Tag Archives: Washington. D.C.

የህዳሴ ግድብ ተደራዳሪዎች ጫና እንደነበረባቸው በውይይት መድረክ ላይ ገለጹ

20 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

የህዳሴ ግድብ የውኃ አሞላልና አለቃቀቅን በተመለከተ እየተደረገ በሚገኘው ድርድር ጫና እንደ ደረሰባቸው ኢትዮጵያን ወክለው የሚደራደሩት የሕግና የቴክኒክ ባለሙያዎች፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በበተደረገ የውይይት መድረክ ላይ ገለጹ።

ሰኞ የካቲት 9 ቀን 2012 ዓ.ም. በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አዳራሽ በተካሄደው የውይይት መድረክ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባላት፣ በአሜሪካና በዓለም ባንክ አመቻችነት የህዳሴ ግድቡን የውኃ አሞላል አስመልክቶ እየተካሄደ የሚገኘው ድርድር፣ ኢትዮጵያን የሚጠቅም ሂደት ነው ብለው እንደማያምኑ መናገራቸውን የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል።

ውይይቱን እንዲከታተሉ የተወሰኑ የመንግሥት የመገናኛ ብዙኃን ብቻ ተጠርተው የነበረ ቢሆንም፣ ውይይቱ ከተጀመረ በኋላ የውይይቱን ይዘቶች እንዳያስተላልፉ መመርያ እንደተሰጣቸው ተሰምቷል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የውይይት መድረኩን ከከፈቱ በኋላ ጥሪ እንደ ተደረገላቸው ሌሎች ተሳታፊዎች በታዳሚነት የተከታተሉ መሆኑን የገለጹት ምንጮች፣ መድረኩ ከተከፈተ በኋላም የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ በቀለ (ዶ/ር) ሁለት ሰዓት የፈጁ የድርድሩን ሂደትና ይዘት የተመለከቱ የቴክኒክና የሕግ ጉዳዮች ላይ ገለጻ ማድረጋቸውን ምንጮች ለሪፖርተር ጠቁመዋል። ሚኒስትሩ ገለጻቸውን ካጠናቀቁ በኋላ የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን አባላት አስተያየት እንዲሰጡ መጋበዛቸውን፣ የድርድሩ ሂደትም በአሜሪካ መንግሥት በተወከሉ ታዛቢዎች ጫና ይደረግባቸው እንደነበር ይፋ ማድረጋቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

የአሜሪካ መንግሥትን ወክለው ድርድሩን የሚታዘቡ ኃላፊዎች በተለያዩ አጋጣሚዎች፣ ‹‹ኮንሲኩዌንስ (ችግር) ያመጣባችኋል›› በማለት በኢትዮጵያ ቡድን አባላት ላይ ጫና ያደርጉ እንደነበር፣ በግልጽ ለመድረኩ መናገራቸውን ምንጮች አስረድተዋል።

በዚህና መሰል ጉዳዮች ምክንያትም የግብፅ ተደራዳሪዎች የዐባይ ውኃን በተመለከተ፣ ግብፅ ዳግም የበላይነት መቆጣጠር እንዳለባት የሚያመላክቱ አቋሞችን ያራምዱ እንደነበር፣ ተደራዳሪዎቹ ለመድረኩ እንዳስረዱ ከምንጮቹ ገለጻ ለመረዳት ተችሏል።

በግብፅና በኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች መካከል መጥበብ ያልቻሉ የልዩነት ነጥቦች ናቸው ያሏቸውን ለመድረኩ ያቀረቡ ሲሆን፣ ኢትዮጵያ ወደ ዳሴ ግድቡ የሚመጣውን የጥቁር ዐባይ የውኃ መጠን መሠረት ያደረጉ ነጥቦችን ስታነሳ፣ የግብፅ ተደራዳሪዎች ግን የጥቁር ባይ አጠቃላይ የተፈጥሮ ፍሰትን የድርደሩ መሠረት በማድረግ የግድቡ አሞላል እንዲወሰን መጠየቃቸውን፣ የኢትዮጵያ ተደራዳሪዎች በዋነኝነት ማንሳታቸውን ከምንጮች ለመረዳት ተችሏል።

በዚህም ምክንያት እየተደረገ ያለው ድርድር ኢትዮጵያን የሚጠቅም ደት ነው ብለው እንደማያምኑ ለመድረኩ እንዳስታወቁ ምንጮቹ አስረድተዋል። የውይይት መድረኩ ለግማሽ ቀን ብቻ የተያዘ በመሆኑ ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው ምሁራን፣ ሚኒስትሮችና ታዋቂ ሰዎች ጥያቄዎችን እንዳላነሱ ነገር ግን ውይይቱ ከቀናት በኋላ በዝርዝር ጉዳዮች ላይ በስፋት እንዲቀጥል መወሰኑን ገልጸዋል።

የው፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ስለሺ (ዶ/ር) ከሳምንት በፊት ሰጥተውት በነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በድርድሩ ጫና ተሰምቷቸው እንደሆነ ቀርቦላቸው ለነበረ ጥያቄ፣ ‹‹አዎ፣ ጫናዎች መኖራቸው አይቀርም። ጫናዎች በእኛ ተደራዳሪዎች ላይ ነበሩ፣ በሌሎች አገሮች ተደራዳሪዎች ላይም ነበሩ፤›› የሚል ምላሽ ሰጥተው ነበር።

ለሥራ ጉብኝት ወደ ኢትዮጵያ የመጡት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር  ማይክ ፖምፒዮ ከኢትዮጵያ አቻቸው አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ጋር በመሆን ማክሰኞ የካቲት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ፣ የዳሴ ግድብ ድርድርን በተመለከተ አገራቸው ጣልቃ እንደማትገባና ሦስቱም ተደራዳሪ አገሮች ልዩነቶቻቸውን በራሳቸው መንገድ እንዲፈቱ እንደምትፈልግ ገልጸዋል።

/ሪፖርተር

 

 

ስለ ድርድሩ፣ ከተደራዳሪዎቹ ባሻገር—ዋዜማ ራዲዮ

19 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

በመስፍን ነጋሽ [ከዋዜማ ራዲዮ]

ኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብጽ በሕዳሴ ግድብ የውሃ አሞላል ላይ ለመነጋገር የጀመሩት ድርድር ወደ መቋጫው እየደረሰ ይመስላል። ድርድሩ ሳይቋጭ ቢቀር የሚመኙ ኢትዮጵያውያን ቁጥር ጥቂት ባይሆንም፣ ያለንበት ሁኔታ ድርድርን አንጠልጥሎ ለመተው የሚያስችለን አይመስልም። የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አዲሳባ የመጡትም “ድርድሩን ቋጩ” ብለው ጫና ለማሳደር ነው። እንዲያውም አሜሪካና የዓለም ባንክ ያዘጋጁትን የስምምነቱን “የመጨረሻ” ረቂቅ ይዘው መጥተዋል። ይህን ጽሑፍ ባሰፈርኩበት ምሽት፣ አዲሳባ ላይ፣ የኢትዮጵያ ቁልፍ ተደራዳሪዎች የአሜሪካው ልዑክ ይዞት የመጣውን የስምምነት ሰነድ በግራ መጋባትና በእልህ ሲመረምሩና ሲመክሩ ነበር።

በቅርብ ሳምንታት በዋዜማ ሬዲዮ እና በሌሎችም በኩል በአዲሳባ፣ በካይሮ፣ በካርቱም እና በዋሺንግተን ዲሲ ሲካሄዱ የሰነበቱትን ድርድሮች በማስመልከት የወጡት ዘገባዎች ሂደቱ ውስብስብ መሆኑን የሚያስጠነቅቁ ነበሩ። ዘገባዎቹ የድርድሩን ውጤት በዋናነት የሚቀርጹት በጠረጴዛ ዙሪያ የተሰበሰቡ ባለሞያዎች እውቀትና አርበኝነት ሳይሆኑ (ሀ) የኢትዮጵያ እና የግብጽ ውስጣዊ ሁኔታ፣ (ለ) ቀጣናዊ የፖለቲካና የዲፕሎማሲ አሰላለፎች እና (ሐ) ወቅታዊ ዓለም አቀፍ አጀንዳዎች የሚቀርጹት ቁመናች መሆናቸውን ደጋግመው ያስታውሳሉ። ሆኖም ተደራዳሪዎቹን እና ጠቅላይ ሚኒስትሩን በአርበኝነት ስሜት ወይም/እና በእውቀት መጉደል የሚጠረጥሩ፣ የሚወቅሱ፣ የሚከሱ ድምጾች ሞልተዋል።

Continue reading

“…ኢትዮጵያ እንዲህ ያለ ዲፕሎማሲያዊ ፈተና ገጥሟት አያውቅም”—በዋሽንግቶን በዐባይ ጉዳይ አንድ ኢትዮጵያዊ ተደራዳሪ

15 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ዋዜማ ራዲዮ– ውጥረትና ውዝግብ የበረታበትና የመጨረሻ ነው የተባለው የህዳሴው ግድብ የውሀ አያያዝና አለቃቀቅ ድርድር በሱዳን በኢትዮጵያና ግብፅ የውሀ ሚንስትሮች መካከል ረቡዕና ሐሙስ በዋሽንግተን ሲካሄድ ቆይቶ በሚቀጥሉት ሳምንታት በመሪዎች ደረጃ ስምምነት ለመፈራረም የሚያስፈልጉ ዝግጅቶችን ለማድረግ እቅድ በማውጣት ተበትኗል።

ዋዜማ ያገኘችው መረጃ እንዳመለከተው ከፍተኛ የአሜሪካ መንግስት ሹማምንት ባለቀ ሰዓት ተደራዳሪዎችን ለማግባባት ቢሞክሩም በግብፅ በኩል በተነሱና የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት የሚዳፈሩ ፍላጎቶች ሳቢያ ድርድሩ ወደተፈለገው ስምምነት አልደረሰም።

የአሜሪካ መንግስት ምንጮች እንደሚሉት በቀሪ ጉዳዮች ላይ አጭር የባለሙያዎች የማጠቃለያ ምክክር ተደርጎ ከዚያም በመሪዎች ደረጃ ስምምነት ለማፈራረም ዋሽንግተን ዝግጅት ታደርጋለች። ይህን እውን ለማድረግም የአሜሪካ የውጪ ጉዳይ ሚንስትር ማይክ ፓምፒዮ በቀጣይ ቀናት የአዲስ አበባ ጉብኝታቸው ጠቅላይ ሚንስትር አብይ አህመድን በተዘጋጀ ረቂቅ ሰነድ ላይ እንደሚያነጋግሯቸው ስምተናል።

Continue reading

ሥጋት ያጠላበት የህዳሴ ግድብ ድርድር ወደ መቋጫው እየደረሰ ነው

10 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

 

“የኢትዮጵያን ጥቅም የሚነካ አንድም ቃል ከተካተተ ስምምነቱ አይፈረምም” —ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)

 

ስለሺ በቀለ (ዶ/ር)፣ የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር (ሪፖርተር)

 

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮጵያን ጥቅም አሳልፎ ሊሰጥ ይችላል ተብሎ የበርካቶች ሥጋት የሆነው በኢትዮጵያ፣ በግብፅና በሱዳን የታላቁን የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ለስምንት ዓመታት ሲካሄድ የቆየው ድርድር፣ በውሃ አሞላልና አለቃቀቅ ጉዳዮች ላይ ስምምነት ለማድረግ ወደ መቋጫው እየተቃረበ ነው፡፡

Continue reading

Egypt, Ethiopia, Sudan to sign final agreement on GERD by end of February—Ahram report

1 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

In a separate statement, Egypt’s foreign ministry said following the conclusion of the four-day talks in Washington that the “American side has prepared a document for an agreement on the three above-mentioned issues; [where] only Egypt signed the document at the end of the meeting.”

It remains unclear which of the two other countries abstained from the signing of the US-prepared document.

Egypt, Ethiopia and Sudan will meet again in Washington on 12-13 February to approve the final version of the agreement in preparation for signing it by the end of February

(Ahram Cairo) Egypt, Ethiopia and Sudan are set to sign a final agreement by the end of February on Addis Ababa’s Grand Ethiopian Renaissance Dam (GERD), a joint statement by the three countries, the United States and the World Bank read late Friday, hoping to secure an agreement which has stirred months of conflict and a deadlock in talks.

The ministers of foreign affairs and water resources of the three countries agreed on a schedule for the filling plan; a mitigation mechanism for the filling of the GERD during drought, prolonged drought, and prolonged periods of dry years; and a mitigation mechanism for the annual and long-term operation of the GERD in drought, prolonged drought, and prolonged periods of dry years.

Continue reading

በሕዋታዊ አሠራር የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች ወደ ቤተሰቦች መጠቃቀሚያነት መሸጋገር የዲፕሎማሲን ሥራና ከበሬታ አሽቀንጥሮ መጣሉ ቅሬታዎችን አበራከተ! የኢትዮጵያ በዘፈቀደ የማይገሠሡ ሃብቶቿ፡ክብርና ጥቅሞች የቶቹ ይሆኑ? የዓሣ ግማቱ…

23 Nov

የአዘጋጁ አስተያየት፦

    በጣም በተወሰነ ደረጃ፣ ይህ አሠራር ተቀባይነት ሊኖረው ቢገባም፣ የዚህ ዐይነቱ ውሱን አሠራር መለኪያው — ከሁለቱ የአንዱ፣ ማለትም የባል ወይንም የሚስት — ሙያ ተፈላጊነት ብቻ ሊሆን በተገባ ነበር!

    Ambassador Tirfu Kidanemariam Gebrehiwet (Eth Embassy)

    ሃገሪቷ የሕወሃቶች መፈንጫ በመሆኗ፡ በ2015 ሕወሃት ራሱ ወ/ሮ ትርፉ ኪዳነማርያምን — የሕወሃት ሊቀመንበር ዐባይ ወልዱን ባለቤት የሚጥልበት ቦታ ሲያጣ — ግንባሩ በድምጽ ብልጫ ፖሊትቢሮም ሆነ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በመንፈጉ — ያላንዳች ሙያና ብቃት አውስትራሊያና ኒውዚላንድ አምባሳደር አድርጎ መሾሙ፣ የዲፕሎማሲ ባለሙያዎችን ማስገረሙ ብቻ ሣይሆን፣ አምባሳደሯ በተራ ካድሬነትና የትግራይ ጸረ-ሙስና አመራር ሆነው ከመሥራት ውጭ ምንም ስለሌላቸው፣ በስብሰባ ላይ ከስድብ ውጭ የሚያውቁት ባለመኖሩ፣ ግለሰቧ ከኮሚኒቲው እንዳይገናኙ ውሱን ሆነው መቀመጣቸው — የቴድሮስ አድሃኖም መፍትሄ — ለሥራው ያላቸውን አላስፈላጊነት ገሃድ ካደረገው ከሁለት ዓመታት በላይ ተቆጥረዋል!
    Continue reading

Prof. Berhanu Nega in Washington D.C. on business – perhaps talking with Americans; he comments on AG7’s latest Arba Minch operations

15 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Regarding the recent military engagement between the TPLF regime and Arbengoch Ginbot 7 (AG7) forces, in its article of May 14, 2016 TEO questioned validity of the regime’s statement about its A – Z knowledge and whereabouts the of ‘Eritrea-recruitd-and-disptached’ destabilization force from its inception in Asmara to its arming, flight to Uganda, to its return by car to Kenya and then its entry into southern Ethiopia on land.
Continue reading

ከእንግዲህ ሕወሃትን ለማንኮታኮት አምስት ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረግ የወደፊቱ ትግል ምን እንደሚመስል ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ከአርበኞች ግንቦት7 ዕይታ አንጻር አቅጣጫ አመላከተ

1 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

78.28 ደቂቃዎች በፈጀ ንግግር የአርበኞች ግንቦት7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ትኩረት በሳበ ንግግር እሁድ ጥር 31/2016 ድርጅቱ ባለበት ደረጃ “በተለያዩ መስኮች በሁለንተናዊ መልኩ መታገል የሚችል ጠንካራ ዘመናዊ ደርጅት መገንባት ችለናል!” ማለቱ አዳራሹን በጭብጨባ አድምቆታል።
Continue reading

%d bloggers like this: