Tag Archives: wollega

ወለጋና ምዕራብ ሸዋ ከተሞች ውስጥ ዜጎች በሕወሃት እየተገደሉ ነው! ሕዝቡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን በመቃውሙ መንገዶች ዝግ ናቸው!

3 Mar

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 

 

በየአካባቢው ሕዝቡ አስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ረግጦ ተቃውሞውን መግለጹን ቀጥሏል! ሕዝቡ ማሰብ የተሳነውን ሕወሃት ውድቀቱን እንዲያፋጥን እየረዳው ነው!

25 Feb

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

ኢትዮጵያ ውስጥ የሕዝብ አመጽ እየተጠናከረ ነው፡ የታሪካዊዋ አምቦ ግለት!

13 Jul

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
by Merga Dejene
 

የአምቦ ከተማ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው፡፡

ለተቃውሞው ምክንያት የሆነው በቅርቡ ተገቢ ያልሆነ ግብር ነጋዴው ላይ መጨመሩ ሲሆን። ስርአቱ የህዝቡን ጥያቄ በሰላማዊ መንገድ ከመመለስ ይልቅ ሃይልን መፍትሄ አድርጎ መንቀሳቀሱ በተፈጠረው ግጭት አንድ የፌደራል ፓትሮል መኪና ሲቃጠል ሌላ ተሰባብሯል፡፡ እንዲሁም አንድ አውቶብስ ላይ የመሰባበር አደጋ ደርሶበታል፡፡ ከፍተኛ ተኩስ እንዳለና ወደ ወለጋ የሚወስደው መንገድም እስካሁን እንዳልተከፈተ ለማወቅ ተችሏል፡፡

በከተማው ያሉ አገልግሎት የሚሰጡ ተቋማት ሙሉ በሙሉ ተዘግተዋል። ከፍተኛ የግብር ጭማሪን ተከትሎ በሌሎች አካባቢዎች የተቃውሞ እንቅስቃሴ ሊኖር እንደሚችል አስተያየት ሰጪዎች ይናገራሉ።
 

ተዛማጅ:

BreakingNews: Several districts in Oromia & SNNPR fall from dusk to dawn curfew; night public transport stopped

ትልቁ የኢትዮጵያ ‘ፌደራል’ በጀት ድክመቱ፣ገጽታዎቹና ውስብስብ ችግሮቹ
 

የአጋዚ ጦር መከማቸት ሳያግደው በኦሮሚያ ተቃውሞው በተጠናከረ መንገድ እያገረሸ ነው!

20 May

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)
 


 

በኦሮምያ ህዝባዊው ተቃውሞው አገረሸ

ግንቦት 11 2008 ዓ/ም (ኢሳት ዜና):- ለሳምንታት ጋብ ብሎ የነበረው የኦሮምያ ክልል ተቃውሞ ካለፈው ሳምንት ጀምሮ መጠነኑን እያሰፋ በመምጣት ላይ ሲሆን፣ ዛሬ በምእራብ ሃረርጌ የማሳለ ከተማ ነዋሪዎች ወደ አደባባይ በመውጣት ተቃውሞ አሰምተዋል። ከሁለት ቀናት በፊት በአሰቦ ከተማ ተመሳሳይ ተቃውሞ የተካሄደ ሲሆን፣ ትናንት ምሽት ደግሞ በሃሮማያ ዩኒቨርስቲ የፈደራል ፖሊሶች በተማሪዎች ላይ እርምጃ ወስደዋል። በርካታ ተማሪዎችም መጎዳታቸው ታወቋል።

መንግስት የአዲስ አበባ አዲሱን ማስተር ፕላን መተውን በይፋ ካስታወቀ በሁዋላ፣ የአርሶ አደሩን መሬት መልሶ የሚወስድበትን አዲስ እቅድ ይፋ አድርጓል። እቅዱን አርሶ አደሮች አጥብቀው በመቃወም ላይ ናቸው።
 

ቤተ እምነቶች የሰው ሕይወት ጭፍጨፋና የንብረት መውደም እንዲቆም የጠየቁ አስመስለው በኦሮሚያ የእኩልነት ትግል ላይ የተነጣጠረ አቋም አንጸባረቁ!

25 Feb

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)
 

የሕወሃት ፋና ረቡዕ የካቲት 24/2016 ባወጣው ዜና “የኢትዮጵያ የኃይማኖት ተቋማት ጉባዔ በሰው ሕይወት፣ በእምነት ተቋማትና በሕዝብ ሃብት ላይ የደረሰውን ጥፋት አወገዘ” በማለት ያቀረበውን አንብቤያለሁ።
Continue reading

ሕወሃት የኦሮሚያን ሕዝባዊ ተቃውሞ አከሸፍኩ ብሎ መፎከሩን ሳያቆም፣ለምን እንደገና አገረሸ?

29 Dec

በከፍያለው ገብረመድኅን – The Ethiopia Observatory (TEO)

ለሣምንት ጋብ ብሎ የነበረው ሕዝባዊ ተቃውሞ ካለፈው አርብ ታህሳስ 25 ቀን 2015 ጀምሮ በምዕራብ ወለጋ፣ በም ዕራብና ሰሜን ሸዋ በተለያሉ ከተሞች ዩኒቨርሲቲዎችና ሁለተኛ ድረጃ ትምህርት ቤቶች ተቀጣጥሎ መቀጠሉን ኢሣት የሃገር ቤት ምንጮቹን ዋቢ በማድረግ ምክንያቱን ዘግቧል።
 

እስካ ሣምንት በፊት በነበረው የአምስት ሣምንት የሕዝብ ተቃውሞ 122 ሰዎች በሕወሃት ወታደሮችና ፖሊሶች ተገድለዋል፣ እንዲሁም ከአራት ሺህ በላይ ዜጎች በእሥር ላይ መሆናቸውም ተገልጿል። እሥሩም፣ ግለሰቦች የደረሱበት ቦታ አለመታወቁ ቀጥሏል።

ባለፈው ዓመትና አሁንም ከፍተኛ የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተፈጸመበት የአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ ኢሣት እንደዘገበው፣ የዩኒቨርሲቲው ካምፐስ ወታደራዊ ካምፕ በሚመስል መልኩ በሠራዊት መጥለቅለቁን ለማወቅ ተችሏል።

ምንግግስት ተማሪዎች ትምህርት ከመጀመራቸው በፊት ስብሰባ እንዲሳተፉ ያደረገው ጥሪና ግፊት ተማሪዎቹን እንዳስቆጣችው ይነገራል።

በአምቦ ዩኒቨርሲቲ በፖሊስ ዱላ የተጎዱ ተማሪዎች ወደ ሆስፒታል ተወስደው ዕርዳታ ከተደረገላቸው በኋላ ወደ እሥር ቤቶች ተግዘዋል።

አብዛኛው ተማሪ ግን ካምፐሱን ለቆ ወጥቷል።

የአምቦ ተማሪዊች ለኢሣት እንደገለጹት፣ አሁን ባለው ሁኔታ ‘መንግሥትና’ ሕዝብ ሆድና ጀርባ ሆነዋል ይላሉ። በወለጋ በሆሮ ጉድሩ፣ በሰሜን ሸዋ ኢጅሬና ሂጃቡ አቦ ተማሪዎች ክፖኪስና ወታደራዊ ኮምንዶች ጋር መጋጨታቸው ተገልጿል።

ሰሞኑን ከ15 በላይ የሚሆኑ ታዋቂ የኦሮሞ መሪዎች እየተለቀሙ መታሠራቸው ቀደም ብሎ የተዘገብ ሲሆን፡ የአስተዳደሩ ጥቃት ኦሮሞና ኦሮሞ ያልሆኑ ጋዜጠኞችም ላይ ጥላውን አጥልቷል።

በፖለቲካ ፓርቲዎች ደረጃም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግሬስ (ኦፌኮ) የመጀመሪያው ግንባር ቀደም ተጠቂ ሲሆን፣ ሌሎችም – ለምሣሌ እንደ ሰማያዊ ፖርቲ/አንድነት ዐይነቶችም – አንዳንድ አባሎቻቸውን በማሠር ዱላው አርፎባቸዋል።

አሁን ካለው ሁኔታ የሚታየው፣ ሁሉን ረግጦና አስፈራርቶ የመግዛት የሕወሃት የጠብ ያለሽ በዳቦ ለመሆኑ ምንም አያጠራጥም። ውድቀት ሲቃረብ፣ የዚህ ዐይነቱ ቀቢሰ ተስፋ በታሪክ በተደጋጋሚ መመዝገቡ ይታወቃል!
 

ኢትዮጵያ ውስጥ በርካታ ወጣቶች በየሥፍራው በደህንነት ኃይሎች እየታሠሩ፡ እየታፈኑ ነው

6 Jun

Posted by The Ethiopia Observatory (TEO)

አቦከር መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሐረር:

ግንቦት ፳፰ ቀን ፳፻፮ ዓ/ም (ኢሳት ዜና):- የአቦከር መሰናዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች የታሰሩት የሁለተኛ ደረጃ ፈተና ካጠናቀቁ በሁዋላ ከግቢያቸው በመውጣት መፈክሮችን እያሰሙ ወደ ማሃል ከተማ በመጓዝ ላይ እያሉ ነው። ተማሪዎቹ “በሀረር ክልል የሚታየው አድሎ ይቁም፣ ፍትሃዊ አስተዳደር ይኑር፣ መንግስት በህዝብ ላይ የሚያደርሰው በደል ይቁም” የሚሉና ሌሎችንም መፈክሮች እያሰሙ ተቃውሞአቸውን ሲገልጹ አርፍደዋል።
Continue reading

Ethiopia’s political parties/organizations condemn TPLF regime’s land grab & bloodthirstiness

2 May

By Keffyalew Gebremedhin – The Ethiopia Observatory

My understanding of what is taking place currently in Ethiopia is brutal use of forces by TPLF agents. It is clear case of violation of human rights. This and all other manifestations are designs by the TPLF against the people of Ethiopia. The only difference is that it administers its doses of brutality on seemingly systematic basis, picking one group this week, the other next week, and then the following on and on – diminishing our country piece by piece.
Continue reading

%d bloggers like this: