Tag Archives: TPLF strategy

“የሕወሃት ታጋዮች ማኅበር”፡                  1,700 አባላት በአዲስ አበባ፣ ከ800 በላይ ጭፍጨፋ በሚካሄድባት ወልድያና አካባቢዋ፣ 800 በቤኒሻንጉል ወዘተ! የእያንዳንዱ ዜጋ ነገ በሕወሃት እየተገደበ ነው!

23 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

እጅግ የሚያስደነግጥ፤ እጅግ የሚያሳስብ ከማንም ሕዋሃታዊ-ትግራይ ግለሰብ ውጭ ሌላውን የማመን ስውነትን የሚገፍ መረጃ ነው!

ከወልድያ ጭፍጨፋ ወዲህ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ አመኔታ ስላጣ በሃገራችን አደጋው በየአቅጣጫው ሊባባስ ይችላል! እንደተለመደው፡ ሕወሃቶች ክህደቶቻቸውንና ትግራዊ ያልሆኑትን ዜጎቻችንን የችግሩ ምንጮች በማድረግ ወደማሣጣቱ ይዞራሉ! ሞኞች ሊያምኗቸው ይቻኮሉ ይሆናል!

በሃገራችን በዘር መከፋፈሉ እየተባባሰ ስለመጣና፡ ሕወሃት ደግሞ በየአካባቢው ገዥያችሁ ነኝ ብሎ በማሰብ ከቀን ቀን እያባባሰ የመጣው የረገጣውና ጭፍጨፋው ጥግ ስለደረሰ፡ ወልዲያ እንደታየው ራሱን የመከላከል እርምጃ ወስዷል። ወደፊትም ይወስዳል! ሕዝቡ ውስጥ ተሰግስገው፡ የሚያሰጨፈጭፉትን ከእንግዲህ እንዳላየ ሆኖ ባለማስተናገድ ራሱን ወደመከላከል ያሳድጋል።
Continue reading

‘ለወያኔ እድሜ ማራዘሚያ በተዘጋጀ መድረክ ተቀዋሚዎች ምን ይሰራሉ?’ የሚለው የአቶ ይገረም ዓለሙ ጥብቅና አልተመቸኝም!

24 Oct

በከፍያለው ገብረመድኅን The Ethiopia Observatory (TEO)
 

ከላይ በተጠቀስው ርዕስ ጥቅምት 23 ቀን 2016 አቶ ይገረም ዓለሙ በኢትዮሚዲያ ፎረም ላይ ፋና ብሮድካስት በአዲስ አበባ ስላዘጋጀው ስብሰባ የፖለቲካውን ጽዩፍነታቸውን የዘገቡበት ጽሁፍ ስላልተመቸኝ፣ ስለፖለቲካችን አያያዝና ሂደት ትንሽ እንዳስብ አድርገውኛልና ከልብ አመስግናቸዋለሁ።
Continue reading

የሕወሃት ስትራቴጂ ሕዝባዊ አመጹን ለማኮላሸት ‘የፕሮፓጋንዳ’ ሥራ እንዲሠራ በመወሰኑ ከፋፋይ ወሬዎችን በተከታታይ ማሠራጨት ዋነኛው ተግባሩ ይሆናል

18 Dec

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ሚኒስትር ጌታቸው ረዳ ለመንግሥት መገናኝ ሠራተኞች ያስተላለፈው መመሪያ

    * የማስተር ፕላኑ ላይ የተነሳው ጥያቄ ሕጋዊ መሆኑን፡ ነገር ግን ከኋላው አፍራሽ ኃይሎች ያደረጉትን ‘የጸረ-ሰላም ኃይሎችን’ ሚና ማጋለጥ

    * ሕዝቡ አመጹን አቁሞ ወደቤቱ ነው የሚል ዜና በተደጋጋሚ ማሰማት

    * የሟችና የቆሰሉትን ቁጥር ላይ ትኩረት በመስጠት አለማስተባበል

    * ሕዝብን በብሔረሰብን ማጋጨት የሚሉት ይገኙበታል።

ሙሉ ዓላማቸውን ለማወቅ ከኢሣት የተገኘውን ኦዲዮ ያዳምጡ


 

ሕወሃት የመለስ ዜናዊን ፍላጎት ተግባራዊ ለማድረግ ዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂን (GMO) ተግባራዊ ማድረግ ጀመረ፤ በዘር ንግዱ ከፍተኛ ድርሻውን ያዘ

24 Nov

የአዘጋጁ ማስታወሻ፡

አፋጥኑት የኢትዮጵያን በምግብ ራስን መቻል ዋስትና ምርጫው ከመደረሱ በፊት ሳይሆን አይቀርም ግፊቱ!

አቶ ኃይለማርያም ሳይንሱንም ቀድመው መጀመሪያ በጥቅምት 2013 ስንዴን አስመልክተው ከአርሲ አፍሪካን እንመግባለን ሲሉ ነበር። ከዚያ ሕወሃት የኢትዮጵያን ሠራዊት ድል ያደረገበትን ሚያዝያ 28 2014 ሲያስከብሩ በአዲስ አበባ ስታድዮም በምግብ ራሳቸንን ችለናል ብለው የሳይንሱን ማራቶን አቸንፈው ነበር! ያኔም አውቀነው ነበር፤ ዛሬም ምሥጢር አልሆነብንም!

ይህ ግን በቂ የሠለጠነ የሰው ኃይልና ሣይንሳዊ መከላከያ የሌላትን ድሃ ሃገር ምን ላይ ይጥላት ይሆን? እነ ሕንድ ከጥጥ ውጭ ያልደፈሩትን፡ ምነው የኢትዮጵያን ባልሥልጣኖች ታላላቅ የአሜሪካና የአውሮፓ ዘር አብቃይ ኮርፖሬሽንና የአሜሪካን አስተዳደር ለማስደሰት ሲሉ ጀብደኞች አደረጋቸው? የአካባቢያችን አየር በአበባዎች ምርት ኬሚካሎችና በጨርቃ ጨርቅ ፋብሪካዎች ዙሪያ ባሉት ወንዞች መበከሉ ሳያንስ፡ አሁን ደግሞ ዕውቅ የተፈጥሮ ሃብታችንን ልናጣ አይደለምን?

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አዲስ አበባ ህዳር 15/2007 (ኢዜአ) የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በዘንድሮው ዓመት በሽታን የሚቋቋሙና የተሻለ ምርት የሚሰጡ ከ30 በላይ የተሻሻሉ የሰብል ዝርያዎች ማውጣቱን አስታወቀ። ኢንስቲትዩቱ በኢትዮጵያ የዘረመል ምህንድስና ቴክኖሎጂን ለመጀመር የፖሊሲ ክለሳና ማሻሻል ሥራ እያከናወነ መሆኑን ገልጿል።
Continue reading

%d bloggers like this: