Tag Archives: Republican Protection Force

መጭው ምርጫ ከፊታችን ተደቅኖ የኦዲፓና ኦነግ ግብግብና ጠለፋ ለሕዝቡ ደኅንነትና ለሃገሪቱም ፖለቲካ መስከንና ኤኮኖሚ ዕድገትዋ አሳሳቢ የችግር ምንጭ ነው!

23 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ሰሞኑን መንግሥት (ኦዲፒ) ከኦነግ ጋር ያለውን የተበላሸ ግንኝነት አስመልክቶ መግለጫ ከሠጠበት ቀን ጀምሮ፣ በየዕለቱ ግንኙነታቸው ወደ ከፋ አቅጣጭ ሲያመራ ይታያል። ይህን አስመልክቶ ኦዲፒና ኦነግ ሳይደማመጡ የሚመክሩ መምሰላቸው በጊዜ ማብቃት አለበት! የሚል አጠር ያለ ጽሁፍ አቅርበን ነበር።

ይህንኑ አስመልክቶ የዚህ ገጽ ኢዲቶሪያል ከሁሉ በላይ የዜጎችን ነጻነትና እኩልነት እንዲሁም ለሃገራችን የተረጋጋ ሁኔታ መፈጠርን ይደግፋል። ስለሆነም መግለጫውን እንዳየን፡ በሃገሪቱ ከተፈጠረው አለመረጋጋት ጋር ተያይዞ፡ የሚከተለውን አመለካከት ሠንዝረናል፦


ይህ በእንዲህ እንዳለ ቅዳሜ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጊዜያቸውን ካሳለፉባቸው ጉዳዮች አንዱ “የረፐብሊኩን ጥበቃ ኃይል” ዝግጅት መመልከት ነበር። በወቅቱ እንደተገለጸው፡ “የሪፑብሊክ የጥበቃ ኃይል አባላት የመንግሥት ባለስልጣናትንና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው በሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከል የተቋቋመ” መሆኑ ታውቋል።

ይህ ረፐብሊካን ኃይል ሲሉ ዓላማው በአንድ በኩል “የአገሪቱን ሕገ መንግሥትና ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓት ከማንኛውም ጥቃት ለመከላከል በአዲስ የተቋቋመ የደኅንነት መሣሪያ” መሆኑን ሲጠቆም፡” የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ትኩረት ሚዛን ያረፈው “የመንግስት ባለስልጣኖችና ቤተሰቦቻቸውን የጥቃት ዓላማን አንግበው ከሚንቀሳቀሱ ኃይሎች ከሚሰነዘር ጠለፋና እንግልት ለመከላከልና ለማዳን” ስለመሆኑ ያወሳል።

ምናልባትም ዋና መንስዔው ከሁሉም በላይ ኦዲፓ (መንግሥት)  ከኦነግ ጋር ያለው ሽኩቻ ነው የሚል ጠንካራ ግምት አሳድሮብናል። ለረፐብሊኩ ልዩ ኃይል መቋቋም ምክንያቱ ይኸው ኦዲፓ (መንግሥት)  ከኦነግ ጋር ያለበት ፍልሚያ አድርገን ወስደነዋል። አሳሳቢው ነገር (ምናልባትም ለሁለቱ ቡድኖች)  ከፊታችን ምርጫ እየተቃረበ መሆኑ ችግሩን ሳያወሳስበው አልቀረም።

ምርጫውን በተመለከተ ኦዲፓም ሆነ ኦነግ እኩል ዕድል እንዲኖራቸውና ሕዝቡ እኩልነትን፥ ነጻነትን፡ የሕግ የበላይነትንና ዲሞክራሲን ያሠፍንልናል የሚለውን ለመምረጥ ዕድል እንዲያገኝ እንመኛለን። እንሻለን።

በሌላ በኩል ደግሞ በኃይል የሚፈልገውን ለማግኘት የሚደራደር ቡድንን ወይንም አካል እንደ ሕገ ወጥና ለሕዝባችን የችግር ምንጭ አድርገን ስለምንወስድ— ኦነግ ሃገር እንዲገባ የጋበዘውን አስተዳደር በኃይልና በሸፍጥ ለመናድ የሚያደርጋቸው ጥረቶች በሃገራችን ላይ አደጋ ጋርጧል። 

ይህንንም አስመልክቶ፣ በትዊተር ገጻችን ወዲያው እኩለ ቀን ላይ የሚከተሉትን ሃሣቦት ሠንዝረናል፦ 


ከላይ የተጠቀስው የረፐብሊኩ ጥበቃ ኃይል፡ አሰያየሙ ከግለሰቦች ይልቅ ሃገርና አመራሯ ላይ ያተኮረ ቢመስልም፡ ምሣሌው ከየት እንደተወሰደ አናውቅም። ስንገምት ግን ክ11936-1939 በተደረገው የስፔይን የሲቪል ጦርነት የተበደርነው ይመስላል። የስፔን ብሐርተኞች ( Nationalists)/ሕዝብ ሁለተኛውን ረፐብሊክ ከቀኝ ዘመም አማጺ ወታደራዊ ኃይሎች ለማዳን የተደረገውን ትግል አመላክች ነው። ብዙ ዋጋ ተከፍሎበት፥ ስፔን አንድነቷንና የመንግሥቷን ሉዓላዊነት ለማስከበር አስችሏታል— በወታደሩና በሲቪሉ መካከል እስከዛሬ የዘለቀ መራራቅን/አለመተማመን ቁስልን የፈጠረ ችግር ቢሆንም!

================

ከዋዜማ ሬዲዮ የተዋስነው–ከአሰመራ ከተመለሰው ዉጪ ያለው የኦነግ ተዋጊ ከየት መጣ? የሚለው ውይይት ጠቃሚ ሆኖ አግኝተነዋል:-

ኦነግ ማንስ አስታጠቀው? የኦነግን ሠራዊት እየመሩ ያሉት እነማን ናቸው? እውነታው ኦነግ ያለፉትን ሶስት ዓመታት በተለይ ባለፉት ወራት በሕቡዕ ሲደራጅና ተዋጊዎች ሲያሰለጥን ቆይቷል። ይህን ገዥው የኦሮሞ ዲሞክራሲዊ ፓርቲም ያውቅ ነበር። ዋዜማ ያሰባሰበችውን መረጃ እንደሚከተለው አሰናድተነዋል።

 

 

 

%d bloggers like this: