Tag Archives: TPLF conspiracy

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አሕመድ:     “መንግሥት እንደ ዕሴት የሚያራምደው ነጻነት፣ሰላምና ማኅበረሰባዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ራዕይ ሕገ ወጥነትንና አመጽን የማይታገስ ነው !”

19 Aug

Posed by The Ethiopia Observatory (TEO)

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አሕመድ ከወረዳ እስከ ክልል ከሚገኙ የብአዴን መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች ጋር በባህር ዳር ከተማ እየተወያዩ ነው።

በውይይቱ ወቅት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ እንደገለጹት የሃገሪቱ ሕዝቦች ለሕግ የበላይነት መገዛት ዘመን ተሻጋሪ ዕሴት ያላቸው መሆኑን በሥነ ቃሎቻቸው ጭምር የሚስተዋል ነው።

ለዘመናት የዘለቀ የስልጣኔ ባለቤት የሆነችው አትዮጵያ የመንግሥት መዋቅርና ሥርዓት በመዘርጋት በሕዝቦቿ ዘንድ ፍትህና ርትዕ የሰፈነባት ሃገር ናት።

ባለፉት አራት ወራት ሃገራዊ አንድነትንና ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብን በማጎልበት አመርቂ ውጤት እየታየ መምጣቱን ተናግረዋል።

”በሃገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም የይቅርታ፣ የነጻነትና የፍትህ ፋና ወጊሥራዎቻችንን በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚገኙ ዜጎቻችን ተስፋን ያጎናጸፈ ነው” ብለዋል።

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳመለከቱት ሕግን እንደመሳሪያ በመጠቀም በሥልጣን የመቆየት አካሄድ ያመጣቸውን መዘዞች ለማረም ከተወሰዱ እርምጃዎች መካከል ያለአግባብ ይወነጀሉ የነበሩ ዜጎችና የፖለቲካ ቡድኖች በይቅርታና በምህረት እልባት እንዲያገኙ ተደርጓል።

በውጭም ሆነ በሃገር ውስጥ የሚገኙ ዜጎችን በማቀራረብ ለአንድ”በሃገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው ሪፎርም የይቅርታ፣ የነጻነትና የፍትህ ፋና ወጊ ሥራዎቻችንን በሀገር ውስጥም ሆነ በውጭ ለሚገኙ ዜጎቻችን ተስፋን ያጎናጸፈ ነው” ብለዋል።ገራቸው ልማት፣ ብልጽግናና እድገት የሚሰሩበት እድል ከምንጊዜውም በላይ ምቹ ሆኗል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዳሉት ለኢኮኖሚና ፖለቲካዊ ፍትህ የሚደረገው ትግል ከማህበረሰቡ የሞራልና የኃይማኖት እሳቤዎች ጋር ተዋህዶ እንዲዘልቅ ከኃይማኖት አባቶች፣ ከምሁራንና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተቀራርቦ መሥራት ተጀምሯል።

ሆኖም የሕዝቡን ዘርፈ ብዙ ፍላጎቶች በአንድ ጀምበር ማሟላት የሚቻል ባይሆንም በፈጣን ተስፋ ሰጪ መዘውር ውስጥ የተገባ በመሆኑ እንደ ሃገር መውደቅም ሆነ ወደ ኢ-ዴሞክራሲያዊ አሰራሮች መመለስ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጸዋል።

“መንግሥት እንደ ዕሴት የሚያራምደው ነጻነት፣ ሰላምና ማኅበረሰባዊ ብልጽግናን የማረጋገጥ ራዕይ ሕገ ወጥነትንና አመጽን የማይታገስ ነው” ብለዋል።

የዜጎች መብት፣ ነጻነትና ፍትሃዊነት በማረጋገጥ የአካል፣ የሕይወትና የኑሮ ዋስትናቸውን ለማስጠበቅ ሕግንና ሕገ መንግሥታዊ ስርዓትን በሙሉ አቅም ማስከበር ግድ ይላል።

የመንግሥት የጸጥታ አካላትና አመራሮችም የሕግ የበላይነት በግለሰቦችም ሆነ በቡድኖች ሲጣስ በቸልታ ማየት እንደሌለባቸው አሳስበዋል።

በተለይም የግልና የቡድን ጥቅሞቻቸውን በሰላማዊ መንገድ ማስጠበቅ እየቻሉ ከዚህ በተቃራኒው በመሄድ ወንጀልን ለመፈጸም የሚያስቡ አካላት ከድርጊታቸው መታቀብ እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል።

ሕዝብን ከሕዝብ እያጋጩ ጸጥታን በማደፍረስ በሕገወጥ ድርጊት ተሰማርቶ የተገኘና በማንኛውም መልኩ የተባበረ አካል ላይ መንግሥት ሕግን ተከትሎ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ ቁርጠኛ መሆኑንም አስታውቀዋል።

ከ2ሺህ በላይ የብአዴን መካከለኛና ዝቅተኛ አመራሮች በተሳተፉበት የውይይት መድረክ ጠቅላይ ሚንስትሩ የመነሻ ጽሁፍ አቅርበው ተሳታፊዎች በሚያነሷቸው ጥያቄዎች ላይም ማብራሪያ እንደሚሰጡ ይጠበቃል።

ተዛማጅ:

 

 

/ኢዜአ/ኢቲቪ

የኢትዮጵያን ደኅንነት የማይሹ ‘የቀን ጅቦች’ ግጭት በማናፈስ ላይ መሆናቸውን ዶር ዐቢይ እንደገና ለዜጎች ገለጹ!

16 Jun

ተዛማጅ፡

“በአንዳንድ አካባቢዎች የተፈጠረው ግጭት በምንም መስፈርት ህብረተሰቡን የማይወክል መሆኑን መንግስት ገለፀ”!

“The truth is elsewhere:”            French journalist warns Eritrea Commission of Inquiry on allegations in its report

16 Jun

By Keffyalew Gebremedhin, The Ethiopia Observatory (TEO)
by Henri Fourcadis’, Media Part
 
Henri Fourcadis’ article on his blog is in French titled – Erythrée: La vérité est ailleurs. Its direct translation means: “The truth is elsewhere” .

In the light of the conflict now between Eritrea and Ethiopia, which is likely to flare anytime, this piece would attempt to provide essence of Fourcadis’ article, if no one cares for my rusty French, which has benefited from machine-assisted translation.
Continue reading

%d bloggers like this: