Tag Archives: Robbery

አይ ሕወሃት! አቤት ቅሌት!አ ይ ጊዜ!

10 Jan

The Ethiopia Observatory (TEO)

ስብሃት ነጋንም ኣጓጉል አደረግሽዉ አይደል! ሰዉ ነንና ይህን ፎቶ ያየ ሁሉ ሠቅጠጥ ይላል!

ስብሃት ነጋ ሌላ ሰው ቢሆን ‘አይ ምሥኪን’ ብዬ ውስጤ ትንሽ መራራት ሊሰማኝ ይችል ነበር! ነገር ግን ቀበጦቹ/ባለጌዎቹ ሕወሃቶች ኢትዮጵያን ልታከናንቡ ያዘጋጃችሁላትን ውርደት በዚህ በሚታየው መልክ ራሳችሁ ተላበሳችሁት!

የኢትዮጵያ አምላክ እግዚአብሔር ክብሩ ይስፋ! 

ምርኮኛዉ ስብሃት አዲስ አበባ ደርሶ ወደ ‘መጨረሻ’ ማረፊያው ሲወስድ! (Picture credit: Fana)

የሕወሃቱ ስብሃት ነጋ! የክፋትህ መጠን~~አነተም ጓደኞችህም~~በጠቅላላው ሁላችሁም የተጠናወታችሁ መጥፎነት፣ ሌላው ቀርቶ በአሁኑ ሰዓት ሕዝባችን ደግነቱን እንዲነፍጋችሁ አድርጓችኋል! ዛሬ ስብሃት ነጋ በወከላችሁ ሃፍረትና አመድ መሰል ሁኔታውም የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊቱን ቢያዞር አልገረምም!

የሚገርመው ስታንጓጥጠው የኖርከው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ዛሬ በአንድ እግርህ ብቻ ካልሲ አድርገህ፡ እውነተኛውን ማንነትህን በሚገልፅ መልክ መቅረብህ፣ ትላንት አንተ የነበርክበት ቦታ ዛሬ እንዳንተው ሁለት እጆቻቸውን ኪሶቻችው ውስጥ ሰንቅረው—’አለኛም ሰው የለም ባዮቹን— ‘ከኔ ሁኔታ በጊዜ ትምህርት ውሰዱ!’ በላቸው! ‘አሁን የኔ ለፈጸምኩት ግፍ፡ ጥጋብና ወስላታነት የምከፍለው ዕዳ ነው!’ በላቸዉ!

በዚህ እርጅና ባዳከመው ዕድሜ ተከብረህ መኖር ሲገባህ፣ ያላጣኸውን ስታሳድድ፣ ሁሉንም አጣኸዉ! ለዓመታት ያንተና የጭፍሮችህ ‘መሬት አልበቃ አለችን’፡ ሃገራችንን ብዙ ጎድቷል! ብዙ ወገኖቻችን ሕይወቶቻቸውን አጥተዋል!

የኢትዮጵያ አምላክ ግን ኢትዮጵያን እንደማይጥላት አሳይቷል! የትግራይ ሕዝብስ በምን ዕዳዉ?

ኢትዮጵያ ይህ በሽታ ከሥሩ እንዲነቀል ትሻለች!

እኔም ጆሮዬን አቁሜ የቀሪዎቹን ወንበዴዎች ፍፃሜ ጠብቃለሁ!

የኢትዮጵያ መከላካያ ሠራዊት በዳዮቿን ለመቅጣት በቀላሉ ሰው ከማይደርስበት ድረስ ወርዳችሁ—ፊቱ ሳይላላጥ፡ የቡጢ ምልክት ሳይኖርበት፡ ሳይሠበር፡ ሳይገረፍና ሳይጎሳቆል መምሰል የሚገባውን አስመስላችሁ በማቅረባችሁ—በምወዳትና በምኮራባት ብቸኛ ሃገሬ ስም ፍቅሬንና ከበሬታዬን እገልጽላችኋለሁ!

ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!

አንዳርጋቸው ጽጌ ከቤተልሄም ታፈሰ ጋር!መታየትና መደመጥ ያለበት ቃለ መጠይቅ!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

ሰባት ዩኒቨርሲቲዎችና መከላከያ በገንዘብ፡ ወርቅ፣ ቤትና ስኳር ዘረፋ ወንጀል እጅ ከፍንጅ ተያዙ፤ ሌሎችም!

17 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የፀረ – ሙስና ኮሚሽን ባለፉት አስራ አንድ ወራት ውስጥ በህገወጥ መንገድ የተመዘበሩ ያላቸውን ከ81 ኪሎ ግራም በላይ ወርቅ፣ ከ26ሺ ካሬ ሜትር በላይ የከተማ መሬት፣ አራት ህንፃዎች፣ ከ74 ሚሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብና ሌሎች ንብረቶች ማስመለሱን ገለጸ፡፡
Continue reading

የሕወሃትና ተወካዮቹ አገር አስተዳደር – ሀስት፤ ሸፍጥ፤ ክህደት፤ ዘረፋ፤ እሥራት፤ ግርፋትና ግድያ

4 May

Posted by The Ethiopia Observatory

I. በኦሮሞች ላይ የተፈጸመውን ግድያ፣ እሥራትና፡ ግርፋት አስመልክቶ የተፈጸሙ ውሸቶች – ሪፖተር እንደዘገባቸው

    ከአዲስ አበባና የኦሮሚያ ልዩ ዞን የተቀናጀ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተማሪዎች ተቃውሞ አሰሙ
    Continue reading

Ethiopia-Kenya border tense: 3,000 Kenyans flee Ethiopia Border

17 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory

by Mathews Ndanyi, The Star

More than 3,000 families have fled their homes at the Kenya-Ethiopia border following increased tension after 10 fishermen were killed by Ethiopia militia yesterday.

Turkana and Ethiopian fishermen on Lake Turkana have been fighting, causing the families to retreat more than 30km from the border. Tukana North DC Eric Wanyonyi said security teams have been deployed along the border. Leaders from the region led by Senator John

Munyes said the frequent attacks along the border have impoverished the Turkana community. Seven bodies of fishermen killed by Ethiopian militia at Todonyang in Turkana North are still missing. Wanyonyi said GSU officers are patrolling Todonyang and areas around the lake.

ዓረና ተዘረፈ – ምነው በስሜን ኢትዮጵያ ዘረፋው ቤተክርስቲያንና ፖለቲካ ላይ አተኮረ?

18 Jun

በትግራይ ክልል ቃፍታ ሑመራ ወረዳ የተከፈተው የዓረና ትግራይ ሉዓላዊነት ለዲሞክራሲ ፓርቲ አዲስ ጽሕፈት ቤት መዘረፉን ፓርቲው አስታወቀ፡፡ በተጠቀሰው አካባቢ ልዩ ስሙ ማይካድራ በተባለው ሥፍራ የሚገኙ የፓርቲው አባላትና ደጋፊዎች በራስ ተነሳሽነት ከፈቱት የተባለው አዲሱ ጽሕፈት ቤት፣ የቢሮ መሣርያዎች ተሟልተውለት ሥራ ለመጀመር በዝግጅት ላይ ሳለ መዘረፉን ነው ፓርቲው ያሳወቀው፡፡

በወረዳ የዓረና ፓርቲ ኮሚቴ አስተባባሪ የሆኑት አቶ ገብረ ዋህድ ሮምሐ ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ በዛሬው ቀን የፓርቲው አመራር አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት ጽሕፈት ቤቱን በይፋ ሊከፈት በዝግጅት ላይ ነበር፡፡ የአካባቢው ሹሞች ጽሕፈት ቤቱ በተዘረፈበት ዋዜማ ሲያስፈራሩዋቸውና ሲዝቱባቸው መዋላቸውን አቶ ገብረ ዋህድ ተናግረዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ጽሕፈት ቤቱን ለፓርቲው ያከራዩ ግለሰብ ‹‹ቤትህን ለጠላቶች አከራይተሃል›› በሚል ኃላፊዎቹ ሲዝቱባቸው መሰንበታቸውን ገልጸው፣ ለፓርቲው ያከራዩትን ቤት መልሰው እንዲረከቡ የቀረበላቸውን ጥያቄ አለመቀበላቸውን አክለው አስረድተዋል፡፡

ወንበርና ጠረጴዛን ጨምሮ በቢሮው ውስጥ የነበሩ የጽሕፈት መሣርያዎችና የፓርቲው ሰነዶች መወሰዳቸውን ዓረና ፓርቲ አስታውቋል፡፡

በትግራይ ክልል ለመጀመርያ ጊዜ ከአራት ዓመት በፊት ተቃዋሚ ሆኖ ብቅ ያለውና ከሕወሓት በአንጃነት በወጡ አመራሮች ዋና አስተባባሪነት የተመሠረተው ዓረና ፓርቲ፣ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ አንድነት መድረክ (መድረክ) ስብሰባ አባል ነው፡፡ ፓርቲው በመቐለ የሚገኘው ዋናው ጽሕፈት ቤቱን ጨምሮ በማይጨው፣ በአድዋና በአላማጣ ቢሮዎች መክፈቱ ሲታወስ፣ የአድዋው በምርጫ 2002 ተዘርፎ መዘጋቱንና፣ የአላማጣው ደግሞ ፓርቲው በራሱ ችግር መዝጋቱን ገልጿል፡፡

የሑመራ ጽሕፈት ቤቱን ዝርፊያ በተመለከተ የአስተዳደርና የፀጥታ ኃላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ ያልተሳካ ሲሆን፣ የወረዳው ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ላይ መሆኑን ከምንጮች ለማወቅ ተችሏል፡፡

(Source:The Reporter)

Transforming Ethiopia TE

%d bloggers like this: