Tag Archives: tplf murders

አብዲ ዒሌ በሶማሌ ክልል ለተፈጸሙ የመብት ጥሰቶች፡ ዘረፋዎችና ግድያዎች ሕዝቡን ይቅርታ ጠየቀ!

12 Jul

የእዘጋጁ አስተያየት፡

ለዚህ ነፍሰ ገዳይ ባላቸው ቀረቤታ ምክንያት የሕወሃት ሰዎች ዜናው እንኳ እንዲጻፍ ያደረጉት፣

“የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል መንግስት ለተፈፀሙ ስህተቶች ኃላፊነት በመውሰድ የክልሉን ህዝብ ይቅርታ ጠየቀ!” በማለት ነው!

ከመቼ ወዲህ ነው ስው መግደል ወደ ስህተት ደረጃ የወረደው? በየቀኑ አይደል እንዴ የሕወሃት ገጾች ‘ታላቅ መሪ’ እያሉ ለዚህ የሰብዓዊ መብቶች ነቀርሳ ሲስገዱ የኖሩት?

ኦሮሞችና ሶማሌ ዜጎቻችን ግጭት ላይ በነበሩበትና አንድ ሚሊዮን ዜጎቻችን በተፈናቀሉበት ወቅት አይደል እንዴ በአሜሪካን ሃገር የሚኖሩ የሕወሃት ‘ተጋሩ አባላት’ ድጋፋቸውን ለአብዲ ዒሌ የሠጡት?

የሰው ዘር በማጥፋት ወንጀል — እንደ ሕወሃቶች — አብዲ ዒሌ አንድ ቀን ለፍርድ መቅረብ እንጂ ስለምን ይቅርታ ነው የሚቀባጥረው?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Abdi pleading for forgiveness of Somalis in particular and Ethiopians in general. Is destroying thousands of lives a matter of simple errors and mistakes? Don’t give international human rights law, Ethiopians and the international human rights community this TPLF political shenanigan!

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 5፣ 2010 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ርእሰ መስተዳድር አቶ አብዲ መሀሙድ በህዝቡ ላይ ለተፈፀሙ ስህተቶች የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ ኃላፊነት እንደሚወስዱ በመግለፅ የክልሉን ህዝብ በይፋ ይቅርታ ጠየ

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ አብዲ መሀሙድ ኡመር ይህንን ያሉት ትናንት በተጀመረው የኢትዮጵያ ሶማሌ ክልል ምክር ቤት መደበኛ ጉባኤ ላይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባለፉት አንድ መቶ ቀናት ያስመዘገቡትን ስኬት ለምክር ቤቱ አባላት ባብራሩበት ወቅት ነው።

ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በኢትዮጵያ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢሶዴፓ) ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ደረጃ የጠቅላይ ሚኒስቴሩን የይቅርታ፣ የፍቅርና የመደመር መርህ ከግብ ለማድረስ የበኩላቸውን ለመወጣት በስፋት ውይይት ተደርጓል፡፡

“በዚህም የክልሉ መንግስትና ገዥው ፓርቲ ኢሶዴፓ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአጭር ጊዜ ውስጥ ላከናወኗቸው ሥራዎች ትልቅ ክብር አለን፤ መደመርን መርጠናል” ብለዋል አቶ አብዲ።

ርዕሰ መስተዳደሩ በምክር ቤት ንግግራቸው አክለው እንደገለጹት፥ የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ የህዝቡን ሰላም ለማረጋገጥና የኑሮ ደረጃ ለማሻሻል አበክረው ይሰራሉ።

ቀደም ሲል በህዝቡ ላይ ለተፈፀሙ ስህተቶች የክልሉ መንግስትና መሪ ድርጅቱ ኃላፊነት እንደሚወስዱ ገልፀው ህዝቡን በይፋ ይቅርታ ጠይቀዋል፡፡

”ሥራ ሲሰራ ስህተቶች ይኖራሉ፤ ነገር ግን በጎ ተግባራትን ማጎልበት እንዲሁም ለተፈጠሩ ስህተቶች በይፋ ይቅርታ መጠየቅ መልካም ባህል በመሆኑ ሁላችንም ማዳበር ይኖርብናል’’ ብለዋል፡፡

አቶ አብዲ አክለውም፥ ቀደም ሲል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሽብርተኝነት ተፈርጆ የነበረው ኦብነግ ከመንግስት የተሰጠውን እድል በመጠቀም ወደሰላማዊ የፖለቲካ እንቅስቃሴ ውስጥ እንዲገባም ጠይቀዋል።

በተለይ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይን የይቅርታና የፍቅር መንገድ ጥሪ የግንባሩ መሪዎች አክብረው በመቀበል እድሉን እንዲጠቀሙበት ነው ጥሪ ያቀረቡት።

የግንባሩ አመራሮች ለዓመታት የያዙትን ጥላቻ በማስወገድ ለቀረበላቸው የሰላም ጥሪ አወንታዊ ምላሽ በመስጠት በአገሪቱና በክልሉ የተጀመሩ የፍቅር፣ የአንድነትና የመደመር መርህ አካል እንዲሆኑ ጠይቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤቱ ጉባኤ በዛሬው እለትም ቀጥሎ በመካሄድ ላይ ይገኛል።

 

ተዛማጅ:

Sat image of Jail Ogaden

Video: Torture in Somali Region Prison in Ethiopia

“We are Like the Dead”

Interview: Years of Untold Suffering at Jail Ogaden

Torture and Ethiopia’s Culture of Impunity

Ethiopia: Torture in Somali Region Prison

 

Optimists hoping for peace in Ethiopia with TPLF have hardly thought through the nature of today’s problems of our country. US also needs to cleanse its name & image alliance with TPLF murders has spoiled

13 Sep

By Keffyalew Gebremedhin The Ethiopia Observatory (TEO)
 

The Tigray People’s Liberation Front (TPLF) is habitually dishonest and a mafia group in power in Ethiopia.

After the cruelties it has perpetrated especially during the past two years, things have gotten worse all the more. In view of this I have chosen to sink in my head and see if anything better could emerge next for this unfortunate country. I am convinced that the biggest success for Ethiopia is not only what comes next; it is whether Ethiopians could succeed in completely removing the roots and branches of the TPLF mafiosi from power and for good!
Continue reading

*LA COSA NEGA*: የሕወሃት ሥርና ምሶሶ ምንድ ነው? መላው የትግራይ ሕዝብ ወይንስ መሠረቱ ኤርትራዊ የሆነ በደም፣ ጋብቻና ጥቅም የተሳሰረ አንድ ትግራዊ ‘የማፍያ’ ቤተሰብ?

24 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)


Credit: Ethiomedia
ስብሃት ነጋ ለአሜሪካ ድምጽ ራድዮ የሰጠው ገላጩ ቃለ መጠይቅ


ማነው ስብሃት ነጋ?

ክፍል አንድ


ክፍል ሁለት


የሕወሃት ሰዎች መሬት፡ ደንና ከርሰ ምድር ላይ ብቻ ሳይሆን ያተኮሩት የሃገራችን የእህል ማከማቻ ሳይሎ ላይ ጭምር ነው! ለሌሎች ተከልክሎ የተከስተ ስብሃት ነጋ ሳይሎቻንን መከራየት!
 
*Updated.
 

%d bloggers like this: