Tag Archives: TPLF corruption

በሚሊዮኖች የሚቆጠር ገንዘብ የዘረፉና ያባከኑ ሰዎች ሜቴክን እየለቀቁና ማዕረጋቸውን እየለወጡ በሲቪል አስተዳደርነት እየተቀጠሩ ነው — ለዋና ከተማችን ምክትል ከንቲባዎች ጭምር!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

( ኢሳት ዜና) ጳግሜን 01 ቀን 2010 ዓ/ም የኢሳት ምንጮች እንደገለጹት ሜቴክ በአገሪቱ ውስጥ ላወደመውና ላዘረፈው በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ዋና ተጠያቂ የሆኑ የቀድሞ ወታደራዊ መሪዎች ማእረጋቸውን እየተዉ በሲቪል ተቋማት ውስጥ እየተቀጠሩ ነው።

የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የሆኑት ዶ/ር ሶሎሞነ ኪዳኔ ወደ ከንቲባነት ከመምጣታቸው በፊት የሜቴክ ዋና ተቋራጭ ነበሩ። ዶ/ር ሶሎሞን ኪዳኔ የመከላከያ ሰራዊት አባል የነበሩ፣ መከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ገብተው ከተመረቁ በሁዋላ፣ ስኮላር ሽፕ ተሰጥቷቸው ወደ አውሮፓ ከተጉዋዙ በሁዋላ፣ ከተሰጣቸው ፈቃድ ውጭ በራሳቸው ጊዜ የፒ ኤች ዲ ዲግሪያቸውን ሰርተዋል። ዶ/ር ሶሎሞን አልትራ ቴክ የሚባል ኩባንያ ከከፈቱ በሁዋላ ከሜቴክ ጋር ያለምንም ጫረታ በርካታ ስራዎችን ወስደው ከፍተኛ ገንዘብ ስብስበዋል።

ዶ/ር ሶሎሞን አልትራ ቴክ ኩባንያቸውን ጓደኞቸው እንዲያስተዳድረው በማድረግ ወደ መንግስት ስራ የተመለሱ ሲሆን፣ ከአዲስ አበባ ትራፊክ ቢሮ ወደ ምክትል ከንቲባነት በፍጥነት ተሸጋግረዋል።
ከእርሳቸው ጋር ቀጥተኛ የቢዝነስ ግንኙነት ያላቸው የሚቴክን የተለያዩ እንዱስትሪዎችን ሲመሩ የነበሩት ከሜቴክ እንዱስትሪዎች አንዱ የሆነውን የኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ እንዱስትሪ ስራ አስኪያጅ የነበሩት ሌ/ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ የኮሎኔልነት ማእረጋቸውን ትተው አቶ አሰፋ ዮሃንስ ተብለው በሜቴክ የጥቅም አጋራቸው በዶ/ር ሶሎሞን አቅራቢነት በከንቲባው አቶ ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ ቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሃላፊ ሆነው በመሾም በሜቴክ ከፈጸሙት ከፍተኛ ጥፋት ለማምለጥ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል።

ኮ/ል ወይም አቶ አሰፋ ዮሃንስ በኢትዮጵያ ፓወር ኢንጂነሪንግ እንዱስትሪ ስር የሚገኙትን ሞጆ የሚገኘውን ኬብልና ዋየር ፋብሪካ፣ ታጠቅ የሚገኘው ትራንስፎርመር ፋብሪካ፣ ሰንዳፋ የሚገኘው ሶላር ፋብሪካ፣ መቀሌ የሚገኙት ኢንጂንና ራዲያተር ፋብሪካዎች፣ ሳሪስ የሚገኘው ኮምፓክት ሰብ ስቴሽን፣ እንዲሁም ህዳሴ ግድብ፣ ስኳር ፋብሪካዎች፣ ማዳበሪያ ፋብሪካውንና አዋሽ የሚገኘውን ተርማል በበላይነት መርተዋል።እርሳቸው የመሩዋቸው ሞጆ የሚገኘው ኬብልና ዋየር ፋብሪካ በችርግ ከመተብተቡም በላይ ታጠቅ የሚገኘው የትራስፎርመር ፋብሪካ ደግሞ አገሪቱን ሊከሳራ ህዝቡን ደግሞ ለምሬት የዳረገ ነው። በኢትዮጵያ ውስጥ ከ4 ያላነሱ ትራንስፎርመር አምራቾች ቢኖሩም ፓወር ኢንጂነሪንግ በሞኖፖሊ እንዲይዘው ተደርጎ ለኢትዮጵያ ኤልክትሪክ ሃይል ኮርፖሬሽን በብቸኝነት ያቀርባል። ሌሎች ኩባንያዎች ያመረቱትን የሚሸጡት በፓወር በኩል ብቻ ሲሆን፣ በዚህ የአየር ባየን ንግድ ከፍተኛ ገንዘብ ተዘርፎበታል። ሜቴክ የሚሰራው ትራስፎርመር በፍንዳታ ዘይት ማፍሰስ የሚታወቅ ነው።

ሰንዳፋ የሚገኘው ሶላር ፋብሪካ፣ ራዲያተር ፋብሪካ እና አዋስ የሚገኘው ተርማል ፕሮጀክት በየሃገሩ የተጣሉ ፋብሪካዎች ያለምንም ማስረጃ እና ጥናት የተገዙ ሲሆን፣ በእነዚህም ከፍተኛ ገንዘብ እንደተዘረፈባቸው ምንጮች ገልጸዋል። እነዚህ ከፍተኛ የህዝብ ሃብት ፈሶባቸው የተገዙት ፋብሪካዎች አንዱም ስራ አልጀመሩም፤ ቴክኖሎጂው ያረጀ በመሆኑ፣ እቃዎች ባለሙዋላታቸውና አዋጪም ስላልሆኑ ለወደፊቱም ስራ ይጀምራሉ ብለው እንደማያስቡ ምንጮች ገልጸዋል። መቀሌ የሚገኘው ኢንጂን ፋብሪካም ስራ መጀመር አልቻለም።

እነዚህን ፕሮጀክቶች በበላይነት ያለ ማንም ከልካይነት ፈላጭ ቆራጭ ሆነው ሲመሩት የነበሩት ሌ/ኮሎኔል የአሁኑ አቶ አሰፋ ዮሃንስ የአዲስ አበባ ቴክኒክ እና ሙያ ቢሮ ሆነው መሾማቸው ግለሰቡን ሆን ተብሎ ከተጠያቂነት ለማዳን የተሰራ ሴራ መሆኑን ምንጮች ገልጸዋል። ግለሰቡ በስራቸው ያሉትን ተቋሞች በሙሉ በዘመዶቻቸው ፣ በአካባቢ ልጆችና ከጥቅም ጋር በተገናኘ በመረጡዋቸው ሰዎች እንደሚሩ ማድረጋቸው ለሜቴክ ውድቀት አንዱ ምክንያት ሆኗል። ግለሰቡ ሜቴክ ካፈራቸው የናጠጡ ቱጃሮች መካከል በግንባር ቀደምነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ በውጭ አገር አካውንት እንዳላቸው በዚህም ተገምግመው እንደነበር የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።

ሌ/ል ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ ሰራተኛው አነስተኛ በሆነ ክፍያ የወር ወጪውን መሸፈን ተስኖት እርሳቸው 4 አዳዲስ ውድ መኪናዎችን በመንግስት ወጪ ገዝተው ይጠቀሙ እንደነበር፣ ባለፉት 7 አመታት በወር አንድ ወይም ሁለት ጊዜ ወደ ውጭ አገር በመመላለስ ጊዜያቸውን የሚያጠፉ እንደነበሩ የሚገልጹት ምንጮች፣ አሁንም ከዶ/ር ሶሎሞን ጋር በመሆን በአዲስ አበባ መስተዳድር ውስጥ የቀድሞ አለቃቸውንና ወዳጃቸውን የጄ/ል ክንፈ ዳኘውን የጥቅም ሰንሰለት አላማ ለማስቀጠል መዛወራቸውን ይናገራሉ።

ከ500 ያላነሱ ሲቪል ሰራተኞች በሌ/ኮሎኔል አሰፋ ዮሃንስ ለተተኩት አዲሱ ማኔጅመንት በፋብሪካው ይደርስ የነበረውን በደል በዝርዝር ተፈራርመው አቅርበዋል።

የሜቴክ አመራሮች በአሁኑ ሰዓት አብዛኛውን ሰራተኛ ያለ ክፍያ ለእረፍት እንዲወጣ በማድረስ ስራ አቁሟል በሚባልበት ደረጃ የደረሰ ሲሆን፣ ድርጅቱን የመከላከያና ሲቪል በሚል ለመክፈል እቅድ እንቅስቃሴም ተጀምሯል።

በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባ ም/ል ከንቲባ ዶ/ር ሰሎሞን ኪዳኔንና ሌ/ኮ አሰፋ ዮሃንስን እንዲሁም ሌሎችንም ባለስልጣናት ለማግኘት ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም። ግለሰቦቹ የሚሰጡን መልስ ካለ በሚቀጥለው ዘገባችን ይዘር እንቀርባለን።

 

ተዛማጅ፡

የሜቴክ ዘረፋ የተደራጀ ሌብነት ነው ተባለ

ከሕወሃት ዘራፊዎች በስተቀር የሕዳሴው ግድብ ገንዘብ የገባበትን የኢትዮጵያ መንግሥት አያወቅም! ግድቡም ገና አያሌ ዓመታትና ከፍተኛ ገንዘብ ያስወጣል!

6 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

(ኢሳት)–ነሐሴ 30/2010 ለሕዳሴው ግድብ ግንባታ ተሰብስቦ ከነበረው ገንዘብ ውስጥ ከግማሽ በመቶ በላይ የሚሆነው የገባበት አይታወቅም ተባለ።

ገንዘቡ የደረሰበትን ለማወቅም በመጣራት ላይ መሆኑን የሜቴክ የኮሜርሻልና ሲቪል ምርቶች ኦፕሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ገልጸዋል።

በ5 አመት ይጠናቀቃል የተባለው የህዳሴው ግድብ ግንባታም ቢሆን ከ25ና ከ30 በመቶ በላይ አለመጠናቀቁም ታውቋል።

አቃቤ ህግ በበኩሉ በዚህ ሒደት ውስጥ ያሉ አካላት በሙሉ ተጠያቂ ይሆናሉ ብሏል።

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለቤትነት እንዲሁም በመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) እና ሳሊኒ ኩባንያ የስራ ተቋራጭ የሆኑበት የሕዳሴው ግድብ አፈጻጸም ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከፍተኛ ብክነትና ምዝበራ የተፈጸመበት መሆኑ ተገለጸ።

“ሕዳሴ ሲገለጥ” በሚል ርዕስ ዋልታ ኢንፎርሜስን ማዕከል ባዘጋጀው የምርመራ ዘገባ የሕዳሴው ግድብ በሰባት አመት ውስጥ ያለበት አፈጻጸም ያለበት ደረጃ ከ25 እስከ 30 በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።

በተለይም የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራውን የተረከበው የመከላከያ ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን(ሜቴክ) ያለጨረታ ፕሮጀክቱን አጠናቆ ለማስረከብ በ25 ነጥብ 58 ቢሊየን ብር ተዋውሎ ስራውን መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ የሆኑት ዶክተር አብርሃም በላይ ገልጸዋል።

ዋና ስራ አስፈጻሚው አክለው እንደገለጹት ኮርፖሬሽኑ እስከ አሁን ድረስ ወደ 16 ነጥብ 79 ቢሊየን ብር ክፍያ ተፍጽሞለታል።

ይህ ክፍያ ከፕሮጀክቱ አጠቃላይ ክፍያ 65 በመቶ ይሸፍናል።

በሌላ በኩል የሜቴክ የስራ አፈጻጸም 42 በመቶ ያህል ብቻ መሆኑን ዶክተር አብርሃም አስታውቀዋል።

ክፍያው ላልተሰሩ ስራዎች ብቻ ሳይሆን ገና ይሰራሉ ተብለው ለሚታሰቡት መፈጸሙን አረጋግጠዋል።

በሜቴክ የሚሰራው የኤሌክትሮ ሜካኒካል ስራ ከ30 በመቶ በታች በመሆኑ ስራቸውን እንዳጓተተባቸው የሳሊኒ ኮርፖሬሽን አማካሪ ሚኒስትር ሮበርት ማሪጊኒ ይህ ደግሞ ለተጨማሪ ክፍያ ጥያቄ እንደገፋው ገልጸዋል።

ሳሊኒ የጠየቀው ተጨማሪ ክፍያ 3 ነጥብ 259 ቢሊየን ብርና 338 ሚሊየን ዩሮ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶክተር አብርሃም በላይ አስታውቀዋል።

አለም አቀፍ ስምምነት በመሆኑም ክፍያው የግዴታ እንደሚፈጸም አክለው ገልጸዋል።

ማንም ከሕግ በላይ ስላልሆነ አጥፊዎችን ተጠያቂ እናደርጋለን ያሉት የሜቴክ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ አብዱላዚዝ መሐመድ ለዚህ ብክነት ሃገራዊ ሃላፊነት መውሰድ ግዴታ እንደሆነ አረጋግጠዋል።

 

Related:

ያ ያልነው ቀን ደረሰ መሰለኝ! ‘ለስኳር ኮርፖሬሽን መውደቅ ሜቴክ ትልቅ ድርሻ አለው፣ የስኳር ኮርፖሬሽን የቀድሞ አመራሮች መጠየቅ አለባቸው’ ተባለ – ሪፖርተር እንደዘገበው

 ምዝበራ በየፈርጁ!

TPLF mismanagement renders useless even existing sugar factories, much less Ethiopia becoming exporter as per GTP I & II

ኢንጂነር ስመኘው በቀለን ሕወሃቶች ስለመግደላቸው መረጃ ወጣ!

30 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

በፌስ ቡኳ ጽዮን ብርሃኑ ብዙ መረጃ ማውጣቷ ይነገራል! ቴዲ ማንጁስ ዋናው ገዳይና እነዳንኤል ብርሃኔም በግድያውና በሌሎች ኢትዮጵያን የማናጋት ወንጀሎች እጃቸው እንዳለበት ጽዮን ብርሃኑ መረጃ ያለችውን ጠቃቅሳለች!

እርሷ መረጃውን እንዴት እንዳገኘች ግን የተጠቀሰ ነገር የለም!

 

መከላከያ የኢሕአዴግ የመጨረሻ ምሽግ?

9 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ቢቢሲ አማርኛ

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የመከላከያና የደህንነት አደረጃጀት ህገመንግስቱ ላይ እንደተቀመጠው ባለፉት ሁለት አሰርታት ህዝብን ከማገልገል ይልቅ የወገንተኝነት ፖለቲካ ውስጥ እንደነበሩ ባለፈው ለፓርላማ ንግግር ሲያደርጉ አመላክተው ነበር።

ቀጥሎም የእነዚህ ተቋማት አሰላለፍ ከመንግስትና ከስርዓት ጋር የሚቀያየር ሳይሆን ወገንተኝነታቸው ለህዝብና ለሃገር ይሆን ዘንድ ማሻሻያ እንደሚደረግባቸውም ተገልጿል።

ይህን ተከትሎም የመከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም የነበሩት ጀነራል ሳሞራ የኑስ በጀኔራል ሳአረ መኮንን፤እንደሁም የቀድሞ የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ በጀነራል አደም ሞሃመድ መተካት ሊደረግ የታሰበው ማሻሻያ ጅማሮ ተደርጎ ሊታይ ይችላል።

ማሻሻያ ይደረግ ሲባል ከሚነሱ መሰረታዊ ጥያቄዎች መካከል ላለፉት ሁለት አሰርታት ከወገንተኝነት ፖለቲካ የፀዱ አልነበሩም የተባሉት የመከላከያና ደህንነት ተቋማትን ከዚህ መስመር ማውጣት የሚቻለው በምን አይነት ማሻሻያ ነው? የሚለው ቀዳሚው ነው።

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

 

“መከላከያ የኢህአዴግ የመጨረሻ ምሽግ”

የቀድሞ አየር ሃይል አዛዥ የነበሩት ሜጀር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት ለቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ መከላከያ ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው የሚያትት ደብዳቤ ፅፈው ነበር።የኢህአዴግ የመጨረሻ መደበቂያ ነው የሚሉት መከላከያም ሆነ ደህንነቱ ላይ ማሻሻያ ማድረግ እንደሚያስፈልግ ዛሬም ጥርጥር የላቸውም።

“መከላከያ የመጨረሻው የኢህአዴግ ምሽግ ነው።ፀረ ህገመንግስት የሆነ መመሪያም ነበራቸው” በማለት አንዳንድ የመከላከያ ባለስልጣናትም ፖለቲካ ውስጥ መግባታቸውንም ይጠቅላሉ።

ማሻሻያው መጀመር ያለበት ረዥም ዓመታትን ያስቆጠረውና ምንም እንኳ ጥሩ ነገሮች ቢኖሩትም በርካታ ችግሮች ያሉበት የአገሪቱ የውጭ ግንኙነትና ደህንነት ፖሊሲን ከማሻሻል መጀመር እንዳለበት ያስረዳሉ።

በማንኛውም ዘርፍ የሚደረግ ማሻሻያ ቀላልል እንዳልሆነ ይበልጥ ደግሞ እንደ መከላከያና ደህንነት ያሉ ተቋማት ማሻሻያ ከባድ እንደሚሆን አመልክተዋል።

ሁሌም የለውጥ ሂደት ላይ ለውጥ ደጋፊና ተቃዋሚ እንደሚኖር ሁሉ መከላከያና ደህንነትን በማሻሻል ሂደት ውስም በጥላቻና በዘረኝነት ፀረ ለውጥ ሃይሎች ሊኖሩ እንደሚችሉ ይገምታሉ።

ለዚህ መፍትሄ የሚሉት ለለውጥ ሂደቱ የሚወጡ መመሪያዎችም ይሁኑ ሌሎች አቅጣጫዎች ህገ መንግስቱንና ህገመንግስቱን ብቻ የሚከተሉ መሆናቸውን ማረጋገጥን ነው።

ከሁሉም በላይ አጠቃላይ የማሻሻል ሂደቱ በባለሙያ በቂ ጥናት ተደርጎበት የሚገባበት ለውጥንና የአገሪቱን ወቅታዊ እውነታ ያገናዘበ እርምጃ መሆን እንዳለበትም ያሳስባሉ።

እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ባለ ታዳጊ አገር ባደጉ አገራትም የመከላከያና የደህንነት ተቋማት ሁሌም ወደ አንድ ወገን የማዘንበል ነገር የሚታይባቸው በመሆኑ የትኛውም አይነት ሪፎርም ቢደረግ እነዚህን ተቋማት ሙሉ በሙሉ ከወገንተኝነት እንደማያፀዳቸው ያስረዳሉ።

ቢሆንም ግን በአገሪቱ የህግ የበላይነትን አረጋግጦ በተቻለ መጠን የተቋማቱ ወገንተኝነት ለህዝብ እንዲሆን ማድረግ እንደሚያስፈልግ ያስረግጣሉ።

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________I

_______________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

 

“ለውጥ አልተጀመረም አልተሞከረምም”

በመፈንቅለ መንግስት ሙከራ ተወንጅለው በእስር የነበሩትና በቅርቡ በይቅርታ የተለቀቁት እንዲሁም ማእረጋቸው እንዲመለስ የተወሰነው ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው ፅጌ መከላከያን ስለማሻሻል ሲታሰብ ዋናው ችግር በወረቀት ላይ የሰፈረው ነገር ሳይሆን በተግባር የሚታየው ነው ይላሉ።

ለእሳቸው ይበልጡን ተቋማቱን የሚዘውሩት እነማን ናቸው? የሚለው ጥያቄ ወሳኝ ነው።

እሳቸው እንደሚሉት በወሳኝ ወታደራዊ ተቋማት መዋቅር ላይ የሚቀመጡት ሰዎች በቅርፅ ደረጃ ህገመንግስቱን መሰረት አድርጎ የህዝብና የሃገሪቱን ጥቅም ታሳቢ ያደረጉ ቢመስልም የመጡበት የፖለቲካ መስመር ተፅእኖ ግን በተጨባጭ የሚታይ እንደሆነ ይገልፃሉ።

በደህንነት ተቋማት በኩል ያለው ነገርም ከዚህ ይለያል ብለው አያምኑም።

“የማሻሻያው ጅምር ተደርገው በሚታዩት የቅርብ ጊዜ ሹመቶችም የነበረው ችግር መንፀባረቁን ቀጥሏል” ይላሉ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው።

ከዚህና ከተመሳሳይ ሃሳቦች በመነሳት መከላከያውንና ደህንነቱን የማሻሻል እርምጃ እንዳልተጀመረ ጨርሶም እንዳልተሞከረ ይናገራሉ ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው።

በሌሎች አገራት በመከላከያም ይሁን በደህንነት ሰዎች ሲሾሙ ከብቃትና ለስርአት ታማኝ ከመሆን የበለጡ መስፈርቶች እንደሌሉና በኢትዮጵያ ግን ድጋፍ ሰጭው ሃይል ሳይቀር መዋቅሮች ከአንድ ፓርቲ ከህወሃት በወጡ ሰዎች መሞላታቸውን ይጠቁማሉ።

የአየር ሃይል አዛዥ የነበሩትና የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሆነው የተሾሙት ጀነራል አደም መሃመድን ሹመት እንደማሳያ በመውሰድ ቀጣዩን ብለዋል።

“እሳቸው ተሾሙ ማለት ተቋሙን ከታች እስከ ላይ ይመሩታል ማለት አይደለም።በየደረጃው ያለው መዋቅር የተሞላው በሌላ ሃይልና ፍላጎት ነው።”ይላሉ።

ብርጋዴር ጀነራል አሳምነው እንደሚሉት አማራ ወይም ኦሮሞ ብሎ ሾሞ ከሌላ ብሄር የወጣ መሆኑን ለህዝብ ለማሳየት መሞከር መሬት ላይ ያለውን እውነታ የመሸፈን ተፅእኖ ስላለው እርምጃው አደገኛ ነው።

ከላይ እስከ ታች ብቃትን መሰረት አድርጎ ከሁሉም ህዝቦች የተውጣጣ እኩል ውክልናና ስልጣንን የሚሰጥ አካሄድን መከተል ባለው የአገሪቱ ነባራዊ የፖለቲካ ሁኔታ እሳቸው አዋጭ የሚሉት አካሄድ ነው።

በሲቪል ሰርቪስ ኮሌጅ የሰላምና ደህንት ባለሞያ ሆኑት ዶክተር ጌታቸው ዘሩ ” አሁን እተደረገ ያለው ለውጥ የዛሬ ሳይሆን የቆየ ሂደት ነው ” ይላሉ።

ይሁን እንጂ አሁን ለውጡ ካለፈው ጠንከር ያለ ሊሆን እንደሚችል ይገምታሉ።

እሳቸው እንደሚሉት በፀጥታና ደህንነት ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎች ከሉዓላዊነትም ይሁን ከአገር ውስጥ ፖለቲካ አንፃርም በጥንቃቄ መታይት አለባቸው።በተለይ ደግሞ አካሄዱ አራቱም የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የተነጋገሩበትና የተስማሙበት መሆን ይኖርበታል።

የሚሾሙ ሰዎችም ተቋማቱን የመምራት ብቃት ያላቸው መሆኑን ማረጋገጥ አስፈላጊ ነው።ካልሆነ ግን ውስጣዊ ሽኩቻዎች ተቋማቱ ላይ ተፅእኖ ማድረጋቸው አይቀሬ እንደሚሆን ያስረዳሉ።

ምክንያታቸውን ሲያስቀምጡም “መንግስት የመሰረቱት እነዚህ ድርጅቶች እስከሆኑ ድረስ ስምምነታቸው ወሳኝ ነው” ይላሉ።

 

ተዛማጅ

ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድ ለፓርላማ ያቀረቡት የመጀመሪያው ግልፅና አስገራሚ ሪፖርት!

በኢትዮጵያ እየመጡ ያሉ ለውጦችን ለማደናቀፍ እየተሰሩ ያሉ ሴራዎችን የሚመረምሩ ኮሚቴዎች ሥራ ጀመሩ!

የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በፀዳ መልኩ እንደሚንቀሳቀስ አዲሱ ድሬክተር ጄኔራል አደም መሃመድ አስታወቁ!

የኢትዮጵያን ደኅንነት የማይሹ ‘የቀን ጅቦች’ ግጭት በማናፈስ ላይ መሆናቸውን ዶር ዐቢይ እንደገና ለዜጎች ገለጹ!

ነፃ ያልወጣው ነጻ አውጭ ጄኔራል ጥቅማችን ተቋረጠ በማለት ወያኔ ኢትዮጵያንና በመካሄድ ላይ ያለውን ለውጥ በኃይል ለማዳፈን መዘጋጀቱን ገለጸ! ወይ ወያኔዎች በሕዝብ መተፋታችውን አለመገንዘብ!

4 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“…ያለው ሁኔታ ከ[ዐ]ብይ ጋር የተገናኘ እንደሆነ ሳይሆን እናይ በመሰረቱ ማየት ያለብን እንደጠላት ሃይል አድርገን ነው። እንደጠላት ሃይል አድርገን ካልወሰድነው እንዴት አምርረን እንደምንወጋውም ግልፅ ሊሆንልን አይችልም። ስለዝህ ሄዶ ሄዶ ከኢህአዴግ ውስጥ ተነስቶ እየበሰበሰ ራሱን እየበላ የኢህአዴግም ፕሮግራም ጭምር እየበላ በልቶ በልቶ ከጨረሰ ብሁዋላ በመጨረሻ በስልጣን ላይ የወጣው ሃይል ከኢህአዴግ ፕሮግራም ጋር የሚገናኝ ትንሽ የኢህአዴግ ሽታ እንኩዋን የለውም። ለእኔ ይህ የጠላት ሃይል ነው። እንደጠላት ሃይል እንውሰደው። አሁን የኢህአዴግ ሽታ የለውም ማለት ይህ ሃይል ህዝባዊ ሽታ ያለው አይደለም ማለት ነው። ከህዝባዊነት የወጣ ስላልሆነ ሄዶ ሄዶም የጊዜ ጉዳይ ካልሆነ ለፌደራላዊ ስርአታችን ሊያጠፋ የሚችል አካሄድ እየሄደ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው።” Continue reading

ለ17-ዓመት ‘የትግራይ ነጻነት’ ጦርነት ሕወሃት የኢትዮጵያን ሕዝብ ካሣ አስከፍላለሁ ይላል! ሌላው ጦር ግንባር!

19 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 
አዲሱ የሕወሃት ተሿሚ ገታቸው ረዳ የተባለው የስብሃት ነጋ ‘የፖለቲካ ክርስትና ልጅ’ ሰሞኑን ከሕወሃትዎች ሰባተኛው ዙር ጸረ-ኢትይዮጵያ የመቀሌ ዱለታቸው ብቅ ብሎ፡ ከላይ የተጠቀሰውን ሃሣብ መፈንጠቁ፣ ሕዝቡ ብዙ ትኩረት ባይሠጠውም ከሰሞኑ የሕዝቡ ግርምቶች አንዱ ነበር።

ወንበዴውና ዘወትር ሃሣቡ ከፍተኛ የዝቅተኝነት ስሜት ከሚንጸባረቅበት ከወንበዴው ሕወሃት ነውና ማንም አላሳሳበም ወይንም ማስደንገጡ አልተሰማም!
Continue reading

‘We fear for our lives’: how rumours over sugar saw Ethiopian troops kill

8 Nov

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Tom Gardner in Ambo, The Guardian
 
It began with a rumour. On 25 October, residents of Ambo, 120km west of the Ethiopian capital, Addis Ababa, heard word on social media that a shipment of smuggled sugar was due to pass through town.

“Sugar is so expensive now, the price has tripled,” explains 18-year-old Israel, a first-year undergraduate at Ambo University. “And they’re exporting it to other parts of the country but the people here don’t have any. It’s not fair.”
Continue reading

የሽፍታ/ወንበዴ መንግሥት በኢትዮጵያ!

25 Oct

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

Related:

    የሽፍታ/ወንበዴ መንግሥት በኢትዮጵያ

    ኢትዮጵያ ወደአደገኛ አግጣጫ እያመራች ነው

 

%d bloggers like this: