከወሎ በመለስ ያለውን አገር፣ ደራና መራቤቴ፣ ከጋላም አገር ጎፋ፣ ባኮ፤

አራተኛ ተጉለትና ሰላድንጋይ፡ ዋግና ዋዩ፡ ጅሩና ጣጤሳ፡ ላሙሻና ሞረት፡ እንሳሮ፡ ጎጃም፡ ዳሞትና አገው ምድር፡ ቋራ፡ አቸፈርና ወንድጌ፡ ሜጫ፡ ጉድሩና ሆሮ፡ አሞሩና ጅዳ፡ ወለጋና ሌቃ፡ ኢሉባቦርና ተገባ ወዲያ ያለ አገር፡ ከፋ፡ ሊሙና ቦተሮ፡ ኮንታና ኩሎ፤

አምስተኛ፡ አንኮበር፡ሐራምባ፡ ዪፋት፡ ወረገኑ፡ባሶ፡ ደጋ፡ ጠራ፡ አሣግርት፡ቅምብቢት፡ ምንጃር፡ ሐራርጌ፡ ባሌ፡ ሲዳሞ፡ ከምባታና ሲሞ፤

ስድስተኛ፡ አመያን ወሊሲ፡ ጨቦና አገምጃ፡ ሶዶና ማረቆ፡ ገሙና ቦረና፡ወላሞ፡ ጅማ፡ ያባ፡ ጅፋር፡ ዳንጀሮ፡ ጌራና፡ ጉማ፡ ወለጋና ዓረብ፡ የደጃችህ ጆቴ አገር፤[ገጽ 338-339]

 

በዚህ ወቅት ነበር—የንጉሡ የመጀመሪያው የጽሕፈት ሚኒስትር (Minister of Pen) ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ በታሪክ ዘመን ዘዳግማዊ ሚኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ  እንደዘገቡት (ሕትመት እ. ኢት.አ. 1959 ዓ.ም) —

“በኢትዮጵያ የአውሮፓን ሥራት (ሥርዓት) ለማግባት አስበው በ1900 ዓ.ም. እንዳውሮፓ አገር ሚኒስትሮች ሾሙ፤ የሚኒስትሮችም ስም ይህ ነው።

የፍርድ ሚኒስትር አፈንጉሥ ነሲቡ

የጦር ሚኒስተር ፊታውራሪ ሃብተጊዮርጊስ

ያገር ግዛት ሚኒስትር ሊቀመኳስ ከተማ

የንግድና የውጭ ጉዳይ ሚኒሰትር ነጋድራስ ኃይለጊዮርጊስ

የገንዘብ ሚኒስትር በጅሮንድ ሙሉጌታ

የጽሕፈት ሚኒስትር ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ

የሥራ ሚኒስትር ቀኛዝማች መኮንን

የግቢ ሚኒስትር አዛዥ መታፈሪያ

እነዚህ ቤት ተሠርቶላቸው የሚኒስትርነት ሥራ ያዙ።” [ገጽ 334]።

 

ከላይ የተጠቀሱት የመጀመሪያዎቹ የኢትዮጵያ መንግሥት የካቢኔ አባላት ሲሆኑ፣ አጼ ሚኒልክም — ፀሐፊ ትዕዛዝ እንዳመለከቱት — ፍርድ የሚሠጥበትን ሕግ አስመልክቶ ለሚኒስትሮቻቸው በቃል የሠጡት የመጀመሪያ መመሪያዎች የሚከተሉት ነበሩ፦

ሰው በተጣላ ጊዜ ከባላጋራው ጋራ ተቋቁሞ ሲነጋገር አልፍ ጅራፍ እሰጥ እያለ ውርርድ የሚተክለው ሁሉ ይቅር።

ውርርደም ማር ይሁን፣ እጅግም ቢበዛ ፈረስ እሰጥ በቅሎ እሰጥ ይበል እንጂ በላይ ውርርድ አይትከል።

ዳኛም ከዚህ በላይ ውርርድ አስተክሎ አያሟግት። የውርርዱም ዕዳ በበቅሎ የተረታ 20 ብር በፈረስ የተረታ 10 ብር በማር የተረታ 4ሩብ ይክፈል። ዳኝነትም 8 ሩብ ይሁን።[ገጽ 334]።

 

በተጨማሪ፡ ሕጉንና አፈጻጸሙን ካለፈው ለማሻሻል፡ በተለይም ወንጀለኛንና የመሬት ውርስን በሚመለክት፡ ሚኒልክ ተጭማሪ ደንብ ለሚኒስትሮችና ዳኞች ሠጡ። ይኸውም በንጉሡ ፈቃድ በነጋሪት በአደባባይ አዋጅ መነገሩን የጽሕፈት ሚኒስትሩ ዘግበዋል።

በፍርድ ቤት የቅጣት መጠን ላይ ያተኮረውና የተከለከለው አሠራር በወጀል  የተከሰሰ ግለሰብ ከመሬቱ ይባረር የነበረውን ሚኒሊከ እንደሚከተለው አሻሻሉት፦

ሀ.  “በወንጀልም እየተያዘ መሬቱን የሚነቀል ሰው ሁሉ ወንጀልም ቢገኝበት በከብቱና በሰውነቱ ይቀጣ [ስለዚህ ትርጉምና አፈጻጸም ተጨማሪ መረጃ አላገኘሁም] መሬቱን አይነቀል።

ለ. “ነፍስ ገድሎ የሄደ በመንግሥት ክፉ ሥራ የሠራ ይነቀል። ርስትም ማለት ያባት የናት መሬት ደግሞ በወርቁ የገዛው መሬት ነው እንጂ የመንግሥት መትከያ የሆነ አይደለም።

ሐ.  የትከያም መሬት ቢሆን መንግሥት ርስት ያደረገለት ይረታል።

መ.  መካንም የሞተ እንደሆን አባቱ እናቱ ገንዘቡንም ርስቱንም ይውሰዱ እንጂ ሹም አይውረስ።

ሠ.  እናት አባት የሌለው እንድሆን ወንድሙ እህቱ ይውረሱ። እናት አባት የሌለው እንደሆን ግን እስከ አራት ትውልድ ላለ ቅርብ ዘመዱ ይሁን።

ረ.  ከመዶቹ ለይቶ ለእገሌ ይሁን ብሎ የተናዘዘ እንደሆነ ተናዘዘለት ይውሰድ። ከአራት ትውልድ ወዲያ የሆነ ግን ውርሱ ለሹም ይሁን ብለው ወሰኑ።

 

ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ፡ የሕግና የፍርድ ቤቶችን ክልሎች (territorial judicial jurisdiction) እንዲህ ያብራሩሉ:-

“በዚህም ዘመን በመሬትም በገንዘብም በሌላም ነገር እየተጣላ አዲስ አበባ ለጩኸት የሚመጣው ሰው ሁሉ ዳኝነቱ፡ አንድ ሰው ላይ ብቻ ሆኖበት፣ ሰው እየበዛ ሕዝብ የሚጎዳ ቢሆን ሃገርዎን ኢትዮጵያን ከስድስት ከፍለው ለአንድ ክፍል ሁለት ወምበር እያደረጉ ለስድስቱ 12 ወምበሮች ሾሙ። እነዚህም ወምበሮች፡ ያዋዋሉትንና ያነጋገሩትን በቀን ብዛት እንዳይረሳ፡ በየክፍሉ ሶስት ሶስት ፀሐፊ አደረጉበት።”[ገጽ 336-338]።

 

የነዚህንም አጠቃላይ ዓላማ: ፀሐፊ ትዕዛዝ ሲያብራሩ፡ እንዲህ ነበር የገለጹት፦

“ኢትዮጵያን ተካፍለው የተሾሙት ወምበሮች ከጃንሆይ አደባባይ ላይ ለየራሳቸው፤ ቦታ ተለይቶላቸው ሲፈርዱ ይውላሉ። ነገርም ገብቶ ለጩኸት የመጣ ድሃ ቢበየንበትም ቢበየንለትም ነገሩ አልቆለት ወደርሻው፣ ወደ ቁፋሮው ቶሎ ወደቤቱ ስለተመለሰ ደስ እያለው እንደዚህ ያለ ዳኛ የሠጠን አምላክ ይክበር ይመስገን እያለ ለእግዚአብሔር ምሥጋና ያቀርባል፤ ሆነ።” [ገጽ 339]

 

እነዚህ የንጉሡ እርምጃዎች በሕግና ፍትሕ ረገድ ያሰገኟቸው ውጤቶች፡ እንደዚህ ተዘግበዋል፦

“ከዚያ ጀምሮ በርስትም በጉልትም በሌላም ነገር እየተጣላ ከወምበሮች ላይ የተነጋገረው ስው ሁሉ በብይንም፡ ቢረታታ የተበየነው ቃል እየተጻፈ በምሥክርም የምስክሮቹ ስምና አገር፡ የምስክሮቹ ቃል እየተጻፈ፡ ባለጋራና ባላጋራውም በስም በስሙ እገሌ ረታ፡ እገሌ ተረታ እየተባለ ያጽፍ ጀመር። ዳግመኛ እነዚያ የተረቱት ሰዎች ውለታቸውን ተካከደው የመጡ እንደሆን ወምበሮቹ መመሰከራቸው ቀርቶ በዚያው በደብዳቤው ቃል ይለያዩ ብለው አዘዙ። ይህም ትዕዛዝ በመኳንንቱም በሠራዊቱም ዘንድ የተወደደ ሆነ።” [ገጽ 339]

 

*******

በብዙ መልኩ በኢትዮጵያ መጻዒ ዕድል እምነታቸውን በመግለጽ የሚታውቁት ፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ፡ በ1901 ዓ.ም. ነው “ከዚህም በኋላ ያገራችንን የኢትዮጵያን ክብር እንጽፋለን” ሲሉ የከተቡት። ይህን ምን እንዳሳሰባቸው እርግጠኛ ሆኖ መናገር ያስችግራል።

ባለፈው ዓመት ሃገሪቷን ሚኒልክ የማዘመን ሥራቸውን አጠናክረው ቀጥለዋል። ከዓመት የሥራ ውጤት በሚመስል መልኩ፡ ንጉሡም የፍርድ ሚኒስትሩን ሥራ ከአፈንጉሥ ነሲቡ ወደ አፈንጉሥ እስጢፋኖስ አስተላልፈፋዋል። አያሌ የክልል አስተዳደሮችም ለዋውጠዋል።

ምናልባትም በፀሐፊ ትዕዛዝ ገብረሥላሴ በኩል ክብደት የተሠጠው የንጉሡ እግር መታመምና መንቀሳቀስ ስላስቸገራቸውና ‘ልጃቸውን’ ልጅ ኢያሱን አልጋ ወራሽ አድርገው መሾማቸው ሊሆን ይችላል።

በዚህ ሁኔታ ውስጥ እራሳቸውንም ለማጽናናት ይሆናል፣ ስለኢትዮጵያ ብሩሕ ወደፊት ዘገባችውን ያጠቃለሉት፦

“እግዚአብሔር የኢትዮጵያን መንግሥት ከቀዳማዊ ሚኒልክ በፊት ከርሱም ወዲህ እስካሁን ድረስ ፈጽሞ አልጣላትም… ይልቁንም በኛ ዘመን ትውልዳቸው ብቻ ያይደለ፡ ርኅራሄያቸውም እንደ ዳዊት የሚሆን ዳግማዊ ሚኒልክን አስነሥቶ የኢትዮጵያን መንግሥት ጠበቃት…ዳግማዊ ሚኒልክ እናት አባት ልጃቸውን ተግትተው እንዲጠብቁ፡ የኢትዮጵያን መንግሥት ተግተው ጠበቋት። በጥበብና በውቀትም አደገች። ከዚህ ቀደም ያላየችውን ልዩ ልዩ የጥብብ መኪናና የንጉሡዋን መልክ ባላድ፡ በሩብ፡ በተሙን፡ በግርሽ፡ በተምብር አሰቀረጡላት። ከዚህ ቀደም መኖርዋን የማያውቁ ክለዩ ልዩ መንግሥት የመጡ ሰዎችም በአደባባይዋ ይመላለሱ ጀመር።” [ገጽ 341]

 

 

ተዛማጅ፦

Relevance of Ethiopia’s sterling victory at Battle of Adwa to present realities

 

ዐቢይ አሕመድ ከሰኔ 18/2010 የፓርላማ ንግግሩ ወዲህ ሌላው ያረካኝ የወደድኩለት መልዕክቱ!

29 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

“ዓለም የማይሠጣትን ሰው አታቅም፤ ያልሠጣትን ሰው አትቀበልም፣ አታገንም፤ አታከብርም፤ ዓለም ገብጋባ አይደለችም፤ ግን ለሚሠጥ ሰው ክብር አላት፤ ያልሠጣትን ስው ከነመፈጠሩም አታስታውስውም!”

 

 

”ወንጀለኞቹ ማንም ይሁኑ ማን . . . አድነን ለሕግ ማቅረባችን አይቀሬ ነው” — ጠ/ሚ ዐብይ አሕመድ

12 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

 

 

ጠ/ሚ ዶክተር አብይና ምክትላቸው ከሃገር መከላከያ ከተለያየ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ የጦር ሠራዊት አባላትጋር ተወያዩ!

10 Oct

Posted by The EthiopiaObservatory (TEO)

አዲስ አበባ፣ መስከረም 30፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ እና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከሃገር መከላከያ የተለያየ ክፍለ ጦር ከተውጣጡ የጦር ሰራዊት አባላት ጋር ተወያይተዋል።

አባላቱ በነበራቸው ቆይታ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ጥያቄ ማቅረባቸውን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነር ጀኔራል ዘይኑ ጀማል ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ጀኔራሉ አባላቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድን አግኝተው ጥያቄያቸውን በአካል ለማቅረብ ወደ ቤተ መንግስት ማምራታቸውንም ነው የተናገሩት።

በወቅቱም ሰላማዊ ውይይት ማድረጋቸውንና ጠቅላይ ሚኒስትሩም ለአባላቱ በዚህ መልኩ ወደ ቤተ መንግስት መምጣታቸው ስህተት መሆኑን ነግረዋቸው አባላቱም ስህተቱን ተቀብለዋል ነው ያሉት።
ውይይቱ ከተጠናቀቀ በኋላም አባላቱ ፑሺ አፕ እንዲሰሩ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ከታዘዙ በኋላ የእራት ግብዣ እንደተደረገላቸውም ገልጸዋል።

ከዚህ ውጭ ግን ቤተ መንግስት አካባቢ የነበረው ሁኔታ ፍጹም ሰላማዊ መሆኑንም ኮሚሽነር ጀኔራሉ አስረድተዋል።

አባላቱ ከተጣለባቸው ሃገራዊ ሃላፊነት እና ግዳጅ ጋር ተያያዥ ጥያቄዎችን ማንሳታቸውን የጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት አስታውቋል።

በውይይቱ የመከላከያ አባላት እንደዜጋ ጥያቄያቸው ሊደመጥ እና በተግባር መመለስ እንዳለበት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ጠቁመዋል።

መንግስት እንደሃገር የጀመረው የማሻሻያ ስራ በመከላከያ ዘርፉም በተመሳሳይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ተጨማሪ ውይይት በሚፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ መድረኮች ይመቻቻሉ ያሉት አቶ ደመቀ፥ ጥያቄዎችም በቀጣይ መንግስት በጀመረው የለውጥ ጉዞ ደረጃ በደረጃ እንደሚፈቱ አረጋግጠዋል። 

የመከላከያ አባለቱም በውይይቱ ለተነሱ የዘርፉ ችግሮች በሰከነ አግባብ እንዲፈታ እና የተጀመረው የለውጥ ጉዞ እንዳይደናቀፍ ታሪካዊ ሃላፊነታቸውን እንደሚወጡ ዝግጁነታቸውን ማረጋገጣቸወን ነው ፅህፈት ቤቱ ያስታወቀው።

 

ተዛማጅ፡

የዐቢይ አስተዳደር የታጠቁ ኃይሎች በአገር ውስጥ እንዲንቀሳቀሱ እንደማይፈቅድ በድጋሚ አስታወቀ! ለምንስ ፈቀደ ሲጀመር?

 

Can EPRDF Hawassa Convention be on path of true reform, as Ethiopians are promised time and again, or it’s still business as usual?

4 Oct

Posted by The EthiopiaObservatory (TEO)

Related:

11th EPRDF Congress will determine the fate of our country, PM Abiy Ahmed

 

Ethiopia’s Prime Minister says 2020 elections will be free & should not be delayed because of his reforms

25 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ADDIS ABABA (Reuters) – Ethiopia’s prime minister said on Saturday an election due for 2020 would be free and should not be delayed by his sweeping reforms to the African nation’s politics, economy and diplomacy.

Abiy Ahmed, who took office in April, also told his first news conference that the World Bank would provide $1 billion in budget support in the next few months.

The Washington-based institution and other donors suspended budgetary help following a vote in 2005 that was disputed by the opposition and accompanied by violence that killed 200 people.

Explaining the World Bank’s decision, the prime minister said: “This is due to the reforms taking place in the country.”

Since becoming prime minister, the former intelligence officer has taken steps to open up the state-dominated economy, released political prisoners and ended decades of hostility with neighbouring Eritrea.

The 42-year-old leader has promised to give more room to opponents in a nation where there are no opposition lawmakers in parliament. He has also lifted a state of emergency put in place after his predecessor resigned in February following political protests since 2015 in which hundreds were killed by security forces.

“My dream and ambition is for democratic elections to be held. Otherwise, what legitimacy can any official have without the mandate earned through elections?” the 42-year-old leader said. “I do not believe that elections should be delayed until reforms are completed.”

Opposition candidates did not win any seats in the 2015 vote. Before Abiy took office the government’s crackdown on opposition parties was criticised by the United States and other governments that provide aid to the nation that has been racing to industrialise even as it struggles to feed itself.

Although many Ethiopians have cheered him for promising change, some political dissidents have voiced skepticism that political space will be opened as long as Abiy’s ruling Ethiopian People’s Revolutionary Democratic Front (EPRDF) remains in power.

Abiy said the EPRDF, which seized power in 1991 after toppling a military junta, planned to focus next year on “preparations for free elections to be held.”

%d bloggers like this: