Tag Archives: Shemelis Abdissa

በተለመደው መንገድ እየሄድን ሲመስለን፣ ኢትዮጵያን ሲመች በሽመልስ አብዲሣ መስመር ለማስኬድ ዐቢይ የሚያደርገው መተጣጠፍ ሃገር ያፈርሣል!

24 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)


====0000====

ባሌ ውስጥ የካቲት 10/2020 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ግድብ ሲመርቁ ከሸመልስ አብዲሣ ጋር በዓላማም ሆነ ተግባር ተመሳስለው ያረፉበት ንግግር መቼም አልተረሳንም!

እረ ተረኞቹ በሃጫሉ ስም ዘረፋው ይብቃችሁ!

9 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ለሃጫሉ ሁንዴሳ ቤተሰቦች የአዲስ አበባ ከተማ ከተማ ከንቲባ በግብር ከፋዩ ገንዘብ ቤት ተሠጣችው። እስካሁንም ለአክቲቪስቱ ብዙ ነገሮች በስሙ ተሠይመውለታል–ትምህርት ቤቶች፡ መንገዶች፣ አምቦ ዩኒቨርሲቲ ማዕከል፣ ወዘተ

ይህ የትላንቱ የከንቲባዋ ‘ሥጦታ’ ያለጥያቄና የከተማው ሕዝብ አንዴም ሳይወያይበት ዘረፋ ተደርጎ ተወስዷል—ተረኛው የዐቢይ አስተዳደር የታወቀበት ባሕር!

የሚያስገርመው ለተያያዙት ዘረፋ አልጠግብ ባይነታቸው እየተተገበረ የሚታየው በሳዑዲ ዐረብያ በቁም ዕሥር ላይ የሚገኘው አላሙዲ ከ1980ዎቹ ያለበት በአሥርት ሚሊዮኖት ብር ዕዳዎች ተሠርዞለታል ተብሏል። በአጭር አባባል ከላይ እስከ መካከል የተከፋፈሉት እነማናቸው? ኢትዮጵያ እንደሆነ፡ መንግሥት በተባለ ኃይል ዘላለም እንድትዋረድና እንድትዘረፍ መሆኑ ግልፅ ነው።

ሃጫሉም በቁሙ ከእነዚሁ ዘራፊዎች አልተለየም–በአዲስ አበባ ተሠጥቶት የነበረውን መሬት በ80 ሚሊዮን ብር መሸጡ ይታወሳል።

እረ ተረኞቹ ይብቃችሁ!

‘ይቅር …. ታ…. ታታ ….. ሿሿሿ’—    የጳጉሜው ይቅርታና ያሬድ ኃይለማርያም ትዕዝብት!

7 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ዛሬ የይቅርታ ቀን ተብሎ መሰየሙን እና አንዳንድ የመንግስት ባላሥልጣናት፤ እንዲሁም የኃይማኖት አባቶች ይቅርታ ሲጠይቁ እየሰማው ነው። በሃሳብ ደረጃ ነገርየው ጥሩ ነው። ይቺን ነገር አምናና፣ ካቻምናም አድርገናት ነበር። ከአምናው ይቅርታ መጠያየቅ ወዲህ በአገራችን የተፈጸሙትን ነገሮች ብቻ ማሰብ ይህ ነገር ከልብ ነው? ያስብላል። የኃይማኖት አባቶችን እና የሕዝብን ለጊዜው ልተውና በባለሥልጣናት በየአመቱ ስለሚጠየቀው ይቅታ ይችን ልል ወደድኩ።

ይቅርታ ጥፋትን እና ጸጸትን ተከትሎ የሚመጣ ነገር ነው። በፖለቲካው አውድ ጥፋት ሳይኖር ይቅርታ አይጠየቅም። ጥፋት፤ ከዛ መጸጸት፤ ከዛ ተጠያቂነት፣ ከዛ ይቅርታ ይከተላል። ፖለቲከኞች እና ባለሥልጣናት የሚፈጽሙት ጥፋት በአገር እና በሕዝብ ጥቅምና መብት ላይ ያነጣጠሩና ጉዳታቸውም ከፍ ያለ ስለሆነ ይቅርታ የሚጠይቁትም አገርን እና ሕዝብን ነው። በመሆኑም ፖለቲከኞች፤ በተለይም ባለሥልጣናት የሚጠይቁት ይቅርታ ሌላው ተራው ሰው እንደሚጠይቀው ይቅርታ ሾላ በድፍኑ አይነት ነገር አይደለም። ቢያንስ ከዚህ የሚከተሉትን የይቅርታ ቋንቋዎች እና ሃሳቦች የያዘ መሆን አለበት።

፩ኛ/ ተገልጾ ለታወቀው ጥፋት መጸጸትን መግለጽ (Expressing regret)

፪ኛ/ ለተፈጸመው ጥፋት ኃላፊነትን መውሰድ (Accepting responsibility)

፫ኛ/ የተጎዳን መካስ ወይም ያበላሹትን ማስተካከል (Making restitution)

፬ኛ/ ዳግም ተመሳሳይ ጥፋት እንዳይፈጸም የሚያስችል ከእውነተኛ ፍላጎት የመነጨ የእርምት እርምጃ (Genuinely repenting) እና

፭ኛ/ ተበዳይ ወገን ይቅርታ እንዲያረግ መጠየቅ (Requesting forgiveness)

እኔ ይሄን ካልኩኝ ዘንዳ ዛሬ አቶ ታከለ ኡማ እና ሌሎች ባለሥልጣናት በቴሌቪዥን መስኮት ብቅ ብለው “ሳናውቅ ለበደልናችሁ ይቅርታ” ያሉበትን መንገድ መፈተሽ ደግሞ የእናንተ ሥራ ይሁን። ይህ አይነቱ ይቅርታ አምና እና ካቻምና ከተደረጉት የይቅርታ ጥያቄዎች በምን ይለያሉ? ከዛስ በይቅርታው ማግስት ምን ሆነ?

እንግዲህ እኔ ፖለቲከኞች ስለሚጠይቁት የይቅርታ አይነት ከላይ ያሉትን አምስት ነጥቦች አስቀምጫለሁ። እናንተ የሹሞቹን ይቅርታ በእነዚህ መስፈርቶች እየመዘናችሁ ‘ይቅር ብለናል’ ማለቱን ለእናንተው ልተው።

እንደ እኔ የፖለቲከኞቻችን ይቅርታ ከላይ ያለውን መስፈርት እሲኪያሟላ እና ከልብ እስኪሆ ድረስ፤ ‘ይቅር …. ታ…. ታታ ….. ሿሿሿ’ ብያለሁ።

መልካም ሰንበት!

======000======

 

ግፈኞችን አራጆችን ያስደነገጠው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን መግለጫ

3 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

 

ወቅቱን የጠበቀ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን መግለጫ!

26 Aug

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Our reality or rhetoric? Ethiopia’s Prime Minister Abiy Ahmed warns citizens “No one is greater than the country”!

 

 

How would Abiy Ahmed respond today to this positive message by the Church? Could he see it as useful direction after the massacres of citizens & destructions the nation suffered? Or, as usual, he would consider the Church source of danger to his power?

 

Could anyone help citizens decode the meaning of Shemelis Abdissa’s supposed conversion from the height of his madness, as noticed in his recorded message from seven plus months ago about “ቁማሩን ተጫውተን በልተነዋል” to this by which he addressed the people of Bale hours ago?

 

%d bloggers like this: