Tag Archives: wazema radio

ሁለቱን የኢትዮጵያ የጭነት መርከቦች ማን ሠወራቸው? የት? በምሥጢር ሸጣቸውስ?—ከሕወሃቱ ሜቴክ ሌላ ማን ይሆናል?

21 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

ዋዜማ ራዲዮ– የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) በርካታ የግንባታ ፕሮጀክቶችን በማዘግየትና በምዝበራ ስሙ ተደጋግሞ ሲነሳ ስምታችኋል። ሌላ ያልሰማችሁትን የሜቴክ ረጅም እጅ ከሀገር ውጪ ጭምር ህገ ወጥ ተግባር የተፈፀመበትን ጉዳይ እንነግራችኋለን። ሜቴክ ሁለት የኢትዮጵያ ግዙፍ መርከቦችን ከብዙ ኪሳራ ጋር ህገ ወጥ በሆነ መንገድ ሽጧቸዋል።

በወቅቱ የዘራፊው ሜቴክ ኃላፊ፣ ዝርፍያ አቀነባባሪና አከፋፋይ የሕወሃቱ ጄኔራል ክንፈ ዳኘው

ነገሩ ከዛሬ ስድስት አመት በፊት በአውሮፓውያኑ 2012 በሀበሻ አቆጣጠር ይጀምራል። በወቅቱ የቀድሞው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ ድርጅት የአሁኑ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ድርጅት በባለቤትነት ሲያንቀሳቅሳቸው ከነበሩ መርከቦች መካከል አብዮትና አባይ ወንዝ የሚባሉት መርከቦች ከ27 አመት በላይ የሆናቸውና ያረጁ በመሆናቸው እንዲወገዱ ይወሰናል።ሁለቱ መርከቦች እያንዳንዳቸው 10 ሺህ ቶን የመጫን አቅም ያላቸው ናቸው።በእርጅና ምክንያት እንዲወገዱ ሲወሰንም የብረታብረት ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ሜቴክ ብረታቸውን አቅልጬ ልጠቀም በሚል መርከቦቹን ይገዛቸዋል።

አግባብነት የሌለው አሰራሩ የጀመረው እዚህ ጋር ነው።ሜቴክ መርከቦቹን የገዛበት መንገድ ግልጽ ያልሆነና ሌሎች ብረት ፈላጊዎችን አግላይ ነበር።በወቅቱ አብዮትና አባይ ወንዝ የተሰኙት መርከቦች ለሜቴክ እንዲሸጡ የወቅቱ የመርከብ ድርጅቱ የቦርድ ሊቀመንበርና የቀድሞ የከተማ ልማትና ቤቶች ሚኒስትር መኩሪያ ሀይሌ : የቦርድ አባሉ አምባሳደር ዶክተር አዲሳለም ባሌማ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበራቸው ዋዜማ ራዲዮ ተረድታለች።

ሜቴክ ብረቱን አቅልጬ ለሌላ አገልግሎት እጠቀምባቸዋለሁ ያላቸውን መርከቦች ለታሰበው አላማ አላዋላቸውም።በመጀመርያ መርከቦቹ ለስምንት ወራት በጅቡቲ ወደብ ቆመው ነበር።ለዚህም በቀን ለእያንዳንዳቸው 4000 የአሜሪካን ዶላር የወደብ ኪራይ ይከፈል ነበር።የሚገርመው በዚህ ጊዜ መርከቦቹ በሜቴክ ይገዙ እንጂ የኪራዩ ወጭ የተሸፈነው በባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት ነበር።ከዚህ ሁሉ ህገ ወጥ ድርጊት በሁዋላም ሜቴክ መርከቦቹን እንዳለው ብረታቸውን አቅልጦ ከመጠቀም ይልቅ የተባበሩት ኤምሬቶች :ዱባይ: ወስዶ ያሳድሳቸዋል። ሜቴክ ለሁለቱ መርከቦች ግዥና ጥገና በጥቅሉ 10 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር አውጥቷል።የመርከቦቹንም ዋጋ ለንግድ መርከብ ድርጅቱ መክፈሉን አውቀናል።

ነገር ግን በኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ስሪት ባልታየ ሁኔታ ለመጀመርያ ጊዜ በሚባል ሁኔታ ሜቴክ መርከቦችን የማንቀሳቀስ ፍቃድ ሳይኖረው በአለም አቀፍ የውሀ አካላት ላይ የመርከብ ባለቤት ሆኖ ነበር። በኢትዮጵያ ይህን አይነት ፍቃድ የሚሰጠው የኢትዮጵያ የማሪታይም ጉዳዮች ባለስልጣንም ቢሆን ለሜቴክ ስራ ምንም አይነት ፍቃድ እንዳልሰጠ ታውቋል።ሌላው ቢቀር ሜቴክ ሁለቱን መርከቦች የንግድ ስራ ሲጠቀምባቸው ማሟላት ያለበትን የአገልግሎት አሰጣጥ ደረጃ ፣ የደህንነት ደረጃ ፣ የባለሙያ ደረጃዎችን ሁሉ ሳያሟላና እጅግ አደገኛ በሆነና ህገ ወጥ በሆነ መልኩ ነው።

ለስራውም ከንግድ መርከብ ጡረታ የወጡና ውላቸው የተቋረጡ ሰዎችን እንዲሁም የውጭ ዜጎችን ይጠቀም ነበር።ሜቴክ መርከቦቹን ይጠቀምበት የነበረው ህገወጥ ተግባር  ነው በሚል የተለያዩ ከበድ ያሉ ውንጀላዎች ይቀርብበታል። በዚህ ወቅት መርከቡን ለመጠቀም ከሆነ ከአንድ የመንግስት የልማት ድርጅት ወደሌላው ማሸጋገር ለምን አስፈለገ?  በሚል ከፍተኛ ትርምስ ተፈጥሮ ነበር።ይሁን እንጂ ሜቴክንም ሆነ ህገ ወጥ ውሳኔ ያስወሰኑ የመንግስት ባለስልጣናትን በህግ የጠየቀ አልነበረም።

 

ሜቴክ መርከቦቹን በሀገር ውስጥ አከናውናለሁ ለሚላቸው ፕሮጀክቶች ግብአት ማመላለሻነት በቅጡ ቢጠቀምበት ምንም አልነበረም ይላሉ ጉዳዩን በቅርበት የሚያውቁ ምንጮቻችን። ሜቴክ ለዚህ ፍላጎቱ የባህር ትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ አገልግሎት ድርጅት አገልግሎትን እየተጠቀመ እስከ 400 ሚሊዮን ብር የአገልግሎት ውዝፍ እየመጣበት በከፍተኛ የመንግስት ሀላፊዎች ውትወታ ነበር ክፍያ የሚፈጽመው።

የሁለቱ መርከቦች አጠቃቀሙም አክሳሪ ነበር።ከሚሰሩበት ወደብ ላይ ቆመው በውጭ ምንዛሬ እለታዊ ክራይ ይከፈልባቸው ነበር።በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር የነበሩት ሱሌይማን ደደፎ ሁኔታው አሳስቧቸው ነገሩን መላ እንዲሉት ለቀድሞው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሀኖም የጻፉት ደብዳቤ አፈትልኮ የማህበራዊ ድረ ገጽ መነጋገርያ ሆኖ ነበር።

ከዚህ ሁሉ የብክነት ጉዞ በሁዋላ ሜቴክ ሁለቱን መርከቦች  ዱባይ ወስዶ ሽጧቸዋል።ለማን? ስንት ሸጣቸው?  የሽያጬ ገንዘብስ የት ገባ? እስካሁን አልታወቀም ።በጉዳዩ ላይ መንግስት ምርመራ መጀመሩን ስምተናል።

ሜቴክ የፈጠረውን ተደጋጋሚ ችግር ታሳቢ በማድረግ ድርጅቱ ወታደራዊና ሲቪል ስራዎች በሚል ለሁለት መከፈሉን በቅርቡ አስታውቋል። በሀገሪቱ ላይ ለደረሰው እጅግ ከፍተኛ ኪሳራ እስካሁን ሀላፊነት የሚወስድ አልተገኘም።

/ENJOY WAZEMA

ኢትዮጵ ከዓለም አየር ንብረት ለውጥ ፈንድ ልታገኝ የሚገባትን 2.5 ቢሊዮን ብር ለምን አጣች? ውድቀት ጋባዡ የሕወሃት ፖሊሲ!

16 Apr

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)</em>
ዋዜማ ሬዲዮ
 


 

በሂደቱ የተሳተፉ ኢትዮጵያውያንና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች ግን ኢትዮጵያ ያቀረበችው ስነድ “የይድረሰ -ይድረስ” የተዘጋጀና የሚጠበቅበትን መስፈርት ያላሟላ ስለነበረ ነው ሲሉ ያስረዳሉ።

“ዘመኑ የሚጠይቀውን አዳዲስ መረጃና አለማቀፍ ሁኔታን ያላገናዘበ ሰነድ ነው። እኛ የባለሙያ ድጋፍ ለማድረግ ፈቃደኛ መሆናችንን በተደጋጋሚ ገልፀን ነበር። የኢትዮጵያ መንግስት ግን ፈቃደኝነት አላሳየም” ይላሉ በለንደን የአየር ንብረት ጉዳይ ጥናት የሚያደርግ ተቋም ባልደረባ – ዋዜማ።

 
ይህም – ባለሙያው ለዋዜማው አርጋው አሽኔ የገለጹትን – የሕወሃት አስተዳደር ጸረ-ባለሙያና ጸረ-መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች የጠላትነት ፖሊሲውን ሚና ለዚህ አያሳንሰውም!
 

ሕወሃት ከኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ጋር መነጋገ ጀምሬያለሁ ሲል፡ ስለድርድር ነው ወይንስ ስለግርግር የሚያወራው? ምን ያህልስ ተዓማኒነት ይኖረዋል? ከነማንስ ጋር ነው የሚደራደረው? የሕዝቡ ፍላጎት እንዴት ይመዘናል?

19 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

Continue reading

ኢሕአዴግ ችግር ላይ ያሉ ግለሰቦችን ለማዳን ብሎ ሐገር ላይ ክህደት አይፈጽምም- ስብሐት ነጋ – ይህ የ2017 ለውጣቸው መሆን አለበት!

4 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

  *  እኔ የትግራይ ሕዝብን አንተን የመሰለ የለም ካልኩት ገድየዋለሁ ማለት ነው

  *  አሁን ያለንበት ሁኔታ ፈታኝ ነው፤ ከዘጠና ሰባቱ የአሁን ይከፋል

  *  መታደስ ማለት ከእንግዲህ ወዲህ ተሀድሶ የለም ማለት ነው

  *  ብሔራዊ መግባባት የሚባለው ቃሉም ብዙ አይገባኝም

  *  ኢሕአዴግ ችግር ላይ ያሉ ግለሰቦችን ለማዳን ብሎ የሐገር ክደት አይፈጽምም

  *  ኢሕአዴግ ችግሮችን ከመፍታት ዉጭ አማራጭ የለውም፤ ይሄን ካላደረገ ግን በአንድ ሀገር ተሰብስቦ የመኖር ነገር አስቸጋሪ ይሆናል

  *  “የትግራይ ሕዝብ ኦሮሚያ ዉስጥ የተሰበሰበን ገንዘብ ላኩልኝ ይላል ወይ…?

Continue reading

ዋዜማ ሬድዮ መጽሔት – ሕወሃት/ኢሕአዴግ የሥልጣን መቀበጣጠሮችና ሌሎችም!

19 Sep

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

የእሁዱን የአዲስ አበባ ሠልፍ ለሚመክቱና መሥዋዕትነት ለሚከፍሉ የፀጥታ ሠራተኞች ሕወሃት ማካካሻ እንደሚሰጥ አስታወቀ – ዋዜማ ራዲዮ!

20 Aug

የአዘጋጁ አስተያየት፡

  በሕግ ሕዝቡን የማያስተዳድረው፣ ራሱን ለሕግ ተገዥ አድርጎ የማያውቀው የሕወሃት አስተዳደር፡ ነፍስ ውጭ ነፍስ ግቢ ሲሆንበት፡ የፀጥታ ኃይሉንም ሠልፉን እስከመከትክልኝ፡ ጠላቶቼን እስከ ጨፈጨፍክልኝ ድረስ (የሲቪልና ጦር ወንጀሎችን በመፈጸም ማለት ነው) ብርና ማዕርግ አርከፈክባችኋለሁ ማለቱ ልብ ሊባል ይገባል!

 

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

በአዲስ አበባ የተቃውሞ ሠልፍ እንደሚደረግ መነገሩን ተከትሎ ሕወሃት ሠልፉን በማናቸውም መንገድ ለማምከን እየተዘጋጀ ነው። ነገ እሁድ በአዲስ አበባ በስሥልጣን ላይ ያለውን ሥርዓት ለመቃወም የተጠራው ሠልፍ በተለያየ የሀገሪቱ አካባቢ ሲካሄድ የሰነበተው ተቃውሞ አካል ነው።
Continue reading

የአገር ሰው ጦማር: ኢሕአዴግስ ቢሆን የት ይቀበራል? – ዋዜማ ራዲዮ

18 Jan

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
በሙሔ ሐዘን ጨርቆስ

ዋዜማን ለማዳመጥ ከዚህ በታች ያለውን ኦዲዮ ሊንክ ይጫኑ፦

መቼ ለታ መታወቂያ ላሳድስ ቀበሌ ሄድኩኝ፡፡ እርግጥ ነው መታወቂያዬ ጊዜው አላለፈበትም፡፡ ቢሆንም መጪውን ጊዜ ላምነውአልቻልኩም፡፡

አትፍረዱብኝ ወገኖች! የኢህአዴግ ሥልጣን፣ የአዲሳባ ዜግነትና የዛፍ ላይ እንቅልፍ አንድም ሦስትም ናቸው፡፡ አዲሳበባዊና ፍልስጤማዊ መሆን መሳ ሆነዋል፡፡ መሬቱ የማን እንደሆነ አለየለትም፡፡ መታወቂያ የሚያድሰው የቀበሌያችን ኃላፊ ራሱ በቀደም ነው ከሰሜኑ የአገራችን ክፍል የመጣው፡፡ ብቻህን ካዛንቺስ ደርሰህ ና ቢባል በእርግጠኝነት ተክለኃይማኖት ጋ ይጠፋል፡፡
Continue reading

%d bloggers like this: