Tag Archives: Torture in Ethiopia

ሌሎችን በማሠቃየት ከታየው የሕወሃቶች አረመኔያዊነት በኋላ ወንጀለኞች ለፍርድ፤ ሕወሃትም ወደ ማክተም መገፋት አለበት!

13 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)

በየሣምንቱም ሆነ በየአጋጣሚው፡ ሕወሃት መቀሌም ሆነ በየመንደሩ— በኢትዮጵያ የሚካሄደውን ለውጥ በመቃወም — በጸረ-ኢትዮጵይዊነት ያሠልፋል! ዓላማው አፍኖ የያዘውን የትግራይን ሕዝብ ከራሱ ጋር የተቆራኘ በማስመሰል፡ መሸሸጊያው ለማድረግ ነው።  ይህም የመጀመሪያው አይደለም። 

ሕዝቡም በልቡ፡ ይህ ለግንባሩ ጥቅም እንጂ ዋርካው እንዳልሆነ ያውቀዋል የሚል እምነት አለኝ። የዚህ እምነቴ መሠረት ደግሞ፡  ሁሌም የድርጅት ዓላማና  የሕዝብ ፍላጎቶች የተሳለጡ አለመሆናቸውን ታሪክ ስለሚያስተምረን ነው።  በሃገራችንም  ለአያሌ አሥርታት ከ”ሠልፍ ካልወጣችሁ ስኳርና ዘይት አታገኙም”፡ “ድጋፍ ካልሠጣችሁ ከቀበሌ ቤት ትባረራችሁ”፣ 2ከገዥው ፓርቲ ጋር ካለተባበራችሁ ከኅብረት ሥራ ማኅበር ብድር አታገኙም” ወዘተ ኢትዮጵያውያን ተገቢውን ትምህርት ወስደዋል።

ይህ ማለት ግን በእምነት፡ በዘር አዋዜ የታጀሉ፡ በቅጥር፡ በጥቅማ ጥቅም  የተሳሰሩ ግለሰቦች የሉም ማለት አይደለም!

ከሁሉም የሚያሳዝነው፣  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በትግራይ ወንጀለኛውና ፋሽስቱ ሕወሃት የሕገ መንግሥት አስከባሪ አድርጎ  ራሱን መሠየሙ ነው! ደብረጽዮንም በተከበረችው አክሱም ጽዮን  መንበር ላይ—  ለዚያውም በማትያስ አጋፋሪነት — አክሊል ደፍቶና ተኮፍሶ መታየቱ፡ በስብሃት ነጋ ትዕዛዝመላው ኢትዮጵያውያን ምዕመናን እምነት በወንጀለኛው ሕወሃት ቡድን መረገጡ ነው!

እውነቱን እንነጋገር ከተባለ፣ ትግራይ የግንባሩ መሣሪያ  ላለመሆንና ድርጊቱን በጣም በሚጠላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ፊት ትሥሥሩ የግንባሩን ሕይወት ማራዘሚያ ከመሆን ውጭ  ሃቀኛ ሁኔታውን አንጸባራቂ አይደለም። ሆኖም በዚህ አስከፊና አሳዛኝ ወቅት ሕዝቡ — ሕወሃት እንደሚያስተጋባው —የወንጀሎቹ ደጋፊና ተሳታፊ አለመሆኑን በግልጽ ማሳየት በቻለ፡ ለሁሉም ዜጎች እንዴት ጠቃሚ በሆነ!

ህ ጉዳይ የወደፊቱ የትግራይ ሕዝብ የችግር ምንጭ መሆኑን የተገነዘቡት ሌተና ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሣይ ነሐሴ 24/2016 የትግራይ ሕዝብ ሚና ወደፊት ምን መሆን እንዳለበት እንዲጠና በጻፉት አስተያየት (የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦችየሚከተለውን ምክር ለግሠውነበር፦

የዚህ ጉዳይ የወደፊቱ የትግራ ሕዝብ የችግር ምንጭ መሆኑን የተገነዘቡት ሌተና ጄኔራል ጻድቃን ገብረተንሣይ ነሐሴ 24/2016 የትግራይ ሕዝብ ሚና ወደፊት ምን መሆን እንዳለበት እንዲጠና በጻፉት አስተያየት (የሃገራችን ፖለቲካዊ ሁኔታና የመፍትሔ ሃሳቦችየሚከተለውን ምክር ለግሠውነበር፦

“አሁን ባለችው ኢትዮጵያ የትግራይ ህዝብ የሚኖረው ድርሻና የሚጫወተው ሚና ምን መሆን አለበት? የትግራይ ህዝብ የስልጣን ዘመኑን በፀጥታ ሃይሎች ድጋፍ የሚያራዝም በየግዜው ከህዝብ እየተነጠለና በህዝብ እየተጠላ የሚሄድን የፖለቲካ ስርዓት ጠባቂና ተከላካይ ነው መሆን ያለበት? ወይስ ሌላ ምርጫ አለው? የትግራይ ህዝብ አሁን ባለው የኢትዮጵያ የፖለቲካ ሁኔታ የሚወስደው የፖለቲካ አቋም ምን ይሁን? ብሎ መጠየቅ ይገባል። በሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦችስ ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን የሚጥስ ፖለቲካዊ ስርዓት ጠባቂ ተደርጎ የተለየ ጥቅም የሚያገኝ ጠላት ተደርጎ ነው መታየት ያለበት ወይስ በዴሞክራሲና በእኩልነት ላይ ለተመሰረተ የህዝቦች አንድነት ፣ ለህዝቦች መብት መከበር ለትክክለኛ ፍትሕና ለፍትሃዊ ኢኮኖምያዊ ተጠቃሚነት በፊታውራሪነት የሚታገል ህዝብ ተደርጎ ነው መታየት ያለበት? ብለን እየጠየቅን መልሱን መፈለግ ይኖርብናል።”

ግፍና ሠቆቃ በኢትዮጵያ የሥውር እሥር ቤቶች

ይህንን ውይይት ለኔ አሁን አስገዳጅ ያደረገው፣ አያሌ ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦች ውስጥ ከማክሰኞ ምሽት ታኅሳስ 11/2018 ወዲህ ከፍተኛ ኃዘን ንዴትና ቁጣ ስሜት መቀስቀሱ ነው። በአቃቤ ሕግ ቀደም ሲል በተገለጸው መሠረት፡ ማክሰኞ በትግራይ የወንበዴዎች አመራር ትዕዛዝና ተሳታፊነት በዜጎቻችን ላይ የተፈጸመው ሠቆቃ ዶክመንታሪ ፊልም ለሕዝብ ዕይታና ግንዛቤ በቴሌቪዥን ቀርቦ ዐይተናል።ማናችንም እንደሰብዓዊ ፍጡር ግለሰባችን መሸከም የማይችለውን ወንጀሎች አያሌ ወጣቶቻችንና ምሁራኖቻችን ላይ በተለይም ያለኃጢያታቸው በዝርያቸው ብቻ እየታፈኑ ለሠቆቃ መዳረጋቸውን ተመልከተን ልባችን ተሠብሯል!

ሃገር ውስጥም በአፈናው ምክንያት፡ ዜጎቻችን ላይ ሥቃዩ ሲፈጸም፡ ሌሎቻችን ለዓመታት እንዳላየን አፋችንን ሸክፈን ፊታችንን አዙረን ለመኖር ብንሞክርም፡ በማንኛውም ሰላማዊ ሕይወት አልተገኘም! የሕወሃት ሰዎች —ተማርን የሚሉት ጭምር —ጥጋብና ብልግና እንዲሁም አይተው የማያውቁት ሃብትና ሥልጣን አላግባብ ‘ባለቤት’ መሆን ስላሰከራቸው— ሌላውን በመፍራት ብቻ በድንቁርናና ስግብግብነታቸው ምክንያት— ሕዝብን መርገጥ፡  ማሰናከል ማኮላሸትና  ማጥፋት ምርጫቸው ሆነ! 

አያሌ ዜጎቻችን በሕይወት ለመኖር ዕድሉን ተነፍገዋል! 

ዶኪመንተሪ ውስጥ የሚታዩት እነዚህ ሰቆቃ የደረሰባቸው ዜጎቻችን ተመልሰው ጤናማ ሕይወት ለመምራት አይችሉም! እንዴት ነው የሚደገፉትና በፊታቸው የተጋረጡት ችግሮች የሚቃለሉላቸው? መልሴ ሶስት ዘርፍ አለው:-

ሀ.   ትግራይ ውስጥ የተሸሸጉት ፀረ-የሰው ዘር የሆኑት ወነጀለኞች የሕዝብና የሃገራችን ጠላቶች በመሆናቸው፡ ንጹሃን ትግራውያን ላይ ሁሉ አስከፊ ድርጊታቸው እንዳይለጠፍ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ እንዳሉት “ግፍ ሠርቶ መንደላቀቅ አይቻልም[ና]” በገባው ቃል መሠረት፣  ወንጀለኞቹን የዐቢይ አስተዳደር ለፍርድ ለማቅረብ ማናቸውንም እምርጃ በአፋጣኝ እንዲወስድ እንጠብቃለን/ እንጠይቃለን! ወንጀለኞቹ በኢትዮጵያና የዓለም ሕዝብ ፊት ፍርዳቸውን መቀበል  ይገባቸዋል። 

ለ.  የአንድ መንግሥት ኃላፊነት የዜጎቹን ደኅንነት መጠበቅና ማስከበር እንደመሆኑ፡ በተፈጸመባቸው ሠቆቃ ምክንያት አካለ ጎደሎ የተደረጉት፡ እስትንፋሳቸው ስላለ ለመኖር ለሚገደዱ እነዚህ ዜጎች እንክብካቢ ያስፈልጋቸዋል። ለዚህም በዘረፋም ሆነ በተለያየ መንገድ ሕወሃቶች  ያፈሩት ሃብትና ንብረት ለነዚህ ወገኖች እንክብካቤ መዋል ይኖርበታል። እስከዚያ መንግሥት ሊንከባከባቸው ይገባል!

ሐ. እነዚህ የሕወሃት ወንጀለኞች የሕግን የበላይነት እንዲቀበሉ፡  ኢትዮጵያ ሁሉንም ዐይነት አማራጮች መመርመርና መጠቀም ይኖርባታል። ከነዚህም መካከል፣ የአፍሪካ ዲክታተሮች –  በአፍሪካ አንድነት ድርጅት መድረክ ና በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት አማካይነት (በቴድሮስ አድሃኖምና/ኃይለማርያም ደሣለኝ መሣሪያነት ሊያጠፉት የሞከሩትን  — የዓለም አቀፍ  የወንጀል ፍርድ ቤትን (International Criminal Court -ICC) በመፈረም ቀደሚ እርምጃ በመወስድ እንቅስቃሴ መጀመር አለበት! ከLeague of Nations ጀምሮ ሃገራችን የምትታወቀው የሕጎች መከበር ለብሔራዊና ዓለም አቀፍ ሰላም የሚኖረውን እሴት ሃይማኖቷ በማድረጓ መሆኑ እስከዛሬ ይጠቀሳል!  ይህ ዛሬ እንደገና ሊታደስ ይገባዋል!

የትግራይ ሕዝብ ለእነዚህ እርምጃዎች ስኬት ከኢትዮጵያ ወገኖቹና ከመንግሥት ጋር ተባባሪ እንዲሆን ይጠበቃል። ሕወሃት መቶ በመቶ የ2015ን አምስተኛ ዙር ምርጫ አሸነፍኩ ብሎ ሃገር በአሰችኳይ ጊዜ አዋጅ  ለመግዛትት ሲያደባ ነው፡ የኢትዮጵያ ሕዝብም ትዕግሥቱ አልቆ ግማሽ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እልሁን ሠንቆ ወደ ትግል በመግባት የአሁኑን ለውጥ ማምጣት የቻለው።

ከላይ ሶስተኛውን እርምጃ በተመለከተ፡ ነገሩን ግልጽ ለማድረግ ICC (ዓለም አቀፍ  የወንጀል ፍርድ ቤት) አፍሪካ ውስጥ ተቀባይነት እንዳያገኝ የአፍሪካውያን ጠላት ነው ብለው በአፍሪካ አንድነት (የዲክቴተሮች ክለብ) ውስጥ የሃሰት የጥላቻ ዘመቻ ያካሄዱት:- ኢትዮጵያ (ሕወሃት)፡ ሱዳን፡ ኡጋንዳ፣ ሩዋንዳ ዋናዎቹ ናቸው። እነዚህም ሃገሮች በጨቋኝ አመራሮች መዳፍ ሥር ስለሆኑ፡ መሪዎቹ አንድ ዓላማ ብቻ ነበራቸው— ራሳቸውን ከዓለም አቀፍ ፍርድ ማዳን!

ከብሔራዊ ጥቅማችን በላይ ምንም ስለሌለ፡ ይህ ዓለም አቀፉን ኅብረተሰብ የማንቀሳቀስ እርምጃ ኢትዮጵያ አያሌ ገንዘብ ከሃገር ሸሽቶ (በሕወሃቶችና የውጭ አጋሮቻቸው)፡ በውጭ ባንኮች ስለተከማቸና ተንከባላይ ሃብት በተለያዩ የአውሮፓ፣ እስያና አፍሪካ ሃገሮች ውስጥ ስላፈራና ተጠቃሚዎቹም የኛው ሌቦችና የውጭ ደላሎቻቸው በመሆናቸው፡  በሕግ ሃብቱንና ንብረቶቹን ለማሳገድና ብሎም ለማስመለስ ማናቸውንም ዓለም አቀፍ ዕድል መጠቀም ያስፈልጋል!

የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ነበር የተመድ ዋና ፀሐፊ የነበሩት ኮፊ አናን — ነፍሳቸውን ይማረውና — ታኅሳስ 18/2016 ከነበራቸው ልምድ በመነሳት ለአፍሪካውያን ወገኖቻቸው The Guardian ላይ የሠጡት ምክር እንዲህ ይላል

“The apparent African exodus from the international criminal court must be stopped or the most heinous crimes will be allowed to go unpunished… ICC remains the continent’s most credible court of last resort for the most serious crimes … [It] does not supplant national jurisdictions; it only intervenes in cases where the country concerned is either unable or unwilling to try its own citizens.”

እንደሁኔታው እየታየ፣ ትግራይ የመሸጉት የሕወሃት ወሮበሎች  ኢትዮጵያ በፈረመቻቸው ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ወንጀሎች በሕጉ በብሔራዊ ደረጃ በቅድሚያ ተፈላጊ ናቸው (Person/s of interest)። ከአፍሪካ ጥቅሞችም አንፃር፡ ሰላምን በማናጋትና ለሕይወቶች መጥፋት ምክንያት በመሆናቸው፡ ፍላጎታቸው ሰላም ሣይሆን የአፍሪካ ቀንድ ወደ ጦርነት አዘቅት ማሽቆልቆል ስለሆነ፡ ሰላምን በማደፍረስ ወንጀል ተፈላጊ ሊሆኑ እንደሚችሉ መመከር አለባቸው!

በሠቆቃው ዶኪመንተሪ እንደተገለጸው፡ በብዛት ደግሞ እስከ 70% ጥቃቱ የተፈጸመው ኦሮሞች ላይ ሲሆን፡ ቀሪው ሰለባ የሆኑት በሃገሪቱ ሁለተኛ ከፍተኛ ቁጥር ባለው  ሕዝብ — አማሮች ናቸው።

የሥልጣን ላይኛውና ታችኛውም መዋቅር ውስጥ የተሠገሠጉት በአያሌው ሕወሃቶች በመሆናቸውም፡ ይህ ከአንድ ብሄረሰብ ሰዎች በየጊዜው የሚወጣው ቅሌትና ውርደት እስካሁን በሃገራችን ታሪክ ተወዳዳሪ አልተገኘለትም!

የቢቢሲ 4 The Reith Lectures 2018 አሸናፊ ካናዳዊዋ Prof Margaret MacMillan አንድ ጥይቄ ቀርቦላቸው ሲመልሱ፦

“War even affects our language. In English, if you want to say something rude, you tend to use the word ‘Dutch’ or ‘French’ and that refers back of course to times when the Dutch and the British or the French and the British were enemies.” 

በሌላ በኩል ደግሞ፣ ስለ ግጭትና ጦርነት ጎጂነት ብዙ የተመራመሩ በመሆናቸው፣ The Uses and Abuses of History (2010) ፈረንሣዊውን ፈላስፋ Ernest Renan በአንድ ወቅት “The existence of a nation is a plebiscite of every day, as the existence of an individual is a perpetual affirmation of life” የሚለው ሃሣብ ቀልባቸውን እንደያዘው በጽሁፎቻቸውና ሌክቸሮቻቸው ሁሉ ይንጸባረቃል! ይህም አለመክንያት አይደለም!

ስለሆነም እንደማንኛውም በሰው ልጅ ላይ እንደተፈጸመና እንደሚፈጸም ዘግናኝ ሥቃይ በእነዚህ 27 ዓመታት ዘመነ አፓርታይድ በመላው ኢትዮጵያ፡ የሕወሃት ቅጥረኞች በወጣትና በተማሩ ኢትዮጵያውያን ላይ የፈጸሙት ጭካኔ፡ የትግራይ ተወላጅ ለሆኑ ዜጎቻችን በቀላሉ የማይገመት የጥላቻና የቂም በቀል አደጋ እንዳረገዘ  ማድረጉን መገመት አያዳግትም! 

ኢትዮጵያውያንም ሰዎች እንጂ መላዕክት ስላልሆን፣ አልፎ አልፎ ክፉው እንደሚሆን ጥርጥር አይኑር! ባይሆን ደስ ይለኛል፤ መሆንም የለበትም! ይህን መሰል ችግር በቂም በቀል አይፈታም! በዓለም ላይ እስካሁን ከተደጋገሙት ጦርነቶችና ቀጣይ ግጭቶች የምንማረው ቢኖር፡ አሁን ሕወሃት የሚሠራው ዐይነት የሞኝ ብልጠቶች የችግሮች ምንጭ ናቸው!

የሕወሃቶች ትግሬዎች ስለሆን ተጠቃን ስሞታ እጅግ ያማል

መንግሥት በዕቅድም ይሁን ካለማሰብ፣ እስካሁን በትግሬዎች ላይ የበቀልና የማግለል እርምጅ ሲወስድ አይታይም። አንድ አስገራሚ ምሣሌ ልስጥ! 

ሪፖርተር  በረቡዕ ዕትሙ  እንደዘገበው፣ ሁለት የትግራይ ተወላጆች የዘር መድልዎ ሳይደረግባቸው፣ እስከ ኅዳር 29/2018 ሥራና ሹመት ላይ ነበሩ:  አንዱ አቶ መአሾ ኪዳኔ —የአቶ ጌታቸው አሰፋ ልዩ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ሆነው ሲሠሩ የነበሩና —እንዲሁም እስከተከሰሱና በቁጥጥር እስከዋሉ ድረስ፡ በዲፕሎማትነት እስታምቡል ተመድበው፣ የመሂጃ ቀናቸውን እየተጠባበቁ እንደነበሩ ተገልጿል። 

ሀ.  አቶ መአሾ ኪዳኔ የተወነጁሉት የኦነግና የአርበኞች ግንቦት ሰባት አባል ናቸው ተብለው በሐሰት የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ሥር እንዲውሉ፣ ለበታች ሠራተኞች ትዕዛዝ መስጠታቸውንና ጉዳት እንዲደርስባቸው ማስደረጋቸውን መርማሪ ቡድኑ ለፍርድ ቤት አስረድቷል። በተጨማሪም አቶ መአሾ ኪዳኔ “ከገቢያቸው በላይ ሦስት ቤቶች መገንባታቸውንና ምንጩ ያልታወቀ ሀብት አከማችተውና ለባለቤታቸው ውክልና ሠጥተው በመገኘታቸው በሙስና ወንጀልም እንደጠረጠራቸው” ፓሊስ አስታውቋል፡፡ 

ለ.  ሁለተኛው ተከሳሽምየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት የኦፕሬሽን ክፍል ዳይሬክተር መሆናቸው የተገለጸው ሌላው የደኅንነት አባል አቶ ሃዱሽ ካሣ ሲሆኑ እርሳቸውም የተወነጀሉት “በከባድ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ወንጀል”ና አላግባብ የተገኘ ሃብት ማከማቸት ነው!

ከሁሉም የሚያስገርመው፣ የሕወሃት ወሮበሎች ሌሎች ኢትዮጵያውያንን በዘራቸው ምክንያት በጥላቻ ሲያሰቃዩና ሲገሉ 27 ዓመታት የቆዩ ሰዎች በወንጀል ተጠርጥረው ሲያዙ፡ የመጀመሪያ ዑዑታቸው በዘራቸው ምክንያት እንደተሠቃዩ የሚያሰሙት ስሞታቸው በተለይ በአሁኑ ወቅት ያሳምማል።

ለምሣሌም ያህል በፌዴራል ፖሊስ ዳይሬክተር ጄኔራል እነዶር ወርቅነህ ገበየሁ ተመልምለው ቀደም ሲልም ሽልማት ተሠጥቷቸው  የነበሩት አቶ መአሾ ኪዳኔ የታሠሩበትን ምክንያት— ሪፖርተር እንደዘገበው— እንዲህ ሲሉ ይገልጻሉ፦

“የተከሰስኩበትና በቁጥጥር ሥር እንድውል የተደረገበት ምክንያት ሁለት ነው፡፡ አንደኛው የትግራይ ተወላጅ መሆኔ ሲሆን፣ ሁለተኛው ደግሞ በፖለቲካ ውሳኔ ነው፤”

 

በነፃነትና ዲሞክራሲ ስም ላለፉት 27 ዓመታት በብቸኝነት ሥልጣን ላይ በመፈናጠጥ የትግራይ ሕዝብ ነፃነት ግንባር (ሕወሃት) በዚህም ምክንያት ሌቦችን፡ ነፍሰ ገዳዮችንና ወንጀለኞችን ከሕግ ለመደበቅ ሕወሃት ተደጋጋሚ ሠልፎች ሲያደርግ የኢትዮጵያ ሕዝብ እነዚህ ሰዎች መቼ ነው ከከንቱነታቸው የሚላቀቁት ከማለት ባሻገር፡ በመገረም ነበር የሚመለከታቸው።

ምነው እነዚህ ሰዎች እንዲህ ፍንጣቂ ሰብዓዊነትና ይሉኝታ አጡ?

ከላይኛው ጋር ተያያዥ የሆነ ሌላ ምሣሌ ላቅርብ:

ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያምን (የአቶ ዐባይ ወልዱ ባለቤት) ሕወሃት ግንባሩ አመራር በ12ኛው ኮንግሬስ መስከረም 2015 ላይ ከአባልነት ሊያባርር ፣ ነሐሴ ውስጥ በሲያትል በተከበረው የትግራይ ፊስቲቫል ላይ እንዲገኙ ተደረገ።  ስለሆነም እግረ መንገዳቸውን ከደኅንነቱ ኃላፊ አቶ ጌታቸው አሰፋ ወንድም ከአቶ ዳንኤል አስፋ ጋር ዋሽንግቶን ዲ.ሲ. ኢትዮጵያ ኤምባሲ ጎራ ይላሉ።    

ለነገሩ ወይዘሮ ትርፉ — ከሕወሃት አመራርነት ቢባረሩም፡ የአቶ ዐባይ ወልዱ ባለቤት ስለሆኑ  ተከታዩን በር መከፈት የግንባሩ ባህል በመሆኑ— ወድያውኑ ያላንዳች ብቃት አውስትራሊያና ኔውዚላንድ አምባሳደር ሆነው ተሾሙ። ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቴድሮስ አድሃኖም ከዲፕሎማቲክ ባህልና አሠራር ውጭ በቦታው ላይ የነበረው አምባሳደር ቤተሰቡን አንኳ ሳያሰባስብ በአስቸኳይ እንዲወረውር መደረጉ በአያሌው ተነግሯል!

የሕወሃትን ሥራ አከናወኑ ለመባል፣ መቶ ያህል በሃገሬው ነዋሪ ከሆኑ የትግራይ ተወላጆች ብቻ (በግል ጥሪ) ስብሰባ ስለተደረገ —አምባሳደሩንና የቤት ሠራተኞችን ጭምር  አስወጥተው — እርስ በርስ የተባሉበትን ስብሰባቸውን አደረጉ!

ምን አጨቃጨቃቸው?  ለወይዘሮ ትርፉና አቶ ዳኔኤል አሰፋ የቀረበላቸው ጥያቄ፡ “የኢትዮጵያ ህዝብ፣ ብሄር ብሄረሰቦች ለምንድነው የሚጠሉን?…ዲሞክራሲና አንድነትን የማንፈልግ የሚመስላቸው ለምንድን ነው?” 

ሁለቱ የሕወሃት መልዕክተኞች በሠጡት መልስ፡ “የኢትዮጵያ ህዝብ አይጠላንም … ይልቁንም ባለን ቦታና ሚና ይበልጥ እየተከበርን እንገኛለን …በየትኛውም የኢትዮጵያ ክልል የትግራይ ተወላጆች በሰላምና ተከብረው እንደሚኖሩ አስረድተዋል። የሚጠሉን ተቃዋሚዎችና ከህወሃት ያፈነገጡ ግለሰቦች ናቸው።”

የሚቀጥለው አስገራሚውና የብስጭት ጥያቄያቸው ያተኮረው ልማት — ትግራይን ዘሎ —ለምን አዲስ አበባና ባሕር ዳር ላይ ብቻ አተኮረ የሚል እንደነበር ታውቋል። ዋናው ጉልህ ፍላጎታቸው በምሽቱ በምሥጢሩ ስብሰባ የተንጸባረቀው ዓመታዊ ስፖርት ውድድር ትልቅ ስታዲዮም ትግራይ ውስጥ ተሠርቶ እዚያ እንጂ ባሕር ዳር እንዳይካሄድ የሚሻ ነበር።

በመጠኑም ቢሆን፣ ይህም የአስተሳሰባቸውን ጤንነት መቃወስ ያመለክታል!

ማጠቃለያ

ባለፈው ቅዳሜ — የትግራይ ክልል ም/መስተዳደር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል መቀሌ በኢትዮጵያ ሃብትና ንብረት እንዲሁም በአያሌ ዜጎች ላይ በብሔራዊ ደረጃም ሆነ በዓለም አቀፍ ሕግጋት የተወገዙ ወንጀሎች የፈጸሙ ወንጀለኞችን አሳልፎ ላለመስጠት፡ ሕዝቡን በመገፋፋትና በማሳሳት ዛቻና ጦር ሰበቃ ውስጥ መግባታቸውን በገሃድ በኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ  የተቃጣ ነው!

ብዙ ቅር የሚያሰኙኝ ነገሮች ቢኖሩም፡ ኢትዮጵያ ትላንት በወሮበሎች ከተያዘችበት 27 ዓመት የተሻለ አመራር ዛሬ አላት ብዪ አምናለሁ! በዚህም ምክንያት፣ በኢትዮጵያ ውስጥ አሁን በዘር ሳቢያ ሥልጣን ላይ እንደ ወያኔዎቹ ለመንጠላጠል የሚሞክሩትን አመራሩ ካየና ገብስና ገለባውን ከለየ በኋላ ሃገሪቱን በትክክለኛ መሥመር እንዲወስዳት እጠብቃለሁ!

ያ ከተደረገ — ሕወሃት ብዙ ክፋትና ጥፋት ሊያደርስ የሚችልበት ቀዳዳዎች መኖር እንደተጠበቀ ሆኖ— ከኢትዮጵያ ጋር የጥፋትን ጎዳና ከመረጡ ከታሪክ አለመማራቸውን ብቻ ነው የሚያሳየው!

ለማንኛውም በቴሌቪዥን የወገኖቻችንን ሠቆቃና ሥቃይ ማየቴ ቢያናድደኝም፣ ስለስማነው አስፈሪ ሠቆቃ በቴለቪዥን ዐይተን ለማመንና የኢትዮጵያ ሕዝብ ጠላት የሆነው ሕወሃት ምን ዐይነት አስከፊ አውሬ መሆኑን በማየት፣ የግንባሩን ዘላለማዊ ሞት እንድንፈልግ ኢትዮጵያውያንን የሚገፋፋን ልዩ ኃይልና አስፈላጊ ቁጣ አድርጌ ተቀበየዋለሁ።

 

 

አብዲ ዒሌ በሶማሌ ክልል ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፡ ዘረፋዎችና ግድያዎች ሕዝቡን ይቅርታ ጠየቀ!

12 Jul

የእዘጋጁ አስተያየት፡

ለዚህ ነፍሰ ገዳይ ባላቸው ቀረቤታ ምክንያት የሕወሃት ሰዎች ዜናው እንኳ እንዲጻፍ ያደረጉት፣

“የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ለተፈፀሙ ስህተቶች ኃላፊነት በመውሰድ የክልሉን ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ!” በማለት ነው!

ከመቼ ወዲህ ነው ስው መግደል ወደ ስህተት ደረጃ የወረደው? በየቀኑ አይደል እንዴ የሕወሃት ገጾች ‘ታላቅ መሪ’ እያሉ ለዚህ የሰብዓዊ መብቶች ነቀርሳ ሲስገዱ የኖሩት?

ኦሮሞችና ሶማሌ ዜጎቻችን ግጭት ላይ በነበሩበትና አንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን በተፈናቀሉበት ወቅት አይደል እንዴ በአሜሪካን ሃገር የሚኖሩ የሕወሃት ‘ተጋሩ አባላት’ ድጋፋቸውን ለአብዲ ዒሌ የሠጡት?

የሰው ዘር በማጥፋት ወንጀል — እንደ ሕወሃቶች — አብዲ ዒሌ አንድ ቀን ለፍርድ መቅረብ እንጂ ስለምን ይቅርታ ነው የሚቀባጥረው?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Abdi pleading for forgiveness of Somalis in particular and Ethiopians in general. Is destroying thousands of lives a matter of simple errors and mistakes? Don’t give international human rights law, Ethiopians and the international human rights community this TPLF political shenanigan!

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀሙድ በህዝቡ ላይ ለተፈፀሙ ስህተቶች የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ ኃላፊነት እንደሚወስዱ በመግለፅ የክልሉን ህዝብ በይፋ ይቅርታ ጠየ

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ይህንን ያሉት ትናንት በተጀመረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት አንድ መቶ ቀናት ያስመዘገቡትን ስኬት ለምክር ቤቱ አባላት ባብራሩበት ወቅት ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደረጃ የጠቅላይ ሚኒስቴሩን የይቅርታ፣ የፍቅርና የመደመር መርህ ከግብ ለማድረስ የበኩላቸውን ለመወጣት በስፋት ውይይት ተደርጓል፡፡

“በዚህም የክልሉ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ኢሶዴፓ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላከናወኗቸው ሥራዎች ትልቅ ክብር አለን፤ መደመርን መርጠናል” ብለዋል አቶ አብዲ።

ርዕሰ መስተዳደሩ በምክር ቤት ንግግራቸው አክለው እንደገለጹት፥ የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥና የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል አበክረው ይሰራሉ።

ቀደም ሲል በህዝቡ ላይ ለተፈፀሙ ስህተቶች የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ ኃላፊነት እንደሚወስዱ ገልፀው ህዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

”ሥራ ሲሰራ ስህተቶች ይኖራሉ፤ ነገር ግን በጎ ተግባራትን ማጎልበት እንዲሁም ለተፈጠሩ ስህተቶች በይፋ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ባህል በመሆኑ ሁላችንም ማዳበር ይኖርብናል’’ ብለዋል፡፡

አቶ አብዲ አክለውም፥ ቀደም ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ የነበረው ኦብነግ ከመንግስት የተሰጠውን እድል በመጠቀም ወደሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባም ጠይቀዋል።

በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን የይቅርታና የፍቅር መንገድ ጥሪ የግንባሩ መሪዎች አክብረው በመቀበል እድሉን እንዲጠቀሙበት ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የግንባሩ አመራሮች ለዓመታት የያዙትን ጥላቻ በማስወገድ ለቀረበላቸው የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት በአገሪቱና በክልሉ የተጀመሩ የፍቅር፣ የአንድነትና የመደመር መርህ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤቱ ጉባኤ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 

ተዛማጅ:

Sat image of Jail Ogaden

Video: Torture in Somali Region Prison in Ethiopia

“We are Like the Dead”

Interview: Years of Untold Suffering at Jail Ogaden

Torture and Ethiopia’s Culture of Impunity

Ethiopia: Torture in Somali Region Prison

 

Greenland’s humane prisons experience, if torcher-loving TPLF regime could pick a lesson, despite the nation’s poverty!

17 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Sarah Lazarus

CNN) – Nestled into the stunning Arctic landscape with panoramic views of sparkling fjords and snowy mountains, Ny Anstalt could easily be mistaken for a luxury ski lodge. But this stylish complex in Nuuk, the capital of Greenland, is actually a prison.

As any onlooker can deduce, when it opens in 2019 it will not be a normal penitentiary. It will be a “humane prison” — a correctional facility that emphasizes rehabilitating criminals through positive design, rather than punishment.
Continue reading

የኢሣት ‘ዕለታዊ ውይይት’ : የተነሱት ጉዳዮች ብዛትና ጥልቀት ዕንባዬን ተቆጣጥሮታል! ብዙ ትግል ቢጠበቅብንም ለኢትዮጵያ ኮራሁባችሁ!

27 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

ሕወሃት መሃል ኢትዮጵያ- አዲስ አበባ – የፈጸማቸው ሰቆቃዎች በዳኞች ፊት ቢጋለጡም፣ እነዚህ የመጀመሪያዎቹ አይደሉም! ዝምታው ግን እስከመቼ?

1 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በጋዜጠኛ መሳይ መኮንን
 
ፍርድ ቤት ውስጥ ሕዝቡ በእንባ ይራጫል። አንድ ሰውነቱ በግርፋት የተዘለዘለ እስረኛ ልብሱን አውልቆ “እዩት ሰውነቴን። አኮላሽተውኛል። ዘር እንዳይኖረኝ አድርገውኛል።” እያለ ሲቃና ለቅሶ ባሸነፈው ድምጽ ይማጸናል። “የኢትዮጵያ ሕዝብ ይፍረደኝም” አለ። ፍርድ ቤቱ በሀዘን ክው ብሎ ቀረ። ሁሉም ተላቀሰ። አሁንም እዚያው አዲስ አበባ ወጣቷ ንግስት 10ሩም የእጆቿ ጥፍሮች ተነቅለው በኪሶቿ ይዛለች።

የደረሰባት ቶርቸር መልኳን አገርጥቶታል። በጉጠት የተነቀሉት ጥፍሮቿን እንድትይዛቸውም አልተፈቀደም። በኋላም በሕወሀት ገራፊዎች ተነጥቃለች። የሻሸመኔዋ ሸጊቱም ትናገራለች ”ጆሮዬ እስኪደማ ድረስ ተደብድቤ ተጎድቷል።ግራ እጄ ታሟል። በእግራቸው ነበር የሚረግጡኝ። ጸጉሬን እየጎተቱ ነበር የሚደበድቡኝ።”
Continue reading

የሕወሃት ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ከቂሊንጦ ቃጠሎ ጋር በተገናኘ የመብት ጥሰትና ሰቆቃዎች መፈጸማቸውን አረጋገጠ!

12 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሪፖርተር
 
ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም. በፌዴራል ማረሚያ ቤቶች በቂሊንጦ ማረፊያ ቤት ላይ ከደረሰ የእሳት ቃጠሎ ጋር በተገናኘ፣ 16 እስረኞች አካላዊ ጉዳት የደረሰባቸው መሆኑንና የሰብዓዊ መብት ጥሰት መፈጸሙን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን አረጋገጠ፡፡

በእነ መቶ አለቃ ማስረሻ ሰጤ መዘገብ 38 ተከሳሾች በቃጠሎው ተጠርጥረው ከታሰሩ በኋላ፣ ቃጠሎውን እነሱ እንዳስነሱ እንዲያምኑ ለማድረግ በቂሊንጦ የቀጠሮ ማረፊያ ቤት አስተዳደር አማካይነት የሰብዓዊ መብት ጥሰት እንደደረሰባቸው ለፍርድ ቤት በማመልከታቸው፣ ኮሚሽኑ አጣርቶ ሪፖርት እንዲያደርግ በታዘዘው መሠረት ማጣራቱ ታውቋል፡፡
Continue reading

Torture in Ethiopia!                   ወንጀል ፈጻሚዎቹ ፊልም ተዋንያንን ማሠለፍ ጀምረዋል!

25 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
በሃገራችን በየቀኑ በዜጎቻችን ላይ ሰቆቃ ይፈጸማል። ለዘረኛው ሕወሃት አስተዳደር፡ ይህም ሕዝብን አስፈራርቶ ረግጦ የመግዣ መሣሪያ ሆኖአል።

ዛሬ ፌስ ቡክ ላይ እንዳየሁት ከሆነ፣ ቃሊቲ ውስጥም የተለያየ ዐይነት ስቆቃ ስለሚፈጸም፡ ዛሬ የርሃብ አድማ መጀመሩን መታሰቢያ ቀጸላና ስንታየሁ ቸኮል — የሚከተለውን መልዕክት በማስተላለፍ –አሰምተውናል፡

Continue reading

For Habtamu Ayalew’s sake & the many nameless TPLF-victims, Dr. Tedros Adhanom must finally show decency by withdrawing his name from candidacy for WHO director-general post!

28 Sep

By Keffyalew Gebremedhin The Ethiopia Observatory (TEO)
 

The end is drawing closer

By the ongoing Ethiopian popular uprising, spearheaded by the people of Oromia and Amhara regions, Ethiopians have been empowered and are resolved to dethrone the TPLF, a regime that has been in power for a quarter century through the suppression and oppression of Ethiopians in all sorts of inhuman ways.
Continue reading

%d bloggers like this: